October 14, 2024
12 mins read

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል።

amhara

የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ ግን ትግራይን ከጦቢያ ሙሉ በሙሉ ለይቶ፣ ራሱን በራሱ ትግራይ ላይ ገድቦ፣ መነሻየ ትግራይ መነሻየም ትግራይ በማለት ትግራይን ከጦቢያ ነጻ ለማውጣት ሕወሐት (ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ) የሚባል ጎጠኛ ድርጅት መሠረተ።  በዚህ ጎጠኛ ድርጅት አማካኝነት ትግራይን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረ በኋላ ደግሞ ተለጣፊወችን በማሰባሰብ ኢሕአዴግ (የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር) የሚባል የቁጩ (የይስሙላ) ድርጅት መሥርቶ ሕብረብሔራዊ ነኝ በማለት ጦቢያን ለመግዛት ሞከረ።

ወያኔ ግን ከመነሻው የትግሬ ጎጠኛ ስለነበረ፣ ጦቢያን ከተቆጣጠረ በኋላ ኢሕአዴግን መሥርቶ ሕብረብሔራዊ ነኝ ቢል ሰሚ አጣ፣ ጆሮ ዳባ ልበስ ተባለ፣ ቅቡልነት ጅባት ሆነበት።   በተለይም ደግሞ የትግሬን ሕዝብ ለጦርነት ያነሳሳውና ከቀረው የጦቢያ ሕዝብ ጋር ደም ያፋሰሰው በትግሬ ጎጠኝነት ስለነበረ፣ የትግሬን ጎጠኝነት እለቃለሁ ቢል የትግሬ ሕዝብ እንደማይለቀው ስለተረዳ፣ የትግሬ ጎጠኝነቱን ሙጥኝ እንዳደረገ፣ የትግሬ ሕዝብ ከሌላው ጦቢያዊ የላቀ ወርቅ ነው እንዳለ፣ ቁልፍ ቁልፍ ስልጣኖችንና ጥቅሞችን ለትግሬወች እንደሰጠ፣ አልትግሬወችን በሁለተኛ ዜጋነት እንደተመለከተ፣ የአልትግሬወችን ተቀባይነት መቸም ሳያገኝ እሞት አፋፍ እስከደረሰባት እስካሁኗ ሰዓት ደረሰ።  መጽሐፉ እንደሚለው ሰይፍ ያነሳ በሰይፍ ይሞታልና፣ ወያኔ በትግሬ ጎጠኝነት ተወለደ በኦሮሞ ጎጠኝነት ሞተ፣ የዘራውንም አጨደ።

የወያኔ ርዕዮተዓለም የተቀረፀባቸው፣ ጎጠኛ አስተሳሰቡ የሰረፀባቸው የወያኔ ግርፎች የሆኑት ዘመነ ካሴና መሰሎቹ ደግሞ ባንድ በኩል አማራነትና ጦቢያዊነት ሊነጣጠሉ ፈጽሞ አይችሉም እያሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አማራንና ጦቢያን ለያይተው፣ ጦቢያን ወደ ጎን ትተው፣ ራሳቸውን በራሳችው አማራ ላይ በመገደብ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ ብለው ተነሱ።  የተነሱበት ዓላማ ደግሞ እነሱ ራሳቸው በግልጽ እንደሚናገሩት አማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል በመቆጣጠር በቂ ኃይል ገንብተው በቀረው የጦቢያ ክፍል ላይ ከኦነግና ከወያኔ ጋር ለመደራደር ነው።

በመጀመርያ ደረጃ ለጥቁር ሕዝብ ነጻነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገው፣ ያድዋው ጀግና ያጼ ምኒሊክ ልጅ የሆነው፣ ነጭን ከመጤፍ የማይቆጥረው፣ በማንነቱ የሚኮራው ትልቁ ያማራ ሕዝብ መዳረሻው ሊሆን የሚገባው አማራም፣ ጦቢያም ሳይሆን አፍሪቃ ከዚያም አልፎ መላው የጥቁር ሕዝብ ነው።  ሙሉ ጥንካሬው አውሬነቱ ብቻ የሆነው፣ ጨለማን ተላብሶ ተከላካይ አልባ ሰላማዊ ሰወችን ከማረድና ከማወራርድ በስተቀር በታሪኩ አንድም ጊዜ እንኳን ፊት ለፊት ተዋግቶም ሆነ ድል አድርጎ የማያውቀው፣ የጦቢያን የመንግስት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ባይቆጣጠርና የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ የሸዋ ፋኖ ብቻ ደምጥማጡን ሊያጠፋው የሚችለው ሙትቻው ኦነግ፣ ኢትዮጵያን በኦሮሙማ መልክ እሰራታለሁ እያለ ሲፎክርና ሲደነፋ፣ ኢትዮጵያን በደምና ባጥንቱ የገነባትንና ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ጠብቆ ያቆያትን፣ በጀግንነቱ ወደር የሌለውን፣ የሕዝብ ቁጥሩ የኦሮሞ ስም ስለተለጠፈበት ብቻ ኦሮሞ ነው የሚባለውን የሞጋሴና የጉዲፈቼ ድምር በብዙ ሚሊዮኖች የሚበልጠውን፣ ትልቁን የአማራን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉት ደግሞ፣ ኢትዮጵያ በሚገባት ደረጃ አማራ፣ አማራ የምትሸት አማራዊ ትሆናለች ከማለት ይልቅ ያማራን ሕዝብ ከኦሮሙማ በማሳነስ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ ሲሉ ከማየት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም።

በሁለተኛ ደረጃ የነ ዘመነ ካሴ መነሻየ አማራ መድረሻየ አማራ የመጨረሻ ዕጣ ከነ መለስ ዜናዊ መነሻየ ትግራይ መድረሻየ ትግራይ የመጨረሻ ዕጣ የተለየ ሊሆን አይችልም። ወያኔ መነሻየ ትግራይ መድረሻየም ትግራይ በማለት ራሱን በራሱ ትግራይ ላይ ገድቦ ጦቢያውያንን ርስበርስ ካጨፋጨፈ በኋላ በለስ ሲቀናው ኢሕአዴግን መሥረቶ ሕብረብሔራዊ ነኝ በማለት ጦቢያን ላስተዳድር ሲል ማንም እንዳልተቀበለው፣ መነሻውን አማራ መድረሻውንም አማራ በማድረግ ራሱን በራሱ አማራ ላይ የገደበ የነ ዘመነ ካሴ ትግል ደግሞ በለስ ቀንቶት ያማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል ቢቆጣጠርና ከወያኔና ከኦነግ ጋር በመቀናጀት ዳግማዊ ኢሕአዴግ መሥርቸ በሕብረብሔራዊነት ስም ጦቢያን ላስተዳድር ቢል ማንም አይቀበለውም።

በሶስተኛ ደረጃ ያማራ ሕዝብ ወያኔና ኦነግን በተመለከተ ያለው ምርጫ ወይ እነሱን ማጥፋት አለያም በነሱ መጥፋት እንጅ መደራደር አይደለም።  ወያኔና ኦነግ አማራን አማራ በመሆኑ ብቻ የሚጠሉ ያማራ ሕዝብ የማንነት ጠላቶች ስለሆኑ፣ መቸም የማይለወጥ ቋሚ ዓላማቸውና ዘላለማዊ ምኞታቸው አማራን ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ጦቢያን አማራአልባ ማድረግ ነው።  በተለይም ደግሞ ወያኔና ኦነግ ለዘመናት በነገሰባቸው የከረረ የዝቅተኝነት ስሜት ሳቢያ አማራ ካልሞተ ሕይወት ያላቸው ስለማይመስላቸው፣ ሰጠቶ በመቀበል መርሕ መሠረት ካማራ ሕዝብ ጋር ተደራድረው፣ ተከባብረው ለመኖር ማስብ ቀርቶ አያልሙትም።  ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ከወያኔና ከኦነግ ጋር እደረደራለሁ ቢል፣ ትርፉ ወያኔና ኦነግ ይበልጥ ተጠናክረው የሕልውናውን ክስመት ይበልጥ እንዲያፋጥኑት ጊዜ መስጠት ብቻ ነው።  መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ የሚለው የነ ዘመነ ካሴ መፈክር አማራን ከጥፋት የሚቤዝ (የሚያድን) ቤዛማራ መፈክር ሳይሆን፣ ወያኔና ኦነግ አማራን እንዲያጠፉ የሚያመቻች ፀራማራ መፈክር ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው።

በተቃራኒው ግን በእስክንድር ነጋ የሚመራ፣ መነሻየ አማራ መድረሻየ ጦቢያ ብሎ የተነሳ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል አማራ ያልሆኑ ጦቢያውያንን በዙርያው በማሰበሰብ የትግሉን ሜዳ አማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል ብቻ ሳይሆን መላዋን ጦቢያን የሚያጠቃልል ሰፊ ሜዳ አድርጎ ፣ በመላዋ ጦቢያ ላይ በሰፊው የተሰራጩትን እልፍ አእላፍ አማሮች በስፋት አሳትፎ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ውድቀቱን በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያቃርበው ሳይታለም የተፈታ ነው።  ያማራ ሕዝብና የጦቢያ ዘላለማዊ ጠላቶች የሆኑት ወያኔወችና ኦነጎች በምዕራባውያን አጋሮቻቸው እርዳታ መረጃ ቲቪን፣ ሮሐ ቲቪን፣ ግዮን ቲቪን፣ ግርማ ካሳን፣ ዘመድኩን በቀለንና መሰሎቻቸውን ከጎናቸው አሰልፈው በእስክንድር ነጋ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱትም በዚሁ ምክኒያት ነው።

 

መስፍን አረጋ

\

3 Comments

  1. Liji Mesfin, the way you drew your conclusion sounds politically divisive , cynical, and of course extremely unconstructive !!! I really do not understand how people like you can be valuable assets / factors in the very huge and serious struggle being carried out by Fano and all other Ethiopians who share the same vision and objective as far as the making of democracy a reality is concerned!!!
    I am sorry to say but I have to say that paying a huge sacrifice for a long time like Eskindir does not and should not be a guarantee to be immune from criticism !!! Never and never!! Because it is not good for Eskindir himself leave alone the people who are languishing under a very horrible political system!!
    Let’s try hard not to be victims of emotion-driven supporters of or that person of politics. Instead let’s try hard to have a balanced and constructive thought !! Let’s not be victims of thing small but big , and talk about issues not just people as such !!!
    Have a good one buddy!!!

  2. I don’t see any difference between Zemene and Eskinder. But, Eskinder came to Fano late and wanted to take over the leadership. That is when Zemene’s group pretended there is ideological difference as where their anticipated destination. Otherwise both groups talk about Ethiopia the same way. They also agree as to how they get to the finish line. If Eskinder call for a repeat of election in a wider leadership meeting all will be well.

  3. “ያማራ ሕዝብ ወያኔና ኦነግን በተመለከተ ያለው ምርጫ ወይ እነሱን ማጥፋት አለያም በነሱ መጥፋት እንጅ መደራደር አይደለም።”
    Hundred percent agree with this statement. The rest is Gunch Alfa kirkir. Mennesha yemibal negher yellem. Mennesha binor tiglu balasfeleghe nebber. Amhara mulu bemullu be highe mengistu yeteneqele hizb new. Mennesha zero medresha meto bibal yishalal. Yeteyazew hair splitting is just a cover for power struggle. While that is natural, we should not use it to cover GoTegninet. The struggle needs both Iskinder and Zemmene. In fact, shat we need is million more Iskinders and million more Zemenes. The slogans have no political, or philosophical value. They are just excuses to create a semblance of an ideological difference.
    It should be stark clear to someone of your caliber.
    No ideological difference among Fanno. They are out to dismantle ethnic-hate federalism in order to guarantee the survival of Amhara and pave the road towards the establishment of an Ethiopia where all are equal citizens.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

89999hjkhhk
Previous Story

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

Diaspora fight
Next Story

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop

Don't Miss

Eskinder

የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ለፋኖ የህልዉና ትግል መቅሰፍት ነዉ!!

አንተነህ ሽፈራዉ (ኢ/ር) October 15, 2024 መርህ አልባዉ እክንድር ነጋ
7

ናዝሬት ሞጆ መንገድ በፋኖ ተያዘ 7 ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ተሸኙ አሁን የደረሱን የድል መረጃዎች

ናዝሬት ሞጆ መንገድ በፋኖ ተያዘ 7 ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ተሸኙ