August 6, 2023
3 mins read

የትግራይን ሕዝብ ጁንታ ብለህ ከጨፈጨፍክ በኋላ አሁን ደግሞ ጃውሳ ብለህ በአማራ ሕዝብ ላይ ሰይፍህን መዘዝክ

F3Ap9heWoAEU9uw 1
ዳንኤል ክስረት በሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ ማወጅህን እግዚአብሔር ይይልህ!!
“ውሻ በበላበት ይጮኻል”
ማለት እንደአንተ ነው።
የዕለቱ የጃውሳው ዳንኤል ወሬ 
ዛሬ በአማራ ክልል የተፈጠረው ቀውስ የሦስት አካላት ድምር ውጤት ነው።
1.ግብ የሌለው ጃውሳ፣
2.አቋምና አቅም የሌለው አመራር፣
3.ባንዳ መግዛት የለመደ የውጭ እጅ።
ከሕወሓት ጋር የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጓል። የሁሉም ክልል አመራሮች በጥናቱ ላይ ተወያይተዋል። ዝርዝር ዕቅድ ነበረው። ይህ የአሁኑ ሁኔታ ሊከሠት እንደሚችል ጥናቱ በግልጽ አመልክቶ ነበር። አብዛኛው የክልሉ አመራር ግን በተቃራኒው ነበር የሚሠራው። የአማራ ክልል ሕዝብ በተደጋጋሚ በዕንባ ጭምር ተናግሯል። በተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ተነድቶ፣ ከጦርነት የተረፈና የተዘረፈ መሣሪያ አንግቶ፣ እየመጣ ያለው ጃውሳ ክልሉን እንደሚያቀውሰው ሕዝቡ ቀድሞ ተናግሮ ነበር። ሰሚ ግን አላገኘም።
የጎጃምን የፖሊስ ኮሌጅ በመዝረፍ፣የጎንደርን የንግድ ሱቆች በማራቆት፣ የሚጓጓዝ ማዳበሪያን ነጥቆ በመሸጥ፣ የመንግሥት የአገልግሎት ተቋማትን በማውደም፣ የእርሻ ጊዜን በማስተጓጎል፣ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በማስተጓጎል፣ ለሕዝብ የሚደረግ ትግል ካለ የጃውሳ ትግል ብቻ ነው። ከእሳቱ ርቀው እሳት በሚያነዱ አካላት የሚመራ ትግል የጃውሳ ትግል ነው። የክልሉ ሕዝብ ገና ካሁኑ የአጋሚዶው የዝርፊያ ጥማት ማርኪያ ሆኗል።
መፍትሔው ምርቱን ከገለባው መለየት፤ ከዚያም ምርቱን ወደ ጎተራ ገለባውን ለእሳት መስጠት ነው። ሀገሩንና ሕዝቡን የሚወድ ራሱን ከጃውሳው ይለይ። የአማራ ክልል ሕዝብ ፈተናዎች አሉበት። የፈተናዎቹን ምንጭ ይረዳል። ፈተናዎቹን በሠለጠነ መንገድ እንዴት እንደሚወጣቸው ያውቃል። ጃውሳ የሚሸከምበት ትከሻ ግን የለውም። “አይ በላንዶ” ስንት ክልል ይዘፈን?!
ጃውሳ፦ ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ ነጣቂ፣ ቀማኛ፣ በጎደጎደ ምድር፣ በጨፈቀ ዱር እያደባ መንገድ ዐላፊውን እየደበደበ የሚቀማ ወንበዴ።

ዘየኔታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop