August 28, 2022
20 mins read

የአማራ ብልፅግና ግሳግስ ሆይ ወይ ይቅርታ ጠይቅ ካልሆነ አሁኑኑ ስልጣን ልቀቅ !!! (ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ)

የጦርነቱን ፍልሚያ ለእውነተኞቹ የቁርጥ ቀን የአማራ ጀግኖች ፣ ፋኖና ልዮ ሃይል ተውለት። ወያኔን አፈር ድሜ ማስገባት ያውቅበታልና!

ONLD 750x500 1ጦርነት በማሸነፍ ስነ-ልቦና የተዋጀ ከሆነ፣ የማይሸበረክ መንፈስ ካለ ፣ ወላዋይነት ከሌለ፣ በአሻጥር ካልተተበተበ፣ በፍራቻ ካልናወዘ ፣ ቆራጥ የሆነ ተዋጊና አዋጊ ያውም ለጦርነት አስፈላጊ የሆኑ ግባአቶች በእጅ እያሉ ይቅርና ልበ ሙሉ ሰራዊት በቁመናው ብቻ የማይደፈር ተገዳዳሪ ፣ አሸናፊና ፍልሚያም ካለ የማሸነፍ ብቃት ያለው ኃይል ነው.። ይህ አይነት ቁመና ያለው ሰራዊት ማሰማራት ለድል ያበቃል ፣ ድሉንም በአጭር ጊዜ ማብሰር ይቻላል።

በቀደምት ታሪካችን “ እንኳን አሁንና ሙሉ ትጥቅ እያለን በጦር በጎራዴ ታንክ እንማርካለን “ ተብሎ ተዚሞ የለም እንዴ።

የአሁኑ የኢትዮጵያ የብልፅግና መንግስት ፍራቻ የአማራ ሰራዊት በጦርነት ብቃትና ስልት ዓለም ያወቀው ፣ የሞራል ልዕልና ያለው፣ በሃገሩ ከመጡበት ግንባሩን ለጥይት የሚሰጥ እንዲሁም የአሸናፊነት መንፈስ የተላበሰ ፣ አንዴ ጦርነት ውስጥ ከገባ የመጨረስ ብቃቱ በተለያየ አውደ ውጊያወች በዘመናት መካከል ስለሚታወቅ ፣ ህውሃትንም ለአራት ኪሎ ቤተ- መንግስት ያበቃው አማራው መሆኑን ውስጠ ህሊናቸው እነ-ብልፅግና ስለሚያውቁት አሁን የተጀመረው ጦርነት በአማራው አሸናፊነት እና የበላይነት እንዲደመደም የማይፈልጉ ምኒልክ ቤተ መንግስት ጉብ ያሉ ጉግ ማንጉጕች አሉ። አማራ ድል ቀንቶት ካንሰራራ የኦሮሞን የበላይነት “ አፈርድሜ ያበላዋል፣ መቀመቅ ያስገባዋል የሚል ህሳቤ በተረኞቹ ስላለ ሃገረ ኢትዮጵያን ለተራዘመ ጦርነት ዳርገዋታል።

አማራ ከገነነ ፣ እንደገና ካንሰራራና የድል መንፈስ ከተጎናፀፈ የቀደመችውን ታላቅዋን ፣ በአንድነት ውቅር የተሰራች እና በዓለም የተፈራች ኢትዮጵያን እንደገና ያመጣታል “ የሚል ህሳቤና መርበትበት ግልፅ ሆኖ በአመራሮች በኩል ይታያል። ለዚህ ነው ጦርነቱ መቋጫ ያጣው ፣ ወገንም ሊያውቀው የሚገባው በተለይ ሃገር ወዳዱ የአማራና የአፋር ሕዝብ ለእልቂት እንዲዳረግ ሆን ተብሎ በአሻጥር እየተሄደበት እና እየተከወነ መሆኑን ሊገነዘብ የግድ ይለዋል።

የጦርነቱን ሂደት የሚመሩት ጄነራሎች ሆነ ፊልድ ማርሻሎች ፣ በላይኛው የስልጣን ቁንጮ የተሰየሙት ለአፋቸው ስለኢትዮጵያ ልህልና ይተርካሉ እንጂ “አብረው ከህውሃት ጋር አንሶላ ስለተጋፈፉ ፣ የአገሪቱን ካዝና በጋራ ስላራቆቱ ፣ እጃቸውን አጣምረው በደቦ የወይን ብርጭቆ ስላጋጩ ፣ ሻኛና ቁርጥ ስጋ በአንድ ቤላ አየቆረጡ ስለተጎራረሱ ፣ ቤተ-መንግስቱንም በቡጊ-ቡጊ ዳንስ ተቃቅፈው አሸሸ ገዳሜ ስላሉበት ወዘተ ለወያኔ-ህወሃት የሚጨክን አንጀት የላቸውም ፣ ቢቻል ተደራድረው ሃገረ ኢትዮጵያን እንደገና ቢመዘብሩ ደስታቸው ነው።

አሁን አማራውን እንመራለን የሚሉት የአማራ ብልፅግና ተብየዎች እነ አምባቸውን ፣ ጀነራል አሳምነውን ቆርጥመው የበሉ ፣ ፋኖን በኦነጉ ብልፅግና ቀጭን ትእዛዝ መውጫ መግቢያ ያሳጡ ፣ያሰሩና የገደሉ ናቸው።

ለህውሃት አማራን እያራቆቱ ቀለብ እየሰፈሩ ለአራተኛ ጦርነት ያደራጁ ፣ ህውሃትን “ቀንቷችሁ አዲስ አበባ ከገባችሁ እንደራደራለን ፣ ወልቃይት ራያንም አታስቡ ፣ የስልጣን ዕርካቡን ከያዛችሁ በበነገታው ለናንተው ጀባ እንላለን” ብለው የተማማሉ የአንድ መንደር ልጆች የተሰባሰቡበት ቡድን ስለሆነ ከእነዚህ የአማራ የእንጊዲህ ልጆች መልካም እና ድል መጠበቅ ጅላ ጅልነት ነው።

ይሄው ህወሃት የጦርነት ነጋሪት ሲጎስም የአማራ ብልፅግና የአንድ ሰፈር ድቡኝቶች “አይጥ እንዳየች ድመት “ አልጋ ስር ፣ ቁም ሳጥን ስርና በአየ ካቡ ስር ተደብቀው የሚይዙትን የሚጨብጡትን አጡ። በደህና ፣ ጫ እና በተትረፈረፈበት ጊዜ “ አይዞህ ያላልካው ወገን ለዛውም ያንገላታህው ፋኖ ታዘበህ ። “በመእንተ እፍረት እንደ ዐፄ ሚኒሊክ “ መኮኑ ነው “ የክተት አዋጅ “ ብለህ ያወጅከው። ይልቅኑ ያዋጣኛል ብለህ ካጎበደድክለት የኦነግ ብልፅግና ጎን “የአማራ ብልፅግና ሆይ ሂደህ ተወሸቅ” እንላለን ። ፍልሚያውን ለሚመለከተው ፣ ለቆራጡ፣ ለቁርጥ ቀን ደራሹ ፋኖ እና ልዩ ኃይሉና ለአማራው ሚሊሻ አስረክብ።

የአማራ ብልፅግና መፈርጠጥ መጀመርህንም ከአንድ ሰፈር ድሩየዎች የሚጠበቅ ነውና “እግሬ እውጭኝ” ብለህ ወደ እናትህ ጓዳ እያስነካህው ነው አሉ። “ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ “ እንዲሉ ህወሃት ከዚህ ደረጃ ደርሶ የአማራን ምድር እስኪዳፈር ድረስ የት ነበርክ ጃል? ።

የአማራ ሕዝብ የጀግንነት ቁመናና የጦርነት ውሎ አውደ ታሪክ።

የአማራ ሕዝብ እንኳን ለህውሃት ዱርየ ለፋሽሽት ጣሊያን ፣ ለሱሜሌ ወራሪ እና ለገጣይና አስገጣይ አልተበረከከም ፣ በሻጥር ትብተባ መንበረ ሥልጣኑ እንዲቀማ ተደረገ እንጂ።

አማራ በሶስት ሺህ ዓመት የዘመናት ቀመር ኢትዮጵያን ቀጥ እድርጎ በአስተዳደረበት ወቅት ሁሉ እንደ አሁኖቹ የዳቦ ስም የተሰጣቸው የ27 ዓመት እና የአራት ዓመት ተረኞችና በሻሞ ስልጣን እንዳገኙት ብሄሮች በማንነቱ ሳይኩራራ ፣ ቱሪናፋና ጉራ ሳይነፋ አማራነቱን ጌጡ አድርጎ ኢትዮጵያን ከፍ እያደረገ ፣ ከሌሎች ሃገር ወዳድ ህዝቦች ጋር በተረጋጋ መንፈስ መርቷል ፣ ድንበሯን ሳያስደፍር በዓለም አቀፍ መድረክ አስከብሯት የዘለቀ ሕዝብ ነው።

የአማራ እና የትግራይ ሕዝብ የሚጋሩት የሃይማኖት ፣ የባህል ፣ የቱፊትና የአኗኗር ዘየ አላቸው።

ባህል /Way of life/ የተለያዩ ቀመር ያካተተ ሲሆን ቋንቋ፣ አመጋገብ ፣ ስነ- ዕንፀት፣ ሙዚቃ ፣ የጦርነትና የውጊያ ስልትን ፣ የመንግስት አስተዳደር ፣ የሕግ ውቅርን ወዘተ ያካትታል

በሰላሙ እና በመልካሙ ዘመን የአማራ ዐፄዌች ረዘም ላለ ዘመናት ፣ የትግራይ ዐፄዎች ለውስን ጊዜ ኢትዮጵያን አስተዳድረዋል ፣ ኢትዮጵያን ከወራሪ ሃይል በጋራ መክተዋል።

ይህን ስንል አንድ ሌላኛውን ለማጥቃት በተለይ የትግራይ ነገሥታት አማራው ለዘመናት ኢትዮጵያን በመንግስትነት ፣ የንግሥናውንና የስልጣን ቁንጮውን ለተራዘመ ጊዜ ጨብጦ ለኢትዮጵያ ቀናይ ሆኖ በመዝለቁ ፣ ኢትዮጵያን ሃዋህዶና አጋምዶ በማሻገሩና ደፋ ቀና ማለቱ ስላልተዋጠላቸው ወይም የቅናት መንፈስ ተጠናውቷቸው የትግራይ አፄዎች ከውጭ ጠላት ጋር ተጣምረውና ተቆራኝተው አማራውን ለማጥቃት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።

What is the root cause of Tigrayans hatred towards Amhara?

Do Tigrayans hatred have any historical cause or is it just a tactical used by the previous regime to get to power. Their songs are said to show deep hatred towards Amhara.

Anyone who is inform will be of great help because we could be heading to a vicious situation, the opposite happening now.

አማራው ለኢትዮጵያ ያለውን ቀናይነትና መቀመቅ ለማስገባት፣ ከከፍታው አውርደው ለመጣል ፣ በብቃት የታጀለውን ፣ በአንድነት መንፈስ ኢትዮጵያን በሆደ ሰፊነት የመምራት ትብዕሉን በአሻጥር ፣ በጦርነት ፣ ከቀሪው ብሄር ጋር በማቃቃር በተለይ በሕዝብ ቁጥር ተመጣጣኝ ከሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ጋር ለማናቆር ያደረጉትን መሰሬነት ላገናዘበ እንኳን ከጎረቤት ፣ ደንበረተኛና የኢትዮጵያ አካል ሆኖ ከኖረ ሕዝብ ይቅርና ከዘመን ተሻጋሪ የጎረቤት ሃገር በላንጣዎች ፣/ Strategic enemies/ እንዲህ አይነት መሰሬነት አልተሞከረም።

እማራው ህውሃትን ከመንበረ ስልጣኑ ከሌሎች አጋር ኃይሎች ጋር ሆኖ ወደ ደደቢት ስለመለሰው ህወሃት ቂም ቋጥሯል ፣ ይህንንም ቂም ለመወጣት እስከ ሲኦል ድረስ በሚለው ፈሊጡ መሠረት በኦነጋዊው ትብዕል ከተጠመቀው የአማራ ብልፅግና ተራ ሰፈርተኛ ጋር በመሆን የታጠቀውን መሳሪያ አስወርደውና ትጥቅ አስፈትተው የአማራ ገበሬን እያሳረዱት፣ ሴት ልጃገረድ ልጆችን እየስደፈሩበት ፣ መሰረተ ልማቱን እንዲወድምና መላ ቁመናውን ለመሸርሸር እየሞከሩ ይገኛሉ።

በአስራ ሰባት ዓመቱ የደርግ ጦርነት ዘመን የህውሃት ቡድን በኢሕአፓ ፣ በኢዲዮና በሚኤሶን ላይ የፈፀመው ስውር ሻጥር እንዳለ ሆኖ በደርግ “የደንባራ በቅሎ ጉዞ” ተደናቀፈ እንጂ በተለይ የወልቃይት ፣ ጠገዴ ፣ በለሳ እና የጎንደር ህዝብ እንዴት ወያኔን ያርበደብደው እንደነበር ህወሃት ያውቀዋል። “ኢትዮጵያን ከደርግ የጭቆና ምንጋጋ እናውጣ ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ሰቲት ሁመራ የጎንደር አማራ ነው” በሚል ማጭበርበሪያ ስልት ወደ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት የስልጣን ዕርካብ ለመሻገር ወያኔ ከፈፀመው ማጭበርበር በፊት የጎንደሬውን አማራ ክንደ ብርቱነት በሚገባ ህውሃቶች ያውቁታል።

ስለዚህ የአማራው እና የትግራይ ሕዝብ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ለጦርነት ማንሳሳት ቢቀፍም ሕውሃቶች አማራን በሕዝብ ማህበል ለማጥፋት ስለተነሱ እነሱ በሚከተሉት የጦርነት ስልት የግድ የተከፈተውን ውጊያ እነሱ በያዙት ስልት መጋፈጥ የግድ ስለሚል “ሀሞትህ የፈሰሰው፣ ግራ የገባህ እና መጀመር እንጂ መጨረስ ያልቻልከው የኦነግ ብልፅግና እና ተጋላቢው የአማራ ብልፅግና አማራን ብሎም ምድረ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳውን ጦርነት ለአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች አስተላልፍ እንላለን ።

ብልፅግና ሆይ የአማራ ልዮ ኃይል ፣ ፋኖና ሚኒሻን ተጋድሎ አፍህ ለመመስከር ቢለጎምም በሶስት ጊዜ ተደጋጋሚ የህውሃት ወረራ ወቅት እንዴት አድርጎ እንደመከተና ህውሃትን መግቢያ መውጫ እዳሳጣው ታውቀዋለህ ፣ እጅህም ተጠርንፎ ወደ ማዕከላዊ የቀድሞው የወያኔ ቅሊንጦ እዳትወርድ እዳዳነህ ልብህ ያውቀዋል።

ከተቻለ ከድል በኋላ እረፍት እግኝተህ በኢትዮጵያ ምድር ሻሂ ፣ ቡና እና መሸታ ቤት እሸሸ ገዳሜ በተረጋጋ መንፈስ ትከውን ዘንድ የአማራን ጀግኖች በወጉ አስታጥቅ ያውቁበታልና። ” የሃገሩን ሰርዶ በሃገሩ በሬ” እንዲሉ ኢትዮጵያ ትድን እና ሰላም ታገኝ ዘንድ ያለው አማራጭ ጉራ ጉሩን ለሚያውቁት ፣ በዘመናት መካከል አብሮ በመኖርም ይሆን ፣ እርስ በርስ ጦር በተማዘዙ ጊዜም እንዴት እንደሚፋለሙና ድሉንም በማያዳግም መልኩ ፈፅሞ ኢትዮጵያን ወደ ነበረችበት ማማ ከፍ ለሚያደርጋት ሃቀኛ ለሆኑት ለአማራ ውገኖችህ ሃላፊነቱን ፣ ግዳጁንና የጦርነቱን ውሎ አስተላልፍ። ከማይበጅህ እና ከአጥፊህ ከህውሃት ጋር እትጎናበስ አትታከክ ፣ እወቅበት።

ማጠቃለያ

እኛ አማሮች መታረድ ፣ ግፉ ፣ መደፈሩና ሰቆቃው በዛብን ፣ ነፃነታችን በራሳችን ክንድ ለመመከት አቅሙ ሆነ ታሪካዊው ውቅር እና ልምዱ አለን ። ከውጭ ወራሪዎች ከፋሽሽቱ ጣሊያን ፣ ቱርክ ፣ ግብፅ ፣ ማህዲስት ወዘተ ጋር እየተጋፈጥን ሃገረ ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እድትቀጥል መስዋዕት ከፍለናል ። የእርስ በርስ ጦርነት ለእኛ አማሮች ጥዮፍ ነው ነገር ግን ለህልውናችን ጠንቅ ከሆነ የውጭ ሃገር ጠላት ቅጥርኛው ህወሃት ጦር ጋር ለመጋፈጥ እቅሙም ፣ ታሪካዊው ውቅርና ብቃት ስላለን እና በተለያየ የጦር ውሎ ስለተፈታተንና ስለምንተዋወቅ ከማንም ጣልቃ ገብነት በጠራ መልኩ እድንጋፈጠው እድሉ እዲሰጥን በሃገረ ኢትዮጵያ ስም እንጠይቃለን ። ጦርነቱ ተራዝሞ ለጉዳትና ለከፋ ክስተት የተጋለጥነው በስማ በለው በተነሱብን አመራርና ተረኞች ሻጥር ነው ብለን ለመደምደም ተገደናል። በራሳችን ጉድ የጉድ የእንግዲህ ልጆች “የአማራ ብልፅግና” ተብየዎች ፣ እንደ ጋሪ ፈረስ ተጎታቾች እና የዘመናት ተለጣፊዎች ተዋርደናል ፣ ማንነታችን አደጋ ላይ ወድቋል።

ስለዚህ ፊት ለፊት እየተዋጋን ካለው የህውሃት ጋር ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ እንጋፈጠው ዘንድ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ። ከተቻለ ሕውሃት በጦር ኃይል ፣መሳሪያ በታሪካዊ ጠላቶቻችን እገዛ ስለተደራጀ የጦር መሳሪያ እና አስፈላጊው ቁሳቁስ የኢትዮጵያ ሃብት የጋራ ሃብታችን ስለሆነ ያልተቆጠበ ድጋፍ እንጠይቃለን ። የአማራ ብልፅግና ተብየው ብቃቱ ስለሌለው በአማራ ጎበዝ አለቃ ፣በፋኖ ፣ በሚኒሻ እና ልዮ ሃይላችን ታቅፈን ጦርነቱን እድንጋፈጥ ከአደራ ጋር እንጠይቃለን ፣ ኢትዮጵያንም ከመጣባት አደጋ ከአምላክ ጋር ሁነን እንደተለመደው እድንታደጋት ዕድሉ ይሰጠን እንላለን።

ኢትዮጵያ በአማራው እና በቀሩት ልጆቿ ተጋድሎና አርቆ አሳቢነት ወደ ነበረችበት ክፍታ ማማዋ ትመለሳለች።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop