ካርቱም ሱዳን ያሉት የኢትዮጵያውያን ስደተኞች እየደረሰባቸው ያለው መከራ እና ስቃይ በተመለከተ የተጥናቀረ ፁሁፍ።
በሱዳን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ
እኛ ሃገር ሱዳን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል እለት በእለት እየተከታተልን ጮኸታችን ሰሚ ያግኝ ዘንድ እናጋልጣለን። በመጀመሪያ የእሮሮችን ጹሁፍ እንደጠቀስነው የጊዜ ገደቡ አልፎ አፈሳው በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል ወያኔና የሱዳን መንግስት ያዘጋጁት የስድስት ወር ጊዚያዊ መታወቂያ ለማውጣት የሚከፈለው ገንዘብ መጠን 110 የሱዳን ፓውንድ ነበር አሁን ግን 170 ደርሷል። ያም ሆኖ መታወቂያው ከእስር እና ከአፈሳ አልታደጋቸውም።
የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)
ባአሁኑ ጊዜ ሱዳን ውስጥ ያለው የሙቀት ደረጃ 50 ዲግሪሴንቲግረድ በደረሰበት ግዜ 400 የሚሆኑ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እምዱሩማን እስርቤት ይሰቃያሉ እነዚህ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን የመጨረሻ እጣቸው ፍርድ ቤት ቀርበው የገንዘብ መቀጮውን ከከፈሉ በኋላ ወደ ሃገር መባረር ነው።
የሰሩበትንም ሆነ የደከሙበትን ገንዘባቸውንና የቤት እቃቸውን እንኳን የመያዝ ወይም የመሸጥ ጊዜ አይሰጣቸውም። በጣም የሚገርመውና ልብን የሚያደማው ለዘህ ሁሉ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባጀት መድቦ አፈሳውን ለሚያደርገው የሱዳን ሰራዊት መገልገያ መኪናዎች ሙሉ ወጨው የሚሸፈነው ወያኔ ነው። ይህ ሆኖ እያለ እስር ቤት ውሰጥ እህት ወንድሞቻችን ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል ። ይህንን ቤት ለቤት ገፈፋ በተመለከተ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች የሆነው መስሪያቤት ዩኤን አች ስአር (UNHCR) አሳምሮ ስለሚያውቅ ሆት ላይን አዘጋጅቶ ችግር ለሚገጥመው ስድተኛ መፍትሄ ይሰጥ ይመስል 0183587005 ቁጥር ለጥፏል:: በጣም የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ ግፍ በ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ሲፈፀም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነን የሚሉ ድርጅቶች አንዳችም ድምፅ አለማሰማታቸው ነው።
እዚህ ላይ ወጭ ላላችሁ ወገኖቻችን ማስገንዘብ የምንፈልገው ሱዳኖች ለማንኛውም አለማቀፋዊ ስምምነቶች በቀላሉ የማይገዙ መሆናቸውን ነው። ይሄን ያልንበት መክኒያት ካርቱም በሚገኘው (UNHCR) መስሪያቤት ውስጥ ሁሉንም እኛ ካላደርግነው አይሆንም ነው የሚሉት ነጮቹ በነጻነት እንዲሰሩ ጭራሽ አይፈቅዱላቸውም። ባጠቃላይ መስርሪያቤቱ ወያኔ በገዛቸው የሱዳን የጸጥታና የስለላ ሰዎች የተሞላ ስለሆነ አንድ ስደተኛ ችግሩን ለማስረዳት ከፍተኛ መከራ ነው የሚያጋጥመው። ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ሱዳን ውስጥ ያለውን የስደተኛውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው (UNHCR) ፕሮቲክሽን ኦፊስ ውስጥ የሚሰሩትን በሙሉ በመዳፉ አስገብቷቸዋል። ምን ችገር አለባቸውሁ ሃገራችሁ ዲሞክራሲ ተትረፍርፏል ለምን ሃገራችሁን አትገቡም እያሉ የሚሰብኩ የወይኔ አባሳደሮች ናቸው። አንዳንድ የሙያው ሰነመግባር የሚያስገድዳቸው ሰራተኞች የመስሪያቤቱ ሕግ በሚደነግገው መሰረት መስራት ሲፈልጉ እነዚህ ሰላይ ናቸው ተብለው በሱዳን መንግስት እንዲባረሩ ይደረጋል። ይታያችሁ እንግዲህ ካርቱም ሱዳን ያለ ስደተኛ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ነው እየተጋፈጠ የሚኖረው።
ሃቁ ግን ኢትዮጵያውይኖች በጠራራ ፀሃይና በለሊት በሱዳን ሰክሪቲዎች ከቤታቸው እየታፈሱ ለወያኔ ባለስልጣናት ተላልፈው ተሰተዋል ያለምንም ከለላ።የሱዳን መንግስት ወደ ሃገሩ የሚገባውን የማንኛውንም ሃገር ዜጋ መቆጣጠር መብት እንዳለው ይታመናል ሆኖም በእኛ ላይ ግን ሰባዊነት የጎደለው
በደል በሱዳን ፖሊሶች ይፈፀምብናል መታወቂያ መቅደድ በያዙት ነግር ሁሉ መደብደብ ፣ መሳደብ ብር መቀማት በሲቶች እህቶቻችን ላይ ይህ ነው የማይባል ለማመን የሚቸግር ግፍ ይፈፀምባቸዋል። ወንዶች እስረኞችን ደግሞ በርሃ በመውሰድ የእርሻ ስራ የሰሯቸዋል። አንዳድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መታወቂያችን ይቀዱብናል በለው በመስጋት ኮፒ ይዘው የተገኙት ዳኛው በሚያሳዝን ሁኔታ ገንዘብ ቀጥቶ ወደሃገራቸው እንዲባረሩ ወስኖባቸዋል ባአንዳንድ አካባቢ ደግሞ ጭራሽ እኛ የስደተኛ መታውቂያ አናውቅም በዚህ አካባቢ ኗሪ መሆናችሁን የሚያስረዳ መታወቂያ ማውጣት አለባችሁ ተብለው 20 የሱዳን ፓውንድ በመክፈል ያወጡ ስደተኞች አሉ።
ባአጠቃላይ የሱዳን መንግስት ስደተኛውን በተመለከተ የተምታታ እና አንድ ወጥ የሆነ አስራር የለውም ይሄ ደግሞ የገቢያ ግርግር ለሊባ ያመቻል እንደተባለው ሆኗል ወያኔ በገንዘቡ ብመመካት የፈለገውን ነገር በስደተኛው ላይ ማድርግ እንዲችል እና የፈለጋቸውን ሰዎች ደግሞ እያነቀ እንዲውስድ በሩን
ከፍቶለታል። ከሁሉም በላይ ለዜጎቹ ክብር የለለው በነሱ ስቃይ ለሚደሰተው ወያኔ አሁን ሱዳን ውስጥ የሚደረገው የስደተኛ ወከባ ስደተኛውን ወደ ሊላ መከራ እየገፋው ነው ይሄውም ወዲ ሊቢያ መሰደድ በስሃራ በርሃ ላይ ተሰቃይቶ መሞት በባህር ላይ ማለቅ ሆኗል የስደተኛው እጣ ፈንታ:: ወያኔ ሱዳን ሃገር ስደተኛ እንዳይኖር የሚፈልግበት የራሱ የሆነ ምክኔያት አለው ይሄውም ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ወያኔ ትንሽ የፖለቲካ እንከን ከሱዳን ጋር ቢገጥመው ሱዳን ሱዳን ውስጥ ያለውን ስደተኛ ያስታጥቃል የሚል የራሱ የሆነ ፍራቻ አለው። አውንታው ግን በጭራሽ ለጎርረቤት
ሃገሮች እንደ ወያኔ ለጋስ የጠየቁትን የሚሰጥ መንግስት ሊመጣ እንደማይችል የታወቀ ነው።
ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር ከሚያዋስነው አካባቢ ለጉልበት ስራ ከሚመጡ የወሎ ፣የጎጃም፣ የጎንደር የአማራ ተወላጆች ሆን ተብሎ እርስ በ እርሳቸው እንዲጨፋጨፉ ስውር ነፈሰ ገዳዮችን በመከከላቸው በማሰማራት ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሔደ እንደሆነ ከ አሁን በፊት ዘ ሀበሻ የህዋ ሰሌዳ በመጠኑ እንደዘገበው ይታወቃል አሁንም በሰፊው ጥናት ተደርጎበትና ታቅዶበት የሚከናወን ስራ ለመሆኑ በመረጃ የተደገፈ ዘገባ እናቀርባለን።
ከላይ የተዘረዘሩት ስደተኛውን የማዋከብ እና በሰላም ሰርቶ እዳይኖር የሚደረገው በወያኔ በጎ ፈቃድ መሆኑን ስደተኛው በሙሉ ጠንቅቆ ያውቀዋል። አሁን ሱዳን ውስጥ የሚደረገው ነገር ልክ ሳውዲ ያ ሁሉ ግፍ ከመፈጸሙ በፊት ሲደረግ የነበረው አይነት ይመስላል መጠኑ የተለያየ ቢሆንም ማለትም ጋዚጦች ስለ ሃበሻ መጥፎ ነገር መጻፋ ባአጠቅላይ የሚታዩ የሚነበቡ የሚደመጡ የዜና አውታሮች ስለዚሁ ጉዳይ በስፋት መቀስቀስ ጀምረዋል። ሱዳኖችም የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ባሽቆለቆለ ቁጥር የወያኔ ተንኮል እና ሴራ ተጨምሮበት ጥላቻቸው በሃበሻ ላይ ጎልቶ እየወጣ ነው። ባአጠቃላይ ሁኔታዎች የሚያመለክቱት የሚመጣው ጊዜ ካለፈው የከፋ እንደሆነ ነው።
ወድ ወገኖቻችን እሮሮዋችን ጣራ አልባ እንዳይሆን ለሚመለከተው ለሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች የስደተኛውን ጉዳይ ሊሚመለከቱ መስሪያ ቤቶች (ድርጅቶች) ባጠቃላይ ይህ ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ይህንን የግፏአን ድምጽ ታሰሙልን ዘንድ እንማጸናለን።
ከ አክብሮት ጋር
ፍቅር ሰላም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!