ለአንዋር መስጂድ ሰዎች ተገደሉ!!! በጎጃም ደብረ ኤልያስ ገዳም ውስጥ ሰዎች መቱ ፎቶ እዩ!!!
ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)
እናንት ናችሁ እኳ …እናንተ! ፈፃሚ የታሪክን ተልኳ …እናንተ!!!የኢትዮጵያ ልጆች መጡ እንደገና!አንድ ለእናቱን እርዱትማ! ትግላችን የመኖርና ያለመኖር የህልውና በህይወት የመኖር መብቶች ትግል ነው፡፡ እናንተ የፀረ- አንባገነኖች ትግል የህዝብ መከታ!!! እናንተ የዴሞክራሲ፣ የነጻነትና እኩልነት አሌንታ!!! እናንተን አምነን እሱን አመንን!!! እናንተ የኢትዮጵያ ልጆች እናታችሁ ትጣራለች! ትጣራለች፡፡ የአገራችን ሰው እንደከብት ታረደ፣ በቁሙ ተቃጠለ፣ ተሰቀለ፣ የኮነሬል አብይ በዘር ከፋፍለህ ግዛ አገዛዝ ለአንዴም ለሁሌም ይገረሰሳል!!! ለምሁራን በዘር ፖለቲካ ከአገር እንዳስገቡ እንዲያወጡ ለማንም አይጠቅምምና አደራ እንላለን!!! (Bombard the Headquarter) ስልጣን ከእውቀት ጋር ለአዲሱ የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣት ፖለቲከኞች የሃገራችንን ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ብቃት ያላችሁ አዲስ ትውልድ ስልጣኑን መጨበጥ ታሪክ የጣለባችሁ አደራ ነው፡፡ አንባገነኑ የኮነሬል አብይ መንግሥት በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች ከ111(መቶ አስራአንደ) ሽህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታውቆል፡፡ ግማሽ ሚሊዮኝ ህዝብ ተፈናቅሎል፡፡ ገና የኦነሬል አብይ ቤተመንግሥትና የሽመልስ አብዲሳ ቤተመንግሥት ሲገነባ የሚሊዮኖች ቤት ፈርሶ ተፈናቃዬች ቁጥር የትየለሌ ይሆናል፡፡ ዛሬውኑ ቆርጠን ለትግል በመነሳት ይሄን ግፍ ማስቆም ታሪካዊ አደራ አለብን፡፡
የቪዝን ኢትዮጵያ ሃገር ወዳድ ዜጎች ዳግም በመሰባሰብ ታሪካዊ ሃላፊነታችሁን ተወጡ፡፡
እስክንድር ነጋ ዳግማዊው ጥቁር ሰውበአማራዳግማዊ ሚኒሊክ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ በአድዋ ጦርነት ድል በመንሳታቸው ‹‹ሚኒሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ፣ ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ›› ተብሎ ነበር፡፡ ዛሬም በአማራ ህዝብ ላይ ለተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ (ጀኖሳይድ) የኦነግ/ኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ ፋሽስት ቡድን አሻፈረኝ አልገዛም በማለት ‹‹ድል ለዴሞክራሲ›› የአማራ ህልውና፣ ለኢትዮጵያ ህልውና ብሎ በመነሳት የዴሞክራሲን አብሪ ጥይት ለኮሰው!!! ጥቁር ሰው በሠላማዊ ትግል ፈር ቀዳጅ በመሆን ከአስር ጊዜ በላይ በወያኔና በብልፅግና እስር ቤቶች ወህኒ ቤቶች የታሠረ ፣ በህይወት አላኖር ባሉት ፋሽስቶች ግፍ የተነሳ ዱር ቤቴ አለ፣ ፋኖውም፣ ሚሊሻውም፣ ፓሊሱም፣ ልዩ ኃይሉም፣ መከላከያውም በደስታ ተቀላቀለው፡፡ የአማራ ህዝባዊ ግንባር ለኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ ትሪ አስተላለፈ፣ ለአፋር፣ ለትግራይ፣ ለኦሮሞ፣ ጋምቤላ፣ ሃራሪ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ ወዘተ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ህዝባዊ ጥሪ አቅርቦል፡፡ የአማራ ህዝባዊ ግንባር ተጠያቂነትን በማንገስ በኢትዮጵያ የፍርድ ቀን ይመጣል!!! አንድ ቀን ይህን የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል በህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዘመን የተቀረጸው ህገ- መንግሥት በኦህዴድ ብልጽግናም የቀጠለውን ህገ-አራዊት በኢትዮጵያ ህዝብ ስምምነት ውስኔ ይሰጠዋል፡፡
የአማራ ህዝብ ስቃይና እንደ ከብት መታረድ የሌሎች ክልሎች ህዝብ ዝምታ የታሪክ ጠባሳ አኑሮል፣ የአማራ ህዝብ የዘር ፍጅትና እልቂት ለናሙና ታህል የቀረበች ጥናት ላይ ተቆንጥራ የወጣችውን እናስተውል፡፡ በዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦነግ ሸኔ/ኦህዴድ ብልፅግና የተገደሉ አማራዎች ከሰባት ሽህ እስከ አስር ሽህ በላይ አሻቅቦል፣ የቆሰሉ ሰዎች በሽህ ይቆጠራሉ፣ ከሠላሳ አስከ ሃምሳ ሽህ አማራዎች በኦህዴድ ብልጽግና እስር ቤቶች በአሰቃቂ ግርፋትና ስቃይ (ቶርቸር) ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከአማራ የተዘረፉ የቁም ከብቶች ሁለት መቶ ሽህ እስከ አራት መቶ ሽህ ይገመታል፣ የተቃጠሉ ቤቶች ብዙ ሽህ ይቆጠራል፣ 68 (ስልሳ ስምንት) ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ 46 (አርባ ስድስት) መስጊዶች ተቃጥለዋል፣ 84 (ሰማንያ አራት) ወፍጮ ቤቶች 163 (መቶ ስልሳ ሦስት) ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፣ ብዙ መኪኖች ተቃጥለዋል፣ 756 (ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት) ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል የትምህርት ማስረጃዎች ተቃጥለዋል፡፡325 (ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሽህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 5227(አምስት ሽህ ሁለት መቶ ሃያ ሰባት) አስተማሪዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል፡፡ በወለጋ 500 (አምስት መቶ) ሽህ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች 647 ንፁሃን አማሮችን መግደላቸው ተገልፆል፡፡ 1252 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት) የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 85 (ሰማንያ አምስት) ሽህ ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 26.7 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዩን ብር የሚገመት ንብረት ወድሞል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት በጦርነቱ 11.6 (አስራአንድ ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፆል፡፡ ከዚህ ውስጥ 9.3 (ዘጠኝ ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ በሰሜኑ ጦርነት በእርሻ ዘርፍ እንዳያመርቱ የተገደዱ ገበሬዎች ናቸው፡፡ 2.3 (ሁለት ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆኑ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ የነፍስ አድን ድጋፍ ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ ወዘተ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ የአማራ ህዝብ በተለይ በወለጋ ኦሮሚያና በመተከል ቤኒሻንጉል ክልሎች ያሉት ህዝብ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ንብረታቸው ተዘርፎል ምንም የቀረን ነገር የለምና ከነዚህ የሰዎች እርድ ቄራዎቸ ስቃይና መከራ ተላቀን ወደፈለግንበት በሰላም እንድንሄድ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምፅ ተነስቶ ነፍሳችንን እንዲያድን በህፃናቶች፣ በእናቶችና በአረጋዊያኑ ስም እንጠይቃለን፡፡ በቅርቡ የአማራ ክልል ግማሽ ትሪሊዮን ብር የሚገመት ውድመት በአማራ ህዝብ ላይ መፈጸሙን በጥናት አረጋግጦል፡፡
ከ2010 እስከ 2015 ዓ/ም የኮነሬል አብይ የብልጽግና መንግሥት የግፍ አገዛዝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ሞተዋል፣መቶ ሽዎች የአካል ጉዳተኘች ሆነዋል፣ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ብዙ ሽዎች ሴቶችና እናቶች ተደፍረዋል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው አምስት አመታት ተጠያቂነት እንዲመጣ፤ ገለልተኛ የስብዓዊ መብቶች አጣሪ ኮሚሽን ገብተው የተፈፀመውን የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀልና የስብዓዊ መብቶች ጥስቶችን አጣርተው ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ የሚታገል የኢትዮጵያዊ ኃይል በየክልሎቹ ማደራጀት፣ ወቅታዊ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ናቸው እንላለን፡፡
ትግላችን ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው›› በሚለው የህገመንግሥቱ አንቀጽ በህይወት የመኖር መብታችንን መጀመሪያ ለማስከበር እንታገላለን፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት ያላከበረ፣ ሰው የሚታረድበት፣ ሴቶች የሚደፈሩበት፣ ሰዎች በገፍ የሚፈናቀሉበት፣ ከክልላችን ውጡ የነገሰበት በኦነግ/ኦህዴድ ስውር የፖለቲካ ሴራ የሚመራ በመሆኑ ዜጎች ትጥቃቸውን ሳይፈቱ በህይወት የመኖር መብታቸውን ማስከበር ያስፈልጋል፡፡ አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት የኦሮሙማ የመሥፋፋት አባዜና ግጭት በሁሉም ክልሎች ላይ እየተፈጸመ በመሆኑ በኦሮሙማ ላይ ‹‹የፀረ-መሥፋፋት የክልሎች ግንባር›› (United Front against Oromuma Expanssion) መመሥረት ያስፈልጋል፡፡
አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት ‹‹የሃገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔር ብሔረሰቦች እና የህዝቦችን ሚዛናዊ ተዋዕዖ ያካተተ ይሆናል) የሚለው አንቀፅ ሰውየው ኮነሬል አብይ የጦርኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ ገብርዬው ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጆላ ገላልቻ ኤታማዦር ሹም በኦነግና ኦነግ ሸኔ ሠራዊት ከላይ እስከታች በኦሮሙማ የተሸሙ ‹‹ከላይ ሰውዬው፣ ከታች ገብርዬው፣መኃል ያለው ንሳ ዝምብዬው!!!›› በኦሮሙማ ዘር ላይ ያማከለ መከላከያ ሠራዊት በመሆኑ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ ይልሆነ በበኦነግ ኦሮሙማና በኦነግ ሸኔ ፖለቲካ የተጠመቀ አራጅ ቡድን አሸባሪነት የተፈረጀ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የክልሎች ልዩ ኃይል ትጥቅ ያለመፍታት ግንባር መፍጠርና መተባበር ግድ ይላቸዋል የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ዜጎች መከላከያ ሠራዊትበጋራ በእኩልነት መመሥረት፡፡ በዘር ላይ የተመሠረተ የክልሎች ሠራዊት በጋራ በስምምነት በማፍረስ ኢትዮጵያ ዜጎች መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ ሳይንስና ክህሎት በሜሪት መገንባት፡፡
ሠላማዊ ህዝባዊ እንቢተኛነት፤የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እናየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ሠላማዊ ህዝባዊ የእንቢተኛነት ትግል እንዲቀጣጠል በቀጣይ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ እና የሌሊት የኡኡታ ጩህት፣ የቆርቆሮ ማንኮኮትና የፊሽካና የጡሩንባ ጩህት በማስተጋባት የውጪ አገራት ዲፕሎማቶችና አንባሳደሮች በብልፅግናው መንግሥት ጸረ-ዴሞክራሲና ፀረ ህገመንግሥት በኃይማኖት ላይ ጣልቃ በመግባት የሚያካሂደውን ኢስብዓዊ ድርጊት እንዲያስቆሙ ለሁሉም ማሳወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የኃይማኖት እምነት ተከታዬች ግንባር ይመስረት!!!(Ethiopian Religious Organization United Front)
የፍርድ ቀን ደርሶል!!! የአብይ አህመድ የብልፅግና መንግሥት ሦስቱ ምሶሶዎች ተራ በተራ ፈራረሱ፣ተናዱ (Things fall apart) አንዱ ምሶሶ በኢትዮጵያ ሙስሊሞችና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ ምእመናን ሠላማዊ ህዝባዊ እንቢተኛነት ትግል እንዲያሸንፍ የኢትዮጵያ የኃይማኖቶች እምነት የጋራ ግንባር መመስረት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡
ስማኝ ያገሬ ልጅ በአንድ ላይ ተነሣ፣ ድር ከተባበረ ይጥላል አንበሣ!!!
የአብይ አህመድ የብልፅግና መንግሥት፣የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኮሚሽነር ስብዓዊ መብቶች የጋራ ምርመራ 156 ገፅ ሪፖርት ”Report of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC)/Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights (OHCHR) Joint Investigation into Alleged Violations of International Human Rights, Humanitarian and Refugee Law Committed by all Parties to the Conflict in the Tigray Region of the Federal Democratic Republic of Ethiopia”OHCHR-EHRC-Tigray-Report.pdfያንቡ፡፡
በድጋሚ በሌላ ገለልተኛ የፍትህ አካል እንዲመረመር በተባበሩት መንግሥታት የተሸመው ገለልተኛ የአለም አቀፍ ኮሚሽን የስብዓዊ መብት በትግራይ፣ በአማራና አፋር ክልሎች ለተፈፀመ የጦር ወንጀል፣ የዘር ፍጅትና የስብዓዊ መብቶች ጥሰት በጀት እንዳይፀድቅና እንዳይቀጥል የኢትዮጵያ መንግሥት የኮነሬል አብይ አህመድ አስተዳደር ደጋግማ ለማክሸፍ እየሞከረ ነበር፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ምክር ቤት ለተቌቌመው የአለም አቀፍ ኮሚሽን የስብዓዊ መብት ኮሚሽን ስብሰባ በ71(ሰባአንድ) ድጋፍ፣ በ32(ሠላሳ ሁለት) ተቃውሞና፣ በ50 (ሃምሳ) ድምፀ ተሃቅቦ፣ በጀቱ እንደጸደቀ ይታወቃል፡፡ኢትዮጵየ መንግሥት በአብይ አህምድ አገዛዝ ዘመን በግፍ በጦርነት ለረገፉ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ህዝብ ተጠያቂነት፣ ለተፈናቀሉት ብዙ ሚሊዮን ህዝቦች፣ ለወደመው መሠረተ-ልማቶች ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ተጠያቂ ናቸው፡፡ የብልፅግና መንግሥትና የህወሓት ሹማምንቶች በጦርነቱ ለተፈጸሙ የስብዓዊ መብቶች ጥሰትና ወንጀሎችን በሽግግር የፍትህ ሥርዓት መልስ እንደሚሰጡ ቢጠይቁም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ አብይና ደብረፂዮን ወንጀለኞቹ ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲታለፍ የአሜሪካንን መንግሥት በመማፀን ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የግፉ ተቌዳሽ የነበሩ የትግራይ፣ የአማራና አፋር ህዝብ የብልፅግና መንግሥትና የህወሓት ሹማምንቶች ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቅና መታገል ለሞቱት ወጣቶች፣ ለተደፈሩት እናቶች፣ ለተፈናቀሉት ሰዎች፣ ለተዘረፉት ንብረትና ኃብት ተጠያቂ እንዲሆኑ መታገል የጊዜው አንገብጋቢ ህዝባዊ ጥያቄ ነው፡፡ የብልፅግና መንግሥትና የህወሓት ሹማምንቶች ለፍርድ ይቅረቡ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሠላማችንን የምናገኘው የብልፅግና መንግሥትና የህወሓት ሹማምንቶች ሲነቀሉ ብቻ ነው፡፡UN rights forum picks ex-ICC prosecutor to lead Ethiopia ድረ-ገጽ ያንቡ፡፡
የአብይ አህመድ ደም የጠማው መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ በሙስሌም ወንድሞቻችን ላይ በአንዋር መስጅድ ሌላ የግድያ ወንጀል መስራት ያሳዝናል፡፡ የሃይሞኖት ጣልቃ ገብነት ያብቃ!!! በህብረት እንነሳ!!!
‹‹በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 21.2 (ሃያ አንድ ነጥብ ሁለት) ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ፣ ከእነዚህ ውስጥ 16 (አስራስድስት ሚሊዮን ህዝብ) በድርቅ የተጎዱ፣ እንዲሁም 4.6 (አራት ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን የተፈናቀሉ መሆናቸው ተገልፆል፡፡ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች አልቅዋል፣ በመቶ ሽህ ወጣቶች አካላቸው ጎሎል፣ እንዲሁም አንድ ትሪለየን አምስት መቶ ቢሊዮን ብር የሚገመት የመሠረተ-ልማት ውድመት በሁለቱ ዓመት ጦርነት ተመዝግቦል፡፡ በዚህም የተነሳ አራት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያየ መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ፣ አስራስድስት ሚሊዮን ዜጎቻችን በድርቅና ርሃብ ቸነፈር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ በመላ ኢትዮጵያ ለደረሰው ስብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶች ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው የፖለቲካ ድርጅቶችና ሹማምንቶች ተጠያቂ እስካልሆኑ ድረስ ፍትህና ርትህ በኢትዮጵያ ምድር አይኖረውም፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዘመን የተቀረጸው ህገ- መንግሥት ምን ይላል፡- ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነጻነት መብት አለው፡፡››አንቀጽ 14 …….‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› አንቀጽ 15……‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፡፡›› አንቀጽ 16 ተፈፃሚ ለማድረግ ተጠያቂነት መቅደም አለበት እንላለን፡፡ መንግሥት ህግ ማስከበር ባለመቻሉ ምክንያት ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠላም አስከባሪ ኃይል እንዲገባ የሚጠየቀው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙ የዘር ፍጅት፣ የጦርነት ወንጀልና የስብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂዎቹን ለህዝብ ማሳወቅና ለፍርድ ማቅረብ የመጪው መንግሥት ተቀዳሚ ሥራ ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
1ኛ/ ህወሓት ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት ግንባር ሆነው የገዙ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴድ በዋነኝነት አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሎቹ ም/ሊቀመንበሮች እና ካቢኔያቸው ውስጥ በፊትና አሁን የሠሩ ሁሉ፤ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
2ኛ/ ህወሓት፣ በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ እስከአሁን ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና ቁስዊ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
3ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጀምሮ እስከ ተጠናቋል በተደጋጋሚ ጊዜ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ከደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ የተደረገው የሰላም ስምምነት ድረስ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው የህዝብ እልቂት፣ ሞት፣ መደፈርና ስደትና ሰቆቃ፣ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡ ኦነግ ሸኔ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በኦሮሚያ ከልላዊ መንግሥት በአማራና ሌሎች ዘሮች ላይ ለፈጸሙት የዘር ፍጅት ወንጀል ተጠያቂ ናቸው፡፡
4ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የኃይማኖት እምነት ተከታዬች ግንባር ይመስረት!!!
(Ethiopian Religious Organization United Front)
What does the demonstration tell you ? People and power , where people have the right to select their leader , honesty is the best political policy.. #JusticeForEthiopia pic.twitter.com/DS3N9SvrTd
— @ዥትዊተር @Ramsey ???????? (@1juxa) June 3, 2023