አሳዛኝ ዜና ልብወለድ የሚመስል ግን “መራር እውነታ”

ወላድ እናት በማንነቷ ኦሮሞ ባለመሆኗ ብቻ በነቀምት ሆስፒታል ከተገላገለች በኋላ ልጇን መነጠቋ እና አባት ከእነ ባለቤቱ ከአስከፊው ጥቃት ሸሽተው መትረፋቸው ተገለጸ።

በነቀምት ሆስፒታል ተፈጥሯል ያለውን አጸያፊ እና ከሙያዊ ስነ ምግባር ያፈነገጠ ዘረኛ አካሄድን አጉልዞ ጥያቄ በሚከተለው መልኩ አጋርቷል:_

331621403 108251625549821 9045876669942140677 n 1 1ማሬ ከተማ ትባላለች። ተወልዳ ያደገችው በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን በአቤደንጎሮ ወረዳ በመንደር 15 ቀበሌ ነው።

ማሬ ከተማ ባለትዳር ናት። ከትዳር አጋሯ ከኦሮሞ ተወላጁ ከጹጋሳ በየነ ለትዳራቸው ማድመቂያ ልጅ ለመውለድ ያስባሉ፥ በዚህም መሠረት ወ/ሮ ማረይ ልክ እንደ ሁሉም ሴት ታረግዛለች።

በአካባቢው የጤና ጣቢያ ዝግ በመሆኑ የተነሳ ከወላጅ እናቷና ከባለቤቷ ከወጣት ጹጋሳ በየነ ጋር በመሆን ለመውለድ በዕለተ እሁድ ማለትም በየካቲት 25-2015 ዓ.ም ወደነቀምት ሆስፒታል ይጓዛሉ።

ወይዘሮ ማሬ ከተማ ነቀምት ሆስፒታል እንደደረሰች በሰላም ትገላገላለች።

ከዚያም ህጻኑም በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኑን ይነግሯታል። ለወላጅ አባትም ለወጣት ጹጋሳ በየነም ይነገረዋል፤ በጣምም ደስ ይላቸዋል።

ወይዘሮ ማሬ የልጇን አይን ሳታይ እናንተ ብሔራችሁ ምንድነው !? ብሎ ዶክተሩ ይጠይቃቸዋል! ጹጋሳ ኦሮሞ መሆኑን ይነግራቸዋል።

በዚህም ንግግር ውስጥ ማረይ ከተማ የሚባል ኦሮሞ የለም። በማለት ዶክተሩ ለወጣቱ ለጹጋሳ ይነግረዋል። የተወለደው ህጻንም የሱ እንደሆነም ይነግራቸዋል።

በመጨረሻም በሆስፒታሉ የአማራ ተወላጆችን አያስተናግድም ህጻኑንም አንሰጥም በማለት ሚስቱን ወደሆስፒታል ወስዶ የሚያሳክመውን የሆስፒታሉ ዶክተሮች በመሰብሰብ ይደበድቡታል።

በዚህም የጹጋሳ በየነ የፊት ለፊት ጥርሱን በመሰባበር “ልጄን ልጄን” እያለ በሆስፒታሉ ጫካ ውስጥ እየሮጠ ያመልጣል።

ከዛም እሷ በአራስ አንጀቷ በሰላም ተገላግላ ከተኛችበት ከአሮጌው የነቀምት ሆስፒታል አልጋ ቁጥር 10 ክፍል በመነሳት ደሟን እያንጠባጠበች ባልጠና ሰውነቷ ህይወቷን ለማትረፍ ከእናቷ ጋር በመሆን ጫካ ለጫካ በማድረግ ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ የከረመችውን ልጇን በአይኗ እንኳን ሳታይ ወደትውልድ ቀዬዋ ተመልሳ ትገባለች።

ወጣቱ ጹጋሳ በየነም ከድብደባው የፊትለፊቱን ጥርስ፣ አይኑንና ሲጓጓለት የነበረውን ህጻን ልጁን አጥቶ ወደቀዬው በየጫካው ደሙን እያዘራ ይገባል። አሁን ማሬ ልጄን ልጄን በማለት እያለቀሰች ትገኛለች።

331622853 599950388648956 6010313503639900656 n 1 1ጹጋሳን ለድብደባ ያበቃው ያንተ ሚስት አይደለችም። ተገዝተህ ነው። የኦሮሞ ባንዳ ነህ በማለት እንደደበደቡት ተናግሯል።

የአለም መጨረሻ የደረሰ ይመስላል። እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት የወይዘሮ ማሬ ከተማን ህጻን ልጅ እና የወጣቱን የጹጋሳ በየነን ልጅ ከነቀምት ሆስፒታል አልጋ ቁጥር 10 በዶክተር አብዲሳ እጅ ስለሚገኝ በወላድ አምላክ ብላችሁ ሼር ሼር በማድረግ ተባበሩ

ለሚመለከተው ሁሉ እንዲደርስ በነቀምት ሆስፒታል የተፈጸመውን ድርጊት በአስቸኳይ ወላጅ እናት እና ህጻንን ለማገናኘት ለሁሉም እንድደርስ ተጠይቋል፤ የነቀምት ሆስፒታልን የፈጠጠ ዘረኝነትን እንቃወም የሚል ጥሪም ቀርቧል።

አሁን ላይ “እህታችን ማሬ ከተማ በተፈጠረባት ነገር በለቅሶ ልትሞት ነው” እባካችሁ ድረሱላት በሚል ተጠይቋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ እና በዙሪያው በሚገኙ አከባቢዎች በነቀምት ሆስፒታል የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት በመቃወም በነቂስ ወደከተማዋ እየተመሙ መሆኑም ታውቋል።

ሰልፉም በነቀምቴ ሆስፒታል ማንነትን መሠረት ባደረገው የህጻናት ዝርፊያ እና ድርጊቱን ለማዉገዝ ነው ተብሏል።

የተፈጸመው ድርጊት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ፣ ከተማረ ሰው የማይገመት፣ ሙያዊ ስነምግባርን የጣሰም ነው ሲሉ በጉዳዩ የተበሳጩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኘው ህጻኑንም በአስቸኳይ ከወላጅ እናቱ ጋር ይመልሱ፤ የሚሉ በርካቶች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በዚህ ሒደት በርካታ ወላድ እናቶች በዚህ አራት አመት ውስጥ ብቻ ከ1,000 በላይ ህጻናት እና እናቶችን አጥተናል።

በድጋሚ በተዘዋዋሪ ይደረግ የነበረውን የዘር ማጥፋት የወንጀል ድርጊት በአሁኑ በቀጥታ እየተተገበረ ነውም ሲሉ በሐዘን ስሜት የአከባቢው ኗሪዎች ገልጸዋል።

ስለሆነም በነቀምቴ ሆስፒታል በአልጋ ቁጥር 10 በቀን 25-06-2015ዓ.ም በሰላም የተገላገለችውን የእህታችን ወይዘሮ ማሬ ከተማ እና የወንድማችን ጹጋሳ በየነን ወንድ ህጻን ልጅን በእጃቸው ያስረክቡልን፤ ሲሉም ጨምረው ሌላኛው አስተያየት ሰጭና ድርጊቱን ለማውገዝ ከሚተሙት መካከል ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

በነቀምት ሆስፒታል የተፈጸመውን አፀያፊ ድርጊት ለሚመለከታቸው ሁሉ ጉዳዩን ያቀረብን ሲሆን ከእነዚህም መካከል፦

የሴቶችና ህጻናት መብት ኮሚሽን

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ)

ለተለያዩ የሐገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የሚድያ አካላት

ለጤና ሚኒስትር

ለአማራ ክልል የጤና ቢሮ

ለመከላከል ሚኒስትር

ለፍትህ ሚኒስትር

ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

ለጠቅላይ ሚኒስትር

ለኦሮሚያ ጤና ቢሮ

ለኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን ያሳወቅን ሲሆን ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።

አሚማ ጉዳዩን በተመለከተ ከአቶ ዱጋሳ በየነ እና ከወ/ሮ ማሬ ከተማ እና ከእናታቸው ጋር ቆይታ አድርጓል፤ የደረሰባቸው በደልም እውነት ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የነቀምት ሪፈራል ሆስፒታል ኃላፊን እንዳገኘን እና ፍቃደኛ ከሆኑ ምላሻቸውን የምናካትት ይሆናል።

@አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

መጋቢት 1ቀን 2015 ዓ/ም

2 Comments

  1. አማራው በርትቶ መከላከያ ሀይሉን ካላጸና ከ500 አመት በፊት ከደረሰበት የከፋ አደጋ ይደርስበታል ብሎ አሳምነው ጽጌ ሲነግርህ መልስ አልሰጠኸውም ። እንግዲህ ዶክተሩ ኦሮሞ ይህን ካደረገ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚማረው የአማራን ደም ጠጡ ስጋውንም ብሉ ከተናገረ ተራው ኦሮሞ ምን ይፈረድበታል? አብይ ስራውን ሰራ ይቅርና ሽመልስ እስኪ በሉት እየሞትን እናያለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

335719504 128714383484009 4329517205669378197 n 1 1
Previous Story

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከጀርመን መንግሥት የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ተገለጸ

Killer abiy 1 1 1 1
Next Story

ያዩትን ወይስ የሰሙትን ማመን ይቀላል? – አሰፋ በድሉ

Latest from Blog

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop