March 28, 2017
3 mins read

ይበቃል ከአንግድህ …….የበላይ ለመሆን

የበላይ ለመሆን አየተሯሯጠ

ሁሉም ሰዉ የራሱን መንገዱን መረጠ

ሌላዉን ረግጦ መሰላል አድርጎ

አምጦ ሳይወልደዉ ሊያደርገዉ ማደጎ

ስም አና አድራሻዉን ቀይሮ አስቀይሮ

ልያኖረዉ ፈለገ በስቃይ በአሮሮ

አልያም ሊያስወታዉ ከአገር አስመርሮ

አረ ለመሆኑ የዚህ ሰዉ መነሻዉ

የት ነበረ ጫፉ የስልጣን ደረጃዉ

ብቃቱ ሳይኖረዉ ይገባኛል ያለ

ስልጣን ተፈናጦ ባደባባይ ዋለ

በስዉር መርዝ ዉሸት ስንቱን አታለለ

ብቃቱ ሳይኖረዉ የበላይ መሆኑ

አለቃ ነኝ ብሎ በራስ መወሰኑ

አኔ ነኝ አያሌ አንድህ መዳፈሩ

ሰዉ ስለታጣነዉ የሚቆም ላገሩ

ተነድቶ ቢገባም ሰዉ ያለ መስመሩ

በዘር ቁአት ተጥዶ ያለአገር ሊጠሩ

አገር ምን ያረጋል ብለዉ አንድቀሩ

ነበር የታሰበዉ ወድቀዉ አንድቀሩ

ሀፍረት የለሽ ነዋ አንድህ መናገሩ

ጀግኖች በየቦታዉ መች ወድቀዉ ሊቀሩ

ይነሳል ከጉአዳዉ ይቆማል ላገሩ

ዘር በሀገሩ ነዉ ባህልም በመንደሩ

ታዲያ ለምንድነዉ አንድህ መዳፈሩ

ራሱን ነግሶ አግዝፎ በወንበሩ

ማንም አይነካኝም ብሎ መፎከሩ

ጫካ የወለደዉ ገብቶ ከመዳከሩ

ሰዉ ስለታጣ ነዉ የሚቆም ላገሩ ?

ቁጭት የማይዘዉ ለወገን ለክብሩ

ባንድራ ጨርቅ ነዉ አያለ ሲያወራ

ላገር ክብር የለሽ ምንም የማይፈራ

ለሆዱ የኖረ የባንዳ ጎተራ

ሁሉን ሊሸጠዉ ነው ይሄዉ በየተራ

ከጫካ አፈትልኮ ከቶ አገር ሊመራ

ምን ዓአምሮ ኖሮት ባገሩ ሊኮራ

መቼ ብቃት ኖሮት ይህንን ሊሰራ

ልሸጠዉ ነው አንጂ ሁሉን በየተራ

ምንም ሳይሰማዉ ያገር ልዕልና

ተረግጦ ተጥሎ ያገር ስብአና

የማንነት ምንጩ ከአገር ዉጭ ሆነና

የሰዉ ዉህደቱ ጥምረቱ ቀረና

ከፋፍሎ ሊያስከረዉ በዘር ጎጥ ቀጠና

ማስደለቅ ጀመረ ከበሮ በገና

የበላይ ነኝ አለ ራሱን አንግሶ

አለቃ ለመሆን ለአርባ ዓመት ደግሶ

የአገር ጠላቶችን አንገት ተንተርሶ

በጉያቸዉ ገብቶ የመርዝ ጉርሻ ጎርሶ

የዋጠዉን ሲለቅ ሁሉም ተተራምሶ

አለቃ ነኝ አለ አገር ደረማምሶ

ትዉልድ አበጣብተህ ከፋፍለህ መግዛትህ

ይበቃል ከአንግድህ ተቆርጧል ገመድህ

የመዉደቂያህ ጊዜ አሁን ነው ሰዓትህ

Go toTop