በምዕራባውያን አጋፋሪነት ደቡብ አፍሪቃ፣ ፕሪቶሪያ ላይ የሚካሄደው ዱለታበኦነግ የበላይነት የወያኔን ሎሌነት በማስቀጠል የአማራን ሕዝብ ቴሳ ለማጥፋትሁለቱ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ከአማራ ሕዝብ ጀርባ የሚስማሙት ስምምነት መሆኑን የማይረዳ ሕፃንወይም ሕጹጽብቻ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ዋና የሕልውና ጠላት የሆነው ጭራቅ አሕመድደግሞ፣ ጅል፣ ጅላጅልና ጅላንፎ እያለ የሚሳለቅበትን የአማራን ሕዝብ የሚመለከተው የማስታወስ ችሎታ የሌለው (short memmory) ሕጹጽ አድርጎ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪቃው ጉዳይ የአማራን ሕዝብ የማይመለከት የኦነግና የወያኔ ጉዳይ ነው ሲባል፣ ከደመቀ መኮንን ወዲያ አማራ ላሳርበማለት ያሾፈውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡ ስለዚህም፣ መሠረታዊው ጥያቄ “እውን ደመቀ መኮንን የአማራ ሕመም የሚያመው አማራ ነው?” የሚለው ነው፡፡
ደመቀ መኮንንበትምህርቱ ብዙም ያልገፋ ከመሆኑም በላይ ራሱን በራሱ የሚያስተምር ዓይነት ሰው አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ የሚያውቃትን በደንብ መግለጽ የማይችል አንደበተግድር(challenged) ከመሆኑም በላይ በራስ መተማመን የሚባል ነገር ምናምኒትም እንደሌለው በግልጽ ያስታውቅበታል፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ኃላፊነት መውሰድን እንደ ጦር የሚፈራ የጃግሬነት ሰብዕና (follower mentality) በጽኑ የተጠናወተው፣ ለጀሌነት እንጅ ለመሪነት ያልተፈጠረ ጃግሬ ግለሰብነው፡፡ ደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን ቢባል በቤተመንግሥት አጥር ዘሎ ድራሹ ይጠፋል የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡
ይህን በእውቀትና በመንፈስ ደካማ የሆነ የምድረገነት(ከሚሴ) ግለሰብ፣ ላኮመልዛ(ወሎ) የኦሮሞ ነው በሚለው የኦነጋውያን የፈጠራ ትርክት አጭበርብሮ ወደ ቀንደኛ ኦነጋዊነትለመቀየር፣ ላጭበርባሪው ለጭራቅ አሕመድእጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ የደመቀ መኮንን ተግባር በግልጽ የሚያመለክተው ደግሞ ግለሰቡ በጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ ስብከት ታውሮ፣ ከወያኔነት ወደ ኦነጋዊነት ተቀይሮ፣ ከለማመበት የተጋባበት ወይም ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኖ፣ የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ ከጭራቅ አሕመድ በላይ እያራመደ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ደመቀ መኮንን አማራ ሳይሆን የአማራ ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላነው፡፡
ደመቀ መኮንን የአማራ ሕዝብ መሪ ነኝ እያለ፣ አማራ ሕዝብ በኦነግ ሲጨፈጨፍ ዝንብ የሞተ ሳይመስለው ድመጹን አጥፍቶ የተቀመጠው የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ባጭሩ ለመናገር ደመቀ መኮንን የወለጋንና የመተከልን አማሮች ቀርቶ የገዛ ልጆቹን ለጭራቅ አሕመድ ጭዳ አድርግ ቢባል፣ ለእርድ ለማቅረብ ቅንጣት የማይቃማማ፣ ለጭራቅ አሕመድ ፍጹም ታማኝ የሆነ የጭራቅ አሕመድ ፍጹም ሎሌ ነው፡፡
የሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋሚስጥር ቁልፉ ያለው ደመቀ መኮንን የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ መሆኑን በመረዳትና በጭፍጨፋው ወቅት ቦሌ አየር ወደብውስጥ ጃኖች መንፈላሰሻ (vip lounge) ተቀምጦ ምን ሲያደርግ እንደነበር አጥብቆ በመጠየቅ ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡ ደመቀ መኮንን በራስ መተማመን እጥረት የሚሰቃይ ሰው ስለሆነ፣ እነከሌ በማንነትህና በምንነትህ ይንቁሃል ብሎ በመስበክ ለበቀል እንዲነሳሳ ማድረግ ለሐሳዊ ተዋኙ(con artist) ለጭራቅ አሕመድ የሕጻን ጨዋታ ያህል ቀላል ነው፡፡ የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትርእንዲሉ፣ እንደ ደመቀ ዓይነት፣ ውሃ ውስጥ የሚያልበውቱርቂ ደግሞ ለበቀል ከተነሳሳ ብትሩ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ ደመቀ መኮንንን በበቀል ስሜት አነሳስቶ ባሕርዳር ላይ ለፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ግብራበሩ ካደረገው ደግሞ፣ ወንጀለኛነቱን እንደ ማስፈራርያ በመጠቀም ሲጠራው ወዴት፣ ሲልከው አቤት፣ ዝቀጥ ሲለው እስከየትየሚል፣ አፋሽ አጎንባሽ ሎሌው ያደርገዋል፣ አድርጎታልም፡፡
ተመስገን ጡሩነህደግሞ ጭራቅ አሕመድን ለማስደሰት እንጦረንጦስ ለመውረድ ዝግጁ የሆነ፣ በጭራቅ አሕመድ ስም ምሎ የሚገዘት፣ የጭራቅ አሕመድ ባልደረባ ሳይሆን ጃንደረባ ነው፡፡ ተመስገን ጡሩነህ ሲፈጠር ጀምሮ አማራዊነት የሌለው ወይም ደግሞ አማራዊነቱን በጭራቅ አሕመድ የተሰለበየጭራቅ አሕመድ ስልብ፣ ደንገጡርወይም የጭን ገረድነው፡፡ ተመስገን ጡሩነህ ለሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ከጭራቅ አሕመድና ከደመቀ መኮንን ቀጥሎ ዋናው ተጠያቂ ወንጀለኛነው፡፡ ተመስገን ጡሩነህ ልክ እንደ ደመቀ መኮንን ከኦነጋውያን በላይ ኦነጋዊነት የሚሰማው የአማራ ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላነው፡፡ ተመስገን ጡሩነህ የአማራ ጥላቸው ከውስጡ እየገነፈለ ግንባሩ ላይ ተንጨፍጭፎ እፊቱ ላይ በመከልበስ በግልጽ የሚነበብበት፣ አማራን የሚጨፈጭፉትንና የሚያስጨፈጭፉትን ለማመስገንና ለመሸለም የሚሽቀዳደም ወደር የሌለው አማራጠልነው፡፡ ተመስገን ጡሩነህ ፋኖን ሳያጠፋ ላያንቀላፋ በጌታው በጭራቅ አሕመድ ስም ምሎ የተገዘተ ፀረፋኖ ነው፡፡ ተመስገን ጡሩነህ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራን ሕዝብ ‹‹ወንጀለኞችን የሚያወድስ ማሕበረሰብ›› በማለት ሸንጎ ላይ በይፋ በመሳደብ የአለምነው መኮንንን፣ የሽመልስ አብዲሳንናየታየ ደንድኣንስድብ የደገመ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ጭራቅ አሕመድ የጫነው ትልቅ መርገምትነው፡፡
የትም ይወለዱ የትም፣ ደመቀ መኮንንንና ተመስገን ጥሩነህን የመሳሰሉ አማራዊነት የሌላቸው የብአዴን ፀራማራ ተኩላወችያላቸው ቋሚ ባሕሪ አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም እጅግ የከረረ የአማራ ጥላቻነው፡፡ ስለዚህም ፀራማራ የሆነን ማናቸውንም ቡድን በሎሌነት ለማገልገል ሙሉ ፈቃደኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ ሙሉ ደስተኞችም ናቸው፡፡ በመለስ ዜናዊ ዘመን የወያኔ ታማኝ ሎሌወች እንደነበሩ ሁሉ፣ በጭራቅ አሕመድ ዘመን ደግሞ የኦነግ ታማኝ ሎሌወች ሁነዋል፡፡ ከወያኔ ሎሌነት ወደ ኦነግ ሎሌነት በቀጥታ መሻገራቸው ደግሞ ለሌላ ሰው እንጅ ለነሱ ምንም ተቃርኖ የለውም፡፡ለነሱ የሚታያቸው ፀራማራነት ብቻ ስለሆነ፣ በነሱ ዕይታ መሠረት በወያኔና በኦነግ መካከል አንዱ የትግሬ ሌላው የኦሮሞ ፀራማራ ከመሆኑ በስተቀር ሌላ ልዩነት የለም፡፡ ስለዚህም እነዚህን የብአዴን ተኩላወች ይበልጥ የሚያረካቸው ሁለቱ ፀራማራወች (ማለትም ወያኔና ኦነግ) ባንድነት ተባብረው አማራን ይበልጥ ቢያጠቁላቸው ከቻሉ ደግሞ ሕልውናውን ቢያጠፉላቸው ነው፡፡
ስለዚህም ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጡሩነህ የፕሪቶሪያውን ድርድርእንዲመሩ በጭራቅ አሕመድ የተመረጡት፣ ወያኔንና ኦነግን አስታርቀው ለፀራማራ ዓላማቸው እንዲተባበሩና የአማራን ሕልውና ክስመት እንዲያፋጥኑያደርጉ ዘንድ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም፣ የአማራ ሕልውና የሚያሳስባቸው የአማራ ልሂቃን ሁሉ፣ በደመቀ መኮንንና በተመስገን ጡሩነህ መሪነት በወያኔና በኦነግ መካከል የሚካሄደውን ድርድርንም ሆነ ውጤቱን በፍጹም እንደማይቀበሉት ማወቅ ለሚገባው ሁሉ፣ በተለይም ደግሞ ለባለጉዳዩ ለአማራ ሕዝብበደንብ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ የወያኔና የኦነግ ሕገመንግሥት አማራን እንደማይመለከት ሁሉ፣ የወያኔና የኦነግ ድርድርም አማራን አይመለከትም፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com