ዘመን የማይሽረው ቸነፈር ፣ ፀበል የማይፈውሰው ውቃቢ ሆንክብን፤
ኧረ ተወን! ተወን ኮኸን ተጀርባችን ውረድልን!
ዘር አምላኪ ጣዖቶችን አገናኝተህ ዘርን ተዘር እንዲያጋጩ በር ከፍተህ ፣
ለብዙ ዓመት እንደ ዓባይ ወንዝ የፈሰሰ ደም ረሳህ?
ወይስ ለጦቢያ ነፍስ ቅንጣት ታህልም ደንታ የለህ?
ኧረ ተወን! ተወን! አቶ ኮኸን በፈጣሪ ተወን ተወን!
በዘር ውቃቢ የሰከሩን እያሰከርክ ዛሬም ዳግም አታባላን!
ሕዝብን በዘር መከፋፈል፣ “ቅዱስ መንፈስ” ተመሰለህ፣
ምነው አትሰብክ የዘር ክልል በአገርህ በመንደርህ?
በጠነጠነው በዚህ እድሜህ እግርህ ሲገባ ተጉድጓድ፣
ምነው አልታይ አለህ ያለቀው ሕፃንና አሩግ በሰይፍ በባሩድ፣
መርጦ ባልተወለደበት በዘሩ በሚናገረው ቋንቋ ምክንያት?
እድሜ በአይበሉብሽ ሲደቃህ መቀበል ሲገባህ ንስሃን፣
ዛሬም እንደ ትናቱ ታበራታለህ የዘር ጎራዴ ሳይዎችን!
ተወንበር በሰቀልካቸው አውሬዎች የተበላውን ወጣቱን፣
ማህጸናቸው ተቀዶ ተነፅንሳቸው የታረዱትን ሴቶችን፣
ተዝካር አውጥተን ሳንጨርስ ዳግም ለመከራ አትዳርገን፣
ኮኸን! ኮኸን! ኧረ ተወን! እባክህ ተወን! ተወን! ተወን!
በላይነህ አባተ ((abatebelai@yahoo.com)
ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ. ም.