የአማራና ሕወሓት ያደራጀው የቅማንት ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ

የአማራና ሕወሓት ያደራጀው የቅማንት ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ:: ስላሬ ፣መተማ ፣ደንቢያ ፣ ቆራ ኮኪት ጭልጋ ፣አብርሃደጅርሃ ወዘተ ግጭቱ እየተባባሰ እንደሆነ ከቦታው የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8
የቀድሞው የመኢአድ አመራር ለገሰ ወልደሃና እንደገለጹት “ትላንትና ትክል ድንጋይ የሚኖሩ የቅማንት ኮሚቴ ነን የሚሉ ሰዎች ወጣቶችን በማደራጀት ከጎንደር ወደ ሳንጃ ሁመራ የሚደረግ ጉዞን መንገድ በዘግተው ወጣቶችን አግተው እንደነበረ ከአካባቢው ያገኘሁት መረጃ ገልፆልኛል” ብለዋል::

የትግራይ ክልል መንግስት ከትንኮሳ አልፎ ሙሉ ለሙሉ ወደ ጦርነት እየገባ ነው ሲል መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ተናገረ:: “በትናንትናው እለት በጎንደር ሽንፋ ከፋኖዎቻችን ጋር ጦርነት ከቅማንት ኮሚቴ ጋር ተቀላቅሎ የገባው የህወሃት ቡድን ሲመታ የትግራይ ተወላጆች መታወቂያዎች ተገኝተዋል” ያለው መቶ አለቃ ማስረሻ ይህንንም መታወቂያ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ በማህበራዊ ገጾች ለቆታል::

“ማታ ላይ በዳዛ ከ 30 በላይ የአማራ ቤተሰቦቻችንን ቤት አቃጥለዋል። ሮቢት ላይም አንድ የሙስሊም ወንድማችንን ገንዘብ ካላመጣህ በሚል በጸረ ሰላሙ ቡድን መገደሉን ሰምተናል።” ብሏል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አምባገነናዊ ዘረፋ በብሔራዊ መረጃ | የውጭ ሃገር ኑሯቸውን ጥለው ሃገር ቤት ለንግድ የገቡ ዲያስፖራዎች ገንዘብና ንብረታቸውን እየተቀሙ ነው | ጥብቅ መረጃ
Share