January 1, 2022
3 mins read

ሰው ሰው ካልሆነ … – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ሰው ሰው ካልሆነ
አይቀር እንደሁ ፤ አዲስ ዘመን መጥባቱ
የኖረ ሰው ቀን ቆጥሮ ፤ ሌላ አንድ ማየቱ
በሰው ቀመር ዘመን ወደዘመን
አይቀርለት መዘመን ።
123 …እያለ ቀን በቀን ላይ መከመር ፤
365 ቀናትን መንጎዱ ፤ በጥላቻና በፍቅር …
ዘመን ተቀየረ ፣ አዲሰ ሆነ ተብሎ ፤
ልባችን ካልተቀየረ ፤ የድሮው ላይ ተቸክሎ ፤
ክፋት ፤ … ና ሥግብግብነትን አዝሎ ።
ህሊናችን ፣ በአዲሱ ዘመን ፤ አሶግዶ ጥላቻን ፤
ካላነገሰ በልባችን ፍቅርን ፤
በንሥሐ ካልተቀየርን …፤
የክፋት ልብ ና አእምሮ ፤
ካለ በሰው በውሥጣችን ወፍሮ ፤
ምን ይፈይዳል የዘመን መቀየር ፤
365 ቀን ሆኖ ቢሽከረከር ?
( በተለመደ ዙረቱ ቢዟዋዟር )
የሰው ልብ ውብ ካልሆነ ፤
ተንኳሉን በጭምብል እየሸፈነ ፤
2022 ዓ/ም አዲስ ነው ብሎ ፤
አሮጌውን በጉያው አንጠልጥሎ ፤
እየኖረ ሰው ሁላ ፤
ሆኖ የቀን ተላላ ።
ምን ይጠቀማል አዳሜ ?… ባልተለወጠ ልቦና
አሥቀድሞ የታወቀ ቁጥርን እንደ አዲስ ተካና
አሮጌው ትላንት አዲስ ተብሎ እንዳልተከበረ
ሰው ሁሉ ከረሳ ዛሬ በነገ ሲፈራረቅ እንደኖረ ።
ከአዲሱ 1 ጋር ፣ እንደ አንዲስ ራሱን ካልቀየረ
ቅንነትን ካልሰበከ ፣ በፍቅር ከሰው ጋር ካልኖረ
ሰውነትን አንግሶ ፤ ከዘመን ጋር ካልዘመነ
ምኑንን በአዲስ ዘመን አዲስ ሆነ ?
ቀርቶ በጥንቱ አመለካከቱ እንደተቸከለ
ሰውነቱን እረሥቶ ሰው ፣ ሰው ላይ ግፍ እየዋለ ።
ሰው ፣ ዘመን ሲቀየር ፤ የክፋት ልቡን ካልቀየረ ፤
( ሰው ሰው መሆኑንን ተረድቶ ፤ ሰው ሰው ከልሆነ )
ምኑን አዲሱን አከበረው ፤ ያለፈ ዘመኑን እየኖረ ።

01/01/2022 ዓ/ም
እንኳን ለአዲስ ዘመን አበቃችሁ ። አውሮፓውያን ። አሜሪካውያን ። አፍሪካውያን ( ኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠሩ ባይመለከታትም በአገራችን የምትኖሩ ሰዎች ሁሉ ። …) ዘመኑ አዲስ የሚሆነው ፣ ዛሬ በህይወት ያለ ሁሉ ከልቡ ጥላቻን አሥወግዶ ፍቅርን ሲያነግሥ ነው ። ያለበለዚያ አዲስ የሚባል ነገር የለም ። ቁጥር ብቻ ነው ። ሁሉም ድግግሞሽና በዙረቱ የሚመጣ አሠልቺ ቁጥር ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop