August 3, 2024
9 mins read

ፓትርያሪክና ጳጳሳት አሜሪካና አውሮጳ እየነጎዱ የሚዝናኑበትን ገንዘብ የሚያገኙት ተየት ነው?

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

 

በዚህ የሕዝብ ደም እንደ ጅረት በሚፈስበት ወቅት ሳይቀር ፓትርያሪኩን ጨምሮ አያሌ ጳጳሳት በሕክምናና ሌላም ምክንያት እያሳበቡ አሜሪካና አውሮጳ በመንፈላሰስ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሜሪካና አውሮጳ ሄዶ ለመታከም ውድ የአውሮፕላን ቲኬት መግዛት፣ መቆያ ሆቴል መኮናተር፣ ከውዲያ ወዲህ መንቀሳቀሻ ታክሲ መያዝ፣ ምግብና ለህክምናው አገልግሎት መክፈልን ይጠይቃል፡፡ የአሜሪካና የአውሮጳ የህክምና አገልግሎት ደሞ በአስር ሺህዎች፣ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግ ተሆነ ደሞ የቅጠል ያህል ዋጋ በሌለው የኢትዮጵያ ብር ሳይሆን በአሜሪካ ገንዘብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ማፈሰስ ያስፈልጋል፡፡ ይህ የአንድ ፓትርያሪክ ወይም ጳጳስ ቁርጠት ለማሳከም የሚወጣው ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አገልግሎት ቢውል በመቶዎች የሚቆጠሩ ክሊኒኮች ይሰራል፡፡

በባህላችን የአበው ተረት “በሽታውን የደበቀ መድሀኒት የለውም” ይላል፡፡ በዘመናዊ ሳንይስም የእግር ቁስሉን በማከም ፋንታ ሸፋፍኖ የደበቀ እግሩን ተቆረጠ ወይም ነፍሱን ተቀጠፈ ይባላል፡፡ ይህ አድግ የተባለው እርኩስ መንፈስ በኢትዮጵያ አናት ላይ ተወደቀባት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መንበር በልማት ካድሬነታቸውና ታማኝነታቸው  ያስቀመጧቸው ፓትርያሪኮችና ጳጳሳት የቤተክርስትያኗን የማይሽሩ ቡግንጆች ሆነዋል፡፡ አብዛኛው ሕዝብ ግን እነዚህን የቤተክርስትያኗን በሽታዎች ወይም መግል የቋጠሩ ቡግንጆች “የቤተክርስትያኗን ክብር ለመጠበቅ” በሚል ክርስቶስን በሚያስከፋ የአስመሳይነት ፋሻ ሸፋፍኖ እየደበቀ ቤተክርስትያኗንና አገሪቱን ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል፡፡

ፓትርያርኮችና ጳጳሳት መነኮሳት ስለሆኑና እንዲያውም ከመነኩሳትም “ተመርጠው” በቤተ ክርስትያን መሪነት የተቀመጡ እንደመሆናቸው መጠን በቅዱሳን መጻሕፍት ከተወለዱት በመጻሕፍተ መነኮሳት ትእዛዝ መገዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ከመጻሕፍተ መነኮሳት አንዱ የሆነው አረጋዊ መንፈሳዊ ገጽ ፻፳፩ ላይ “ከእለት ምግብ በቀር ብዙ ገንዘብ የሚያኖር መነኩሴ የሰይጣንን ፈቀዳ የሚፈጥም ነው …ትጋቱ አሳቡ ተዐቅቦው ስለ ሆዱ ነው ይላል፡፡ [1] ሌላው መጽሐፈ መነኮሳት ማር ይስሐቅ መጻህፍትን  መመልከት ውደድ፤ ከንዑሳን ሕጣውእ ተከልከል” ይላል፡፡ ንዑሳን ሕጣውእንም “ማየት፣ መስማት፣ ያለመጠን መብላትና መጠጣት ናቸው” ይላል፡፡[2]  ማር ይስሐቅ ማስተማሩን ሲቀጥልም “የእንጨት ብዛት እሳቱን እንደሚያበዛው የምግብ ብዛትም ዝሙትን ያበዛል፡፡ በልቼ ጠጥቼ፤ አይቼ ሰምቼ፣ ንጽሕናየን ጠብቄ ከሴት ርቄ መኖር ይቻላል አትበል” ይላል፡፡ [3]ማር ይስሐቅ መነኮሳትን ስለገንዘብ ማሳደድ ሲያስጠነቅቅም “ድሀ ትሆን ዘንድ ውደድ፣ ተርታ ልብስ መልበስን ውደድ” ይላል፡፡ [4] ይኸንን በመከተል እንደ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን ያሉ እህት አባያተ ክርስትያናት ፓትርያሪክና ጳጳሳትት የእለት ጉርሳቸውን ይሰጣቸዋል እንጅ ደመወዝ የሚባል ነገር የላቸውም፡፡

የዘመኑ የተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያሪክና ጳጳሳት ግን የቅዱሱን መጽሐፍና የመጻሕፍተ መነኮሳትን ትእዛዛት እንደ ቀበኛ ላም በመብላት ራሳቸውን በብዙ አስር ሺሆች የሚቆጠር ደመዎዝ ተከፋዮች አድርገዋል፡፡ ብዙዎቹም የቤተክርትያኗን ገንዘብ በዚህም በዚያም አምታተው እንደ ጭልፊት እየሞጨለፉ በግል ሐብት ደልበዋል፡፡ በሕመም እያሳበቡ አሜሪካና አውሮጳ እየነጎዱ ሲዝናኑ ይታያል፡፡ ለመሆኑ ይህ ለመስማት እንኳን የሚዘገንን ደመወዛቸውን፣ ያደለቡት ንብረታቸውን፣ አውሮጳና አሜሪካ የሚንፈላሰሱበትን ገንዘብ ተየት ይመጣል?

99989797970770ቤተክርስቲያኗን የሚወዱ ብዙ የእስልምና ተከታይ ኢትዮጵያውያን ሳይቀር ምዕመናን ለዚህች ጥንታዊት ቤተክርስትያን ተጉረሯቸው እየሞለቀቁ ግብር ያስገባሉ፤ መጽሐፉ ተገንዘብ እራቁ ያላቸው ፓትርያሪክና ጳጳስ በደመወዝ ስም እያፈሱ ይልፋሉ፡፡ እናት ልጇ በጠና  ሲታመምባት እንዲድን፣ ሲታሰርባት እንዲፈታ፣ ሲረሸንባት ነፉሱን እንዲምረው ስለት ታስገባለች፤ ተአሳሪዎችና ተነፍሰ ገዳዮች ጉያ የማይጠፉት ፓትርያሪክና ጳጳሳት በውሎ አበል ስም ላፍ ያደርጉና ፎቅ ይሰሩበታል፡፡  ለማኝ በቁስሉ እየለመነ ተሚያገኘው ሳንቲም አስራት ይከፍላል፤ ፓትርያሪካና ጳጳሳት ግን ቁስሉ ለማድረቅ ለማኙን ጸበል ተጠመቅ ይሉና እነሱ አሜሪካና አውሮጳ የቁርጠት መታከሚያ ያደርጉታል፡፡

በይህ አድግ ዘመን መንኩሰ ሞተ ወደ መንኩሰ ናጠጠ ተሸጋግሯል፡፡ ምንኩስና ተምነና ባህታዊ ድልድይነት ወደ ቅንጦትና ቅልጥ ወዳለ ከተማ መሸጋገሪያነት ተቀይሯል፡፡ ቤተክርስትያኗም ሆነ አገሪቱ እንዲድኑ በሽታቸውንና ቁስላቸውን መሸፋፈን ትተን ማከም ይኖርብናል፡፡ ሕክምናው ደግሞ የእናቶችን መቀነት እያራቆቱ በሐብት የሚደልቡትን፣ የቤተክርስትያኗን ጸጋ እያራቆቱ የፕትርክናና  ጵጵስና ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ምዕመናን በባሩድና በድሮን ተሚጨፈጭፉ አረመኔዎች የሚወባሩትን፣ የቁሰልኛ ለማኞችን አስራት እየሞጨለፉ በሕክምና እያሳበቡ አሜሪካና አውሮጳ የሚሞላቀቁትን ፓትርያሪክና ጳጳሳት ተቤተክርስትያኗ መንበር ዥልጦ ተማውረድ ይጀምራል፡፡  እጅን አጣጥፎ ወይም ተቤት ውስጥ እያሙና እግዚአብሔር ይቅጣቸው እያሉ መልገምን ሕዝብ ማቆም ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔር “እርዱኝ እረዳለሁ!” እንጅ ተጎልታችሁ መና ጠብቁ እንዳለለ ልብ ይሏል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ዋቢ፡-መጻሕፍተ መነኮሳት 1928 ዓ.ም ብርሃንና ሰላም እትም

  1. አረጋዊ መንፈሳዊ ገጽ ፻፳፩
  2. ማር ይስሐቅ ገጽ ፲
  3. ማር ይስሐቅ ገጽ ፶፯
  4. ማር ይስሐቅ ገጽ ፲፬

 

ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ..

1 Comment

  1. የኛ አገር ሰው ከሰው አይወርድም ቀሲስ በላይ ትንሽ ፮ሚሊዮን ሀያሽህ ዶላር አጭበረበሩ ብሎ ያ ሁሉ ጫጫታ ምን ይሉታል አቡነ ሳይሮስስ እሳቸውን የመሰለ ልጅ ስላላቸው እንኳን ደስ አሎት ይባላል እንጅ ምን ይባላል?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Fano
Previous Story

ጎንደር ድል በድል ሆነ ሰራዊቱ ለቆ መውጣት ጀመረ

192805
Next Story

ዘመነ ካሴ ‘’እኔ የምመራው ሐይል ከማንም የመንግስት አካል ጋር ድርድር አልጀመረም’’ አለ ‘’የምንታገለው ለስልጣን እንጂ ለምንኩስና አይደለም” አርበኛ ዘመነ ካሴ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop