July 9, 2013
2 mins read

አቶ ኩማ ደመቅሳ በአቶ ድሪባ ኩማ ተተኩ

(መንግስታዊው ራድዮ ፋና እንደዘገበው) እየተካሄደ ያለው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ አቶ ድሪባ ኩማን የከተማዋ ከንቲባ አደርጎ ሾመ፡፡ ጉባኤው የቀድሞው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን እና ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ወልደገብርኤል አብርሃን በአዲሱ ምክር ቤትም በነበራቸው ስልጣን እንዲቀጥሉ መርጧቸዋል፡፡ አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ የከተማዋን ቁልፍ ከተሰናባቹ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በመረከብ ከአፈ ጉባኤዎቹ ጋር ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
– አዲሱ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ለምክር ቤቱ የካቢኒ አባላቶቻቸውን በማቅረብ አስፀድቀዋል ።በዚህም መሰረት
– አቶ አባተ ስጦታው ምክትል ከንቲባ
– አቶ ሀይሌ ፍሰሃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ
– አቶ ይስሃቅ ግርማይ የአቅም ግንባታ ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ጥላሁን ወርቁ የጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ገብረ ፃዲቅ ሀጎስ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ
– ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ኤፍሬም ግዛው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ፎርኢኖ ፎላ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ሰለሞን ሀይሌ የመሬት ማኔጅመንትና ልማት ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ዲላሞ ኦቶሬ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ
– አቶ ፀጋዬ ሀይለማርያም የፍትህ ቢሮ ሀላፊ
– ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል ።

ምንጭ፡ ራድዮ ፋና

Go toTop