January 13, 2019
5 mins read

አፋር ሰመራ ላይ ከኢትዮ ጁቡቲ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ዋለ

አዲስ በአበባን ከአዋሽ-ድሬዳዋ/ሐረር-ጅግጅጋ እና አዲስ አበባን ከአዋሽ-ሰመራ-ጅቡቲ የሚያገናኘው መንገድ በአፋር ክልል በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ምክንያት ከጠዋት ጀምሮ ተዘግቷል።ችበተቃውሞው የባቡር ትራንስፖርትም ተቋርጧል።
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8
በአፋር ክልል የጀቡቲ ዋናው መንገድ በህዝብ መዘጋቱን ተከትሎ አክቲቭስት አካደር ኢብራሂም እንደገለጹት “በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን በኢሳና አፋር ለዘመናት በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች የአከባቢው ህዝብ ሠላም አጥተዋል። በተለይ ግን አሁን ከለውጥ ጋር በተያያዘ በኢሳ ታጣቂዎች በተነሳው ግጭት የብዙ ሰዎች ህይዎት ልያልፍ ችሏል። ከለውጡ በፊት ከአንዳንድ የመከላኪያ ጀኔራሎችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር የተደራጀ የኮንትሮባንድ ንግድን በመዘርጋት፣ ጎን ለጎን ደግሞ የአፋር አርብቶ አደሮች በአከባቢው በሰላም እንዳይኖሩ ሲያድርግ ቆይቷል። ይሁን እንጂ አሁን በተለየ መልኩ ከለውጥ አደናቃፊዎችና ከጀቡቲ በሚደረግለት ድጋፍ እንዲሁም በግልጽ በሚያራሚዱት የታላቋ ሶማሊያ የመሬት ማስፋፋት ህልማቸው እዉን ለማድረግ የአፋር ክልልን ባንዲራ በማቃጠል የሶማሌ ክልል ባንዲራን ሰቅሏል።” ብለዋል::
አቶ አካደር አክለውም ‘በዚህ የተነሳ በአከባቢው ሰላም ለማስከበር የአፋር ክልል ልዩ ፖሊስ መግባቱ ይታወሳል። የክልሉ ልዩ ሃይል እዛ ከሰፈሩ በሗላ በተደጋጋሚ የኢሳ ታጣቂዎች ወደ ካምፓቸው በመምጣት ትኩስ ከፍቶባቸው ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ይሁን እንጂ የፌደራል መንግስት በአዲስ አበባ ከተወሰኑ የአፋር ክልል አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት የአፋር ክልል ልዩ ሃይል አከባቢዉን ለቆ እንዲወጣ ወስኗል። ይህ ለህዝብ ግልጽ ያልሆነው ህግ ወጥ ውሳኔ በመላው የአፋር ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል።” ብለዋል::

‘ውሳኔው የጠቅላይ ሚንስትር ነው ቢባልም; ውይይቱም ሆነ ውሳኔ ለአፋር ህዝብ ግልጽ አለመሆኑን ለማሳወቅ; ‘የታላቋ ሶማሊያ ህልም በአፋር ምድር እዉን አይሆንም በማለት; “የአፋር ፖሊስ የት እንደሚሰፍር የሚወስነው አፋር ብቻ ነው በማለት እንዲሁም እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ በሰላም አብሮን መኖር የማይፈልገው የኢሳ ሶማሌ ጎሳ ከክልላችን ይውጣልን በማለት ህዝቡ ከሰመራ ጀምሮ እስከ አዋሽ ያለው መንገድ ተዘግቷል” ያሉት አቶ አካደር “የዱኮሂና ወጣቶች ሰላም ለማውረድና መንገዱን ለመክፈት የሚከተሉት 3 ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል:: እነርሱም:
• የኢሳ ሶማሌ ጎሳዎች በኢትዮጲያዊነትና በሰላም መኖር ስለማይችሉ ከዚህ አከባቢ በ አስቸኳይ ይውጡልን።
• የፌደራል መንግስት በህገ ወጥ መንገድ ከ አከባቢው እንዲነሱ የተደረገው የልዩ ሃይል ፖሊስ ወደ ቦታው በአስቸኳይ ይመለሱ።
• የፌደራል መንግስትና የ አፋር ክልል መንግስት ስለጉዳዩ አስቸኳይ ማብራሪያ ይስጡ።
ተቃዉሞው ምላሽ እስኪገኝ እንደሚቀጥል የአፋር ወጣቶች እያሳወቁ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል::

በጉዳዩ ላይ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከመንግስት በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም::

93717
Previous Story

የትግራይ ተወላጆች ጋምቤላን ለቀው እየወጡ ነው

93723
Next Story

የአማራና ሕወሓት ያደራጀው የቅማንት ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop