April 9, 2017
19 mins read

 ማነው? እንዴትስ ነው? (ተገናው ጎሹ)

ማነው?እንዴትስነው?

አዎ!

የረጅሙታሪክየተጋድሏችን፣

ነፃየራስአገርየማቆየታችን፣

ለትውልድትውልድማስተላለፋችን፣

የጋራኩራትነውየጋራክብራችን።

ዋጥአድርገንችለንየቤትብሶታችን፣

የጭቆናንቀንበርየገዢዎቻችን፣

በደምበአጥንትዋጋአገርማኖራችን፣

እንደሕዝብእንደአገርአብረንመዝለቃችን፣

የተገነባነውበምስጢረአብሮነትበውህድደማችን።

ግን

የእብደትፖለቲካንመልክማስያዝተስኖን፣

አብሮነትንሳይሆንጥላቻናቂምንእየተገባበዝን፣

ለከፋፋይናለጨካኝገዢዎችእየተመቻቸን፣

ከረዥሙታሪክከደጉምከክፉምባለመማራችን፣

ነፃባቆየናትበገዛምድራችን፣

ስንቀበልባትስቃይመከራችን፣

ማነውእሚፈታው፣እንዴትነውእሚፈታውእንቆቅልሻችን?

አዎ!

የዚያባለታሪክልጆች፣የልጅልጆችእንደመሆናችን፣

ጥልቅነውሰፊነውክብርኩራታችን።

ግን

በአያት፣በቅድመአያትበተሰራታሪክዘፈንእየዘፈንወይምእየፎከርን፣

ልማድእስኪመስልዘመንእየቆጠርን፣ቀንንእየዘከርን፣

ከተሰቀለበትጦርጋሻእያወረድን፣

ጧሪናቀባሪበሌለውደረትላይሜዳሊያአንጠልጥለን፣

ታሪክንለከዱሸፍጠኛገዢዎችአጃቢዎችሆነን፣

ጎንበስቀናብለንእነሱንደጅጠንተን፣

ከነሱያደረንፍርፋሪለቅመን፣

ደግሞምሲሳካልንኢንቬስተሮችሆነን፣

በዝርፍያውበቅሚያውአብረንተሰማርተን፣

ዘመንመቁጠራችን፣እዚህመድረሳችን፣

እንዴትነውእሚፈታው፣ማንስነውእሚፈታውእንቆቅልሻችን።

አዎ!

የውጪወራሪዎችእንደተመኙልን፣እንደዘመቱብን፣

የዉስጥገዦቻችንእንዳጎሳቆሉን፣

በብሔር፣በቋንቋ፣በባሕልልዩነትእንደመብዛታችን፣

ቤትአልባያልሆነውአፍርሰንቤታችን፣

በመዋሀዱነውለአገርየከፈልነውመስዋዕቱደማችን።

የሩብምዕተአመቱየጎጠኞችእብደት፣የዘረኞችፅልመት፣

ፍርስርስያረገውየስንቱንቤትንብረት፣

እርግፍግፍያረገውየስንቶቹንህይወት፣

ታሪክየለወጠውወደተረትነት፣

ምስቅልቅልያረገውያገርንምንነት፣

እስኪጠፋንድረስትርጉሙየዜግነት፣

መወገድአለበትበላቀትብብር፣በማይፈርስአንድነት።

ይሄእውንሆኖለዉጥመምጣትካለበት፣

የውድቀታችንምንጭየሩብምዕተአመት፣

አስተሳሰባችንመለወጥአለበት።

እኛውችግርፈጥረን፣እኛውአወሳስበን፣

ጥበቡጠፍቶብን፣ቅንነቱጎሎን፣ትግሥትአልባሆነን፣

በሕዝብለሕዝብሳይሆን፣

በቡድንለቡድንእየተደራጀን፣

የግልጥቅምንናዝናንእያሰላን፣

የቆጠርነውእድሜ፣ያሳለፍነውዘመን፣

እስቲይጸጽተንሕመሙይሰማን።

አዎ!ትክክልነው፣

ጠንክሮእንዲወጣየምንፈልገው፣

የዜግነትመብትኢትዮጵያዊነትነው።

ይህግንየሚሆነው፣

ሌሎችማንነቶችበጥበብበትግሥትሲስተናገዱነው።

ግን

አሁንምበዚህወቅት፣ዘረኛገዢዎችፍፁምባበዱበት፣

በሀሳብየተለየንበሚያሰቃዩበት፣

ቀጭንትእዛዝሰጥተውበሚያስገድሉበት፣

ገዳይሀይላቸውንጭራሽጀግናብለውበሚያወድሱበት፣

ስቃይ፣ሰቆቃውን፣ነፃእርምጃዉንበአዋጅባወጁበት፣

አልተጸየፍነውምክፉውንልዩነት፣

የተጓዝንበትንለሩብምዕተአመት።

ይሄክፉአዙሪትእሽክርክሪታችን፣

እንዴትነውእሚፈታው፣ማንስነውእሚፈታውእንቆቅልሻችን?

አዎ!

የእምነታችንታሪክበዉንያኮራናል፣

እስላምክርስቲያኑንበአንድላይአኑሯል፣በፍቅርአጣምሯል።

የአገርፍቅርናሐይማኖቶቻችን፣

ጣምራእሴቶችናቸውያኩሪዉታሪካችን።

የወገንመከራግድይለናልብለው፣

ባለጌገዦችንየገሰፁደፍረው፣

መስዋትየከፈሉበቃላቸውአድረው፣

በታሪክጉዟችንታላቅሥፍራአላቸዉ።

ግን

አሁንባለንበትበዚህዘመናችን፣

ካንጀትሳይሆንካንገትሆኖፀሎታችን፣

ዝናአድርገነውመብዓማቅረባችን፣ምጽዋትመስጠታችን፣

ለእንጀራማብሰያኑሮማሻሻያሲሆንስብከታችን፣

ወደቤተአምልኮመመላለሳችን፣

ተራልማድሲሆንያልገባዉስጣችን፣

ድነንማዳንሲያቅተንአገርወገናችን፣

እግዚኦአድነንእያልንመጮሀችን፣

እንዴትነውእሚፈታዉ፣ማንስነውእሚፈታውእንቆቅልሻችን?

መከራሲነግስገዝፎስንፍናችን፣ገኖፍራታችን፣

የእግዜርቁጣነዉብለንመስበካችን፣ወይማስተማራችን፣

ድርጊትአልባፀሎትየማነብነባችን፣

ከመድረክአላልፍሲልዜማመዝሙራችን፣

ማነውእሚፈታው፣እንዴትነውአሚፈታውእንቆቅልሻችን?

የፈጣጠርነውንመከራናስቃይእኛዉእራሳችን፣

የተጫነብንንየሰቆቃቀንበርበገዢዎቻችን፣

አንተ(ፈጣሪ)አቅለውብለንየመተኛታችን፣

መከራናስቃይየጽድቅስንቅነውእያልንመስበካችን፣

የእንችላለንናየድርጊትመንፈስንየማኮስመናችን፣

ማጠርያለበትንየመከራዘመንየማራዘማችን፣

ማነውእሚፈታው፣እንዴትነውእሚፈታውእንቆቅልሻችን?

ያደንቁሮገዢዎችተባባሪሆነን፣

ሰብአዊማንነትእንዳልሆነሲሆንእየተመለከትን፣

እንዴትለምንሲሉንፖለቲካእያልንየመቀለዳችን፣

እንዴትነዉእሚፈታዉ፣ማንስነውእሚፈታውእንቆቅልሻችን?

በቁሙእያለያልደረስንለትን፣አይዞህያላልነውን፣

በረሀብሲቀጡትያልተቆጣነዉን፣ያላመረርነውን፣

በጥይትሲመትሩትጋሻያልሆነዉን፣

በቆሻሻአኑረውቆሻሻሲያለብሱትመቁረጥያቃተንን፣

ምንአርግነውእምንለዉበሰማይያለውን?

ዝምጭጭብለንቆመንአስገድለን፣

በየቤተእምነቱዙሪያተደርድረን፣

በማኀሌትሆነንቤተመቅደስገብተን፣

እባክህንማረዉ፣እባክህንማራትብለንእንጮሀለን፣

ደግሞምእንደልማድከበሮእንመታለን፣

ድምፁንከፍአድርገንፅናእናንሿሿለን፣

በዜማበንባብሙሾእናወርዳለን፣

ከከንፈርየማያልፍየመጽናኛዲስኩርእንደሰኩራለን።

ይሄእንቆቅልሽ፣ይሄየሰቆቃው፣

እንዴትነውእሚፈታው፣ማንስነውእሚፈታው።

ረቂቅአእምሮብቁአካልየሰጠን፣

እንድኖርአደለምየታምርነፃአውጪእየተጠባበቅን።

እኛግንአሁንምድርጊትአልባጩኸትእናስተጋባለን፣

ማገናኘትአቅቶንቃልናድርጊትን፣

ታምርአዉርድእያልንእግዚኦእንላለን።

ደሞየሚገርመውእጅግየሚቆጨዉ፣

ባለንበትቆመንዘመንስንቆጥርነው።

አዎ!በታላቁመጽሐፍእንደተጠቀሰው፣

ወደፈጣሪዋእጅየዘረጋችዉ፣

የኛአገርመሆኗትልቅትርጉምአለው።

ሁሌምተዘርግተውአቤትሐያሉአምላክየሚሉትእጆቿ፣

ስጥልኝስትልነውፍቅርናአብሮነትለመላዉልጆቿ፣

እኛግንእየተለያየን፣

እየተጠላለፍንአብረንእየወደቅን፣

ፍቅርንእየጠላንጥላቻንአፍቅረን፣

ለወገንመዘርጋትተስኖትእጃችን፣

ግሩምነዉእንላለንበታላቁመጽሐፍበመጠቀሳችን፣

ታዲያይህክፉአዙሪትእሽክርክሪታችን፣

ማነውእሚፈታው፣እንዴትስይፈታልእንቆቅልሻችን።

አዎ!

እንደኛስንፍናእንደክፋታችን፣

እየተጠላለፍንእንደመዉደቃችን፣

የመከራዘመንእንደማርዘማችን፣

ጀግናአልባአልሆነችምኢትዮጵያአገራችን።

ቅድስትማሀፀኗጨርሶእማይነጥፈው፣

ዛሬምጀግኖችወልዷልመቼምአይሳነው።

በዉብማሀፀኗበተሸከማቸዉ፣

በእናትነትክንዷአቅፎባሞቃቸው፣

በጡቶቿወተትበመገበቻቸው፣

በቃልኪዳንፀንተዉበእምነትተሳስረው፣

በዉስጥምበዉጪምከየመኖሪያቸዉ፣

ነፃነትበነፃአይገኝምብለው፣

የቁርጥቀንልጆችፍልሚያውቦታናቸዉ።

አዎ!እዚያትግልሜዳድምጽያስተጋባል፣

አድማሱንአቋርጦአየሩንሰንጥቆኢትዮጵያንአዳርሷል።

ድምበርንተሻግሮውቅያኖስአልፎይሄዳልይነጉዳል፣

ወገንያገርልጅንበአዋጅይጣራል፣

እንዲህይናገራል።

መደማመጥአቅቶንመከባበርጠልተንእዚህየደረስነው፣

የጨካኝዘረኞችሰለባየሆነው፣

የዕለትምግብእንኳዋስትናያጣነዉ፣

የተመፅዋችነትእስረኛየሆነው፣

በመዝገበቃላትየረሀብፍቺመፍቻምሳሌየሆነዉ፣

በማንነታችንየተሸማቀቅነዉ፣

ከየትነህ?ከየትነሽ?የሚልንጥያቄበእጅጉእምንሸሸዉ፣

ደፍረንእንቀበልችግሩከኛዉነዉ።

እናምይሄእሽክርክሪትእንቆቅልሻችን፣

መፈታትአለበትበኛዉበራሳችን።

ደግሞምያስተጋባልበአፅንኦትያዉጃል፣

እንዲህምይለናል።

መሆኑንካመንንየመፍትሔውቁልፉከኛዉከራሳችን፣

እንዴትነውእምንፈታውእንቆቅልሻችን?

ይክበድምይቅለልምመልሱአንድብቻነው፣

የድል፣የነፃነትጠበቃዋስትናዉ፣

እጅለእጅተያይዞመታገልብቻነዉ።

እጅግዘግይተናል፣መከራዉምበዝቷል፣

የተናጠልናየሽኩቻውመንገድከእንግዲህይበቃል።

Tegenaw Goshu (.ጐሹ )

April7, 2017
Go toTop