“ዛራፍ ! …
አካኪ ! ዘራፍ !
ሮጬ እገባለሁ !
ከእናቴ ቀሚስ !
ህዝብ ሲጯጯህ !
ጀግና ሲጋደል !…
እምቢኝ ! ባርነት ሲል…
እምቢኝ !….ጭቆና ሲል።
እኔን ምን አገባኝ !?
“በአፍ ይጠፉ!
ኡ !ኡ ! …
በለፈለፉ ! …
በአንድ ድፋር ነው!
ሺ ጓደኞቹ !…
የሚቀሰፉ !
ኡ!ኡ! …
ዴሞክራሲ ፣ ፍትህ ፣ነፃነት
ከቶ አይገባኝም ፤
በእነሱ ዳፋ ፤
ምች አይመታኝም !… “
ብዬ እጮኻለሁ…
እያልኩ አቅራራለሁ።
“ዘራፍ! ዘራፍ ! ዘራፍ !
የጠቅል አሽከር !…
ዘራፍ ! ዘራፍ ! ዘራፍ!
የደርጊ አሽከር !!…
ዘራፍ! ዘራፍ ! ! ዘራፍ!
የወያኔ አሽከር !…
ዘራፍ !ዘራፍ ! ዘራፍ !
የብልፅግና አሽከር !
የወዘተ አሽከር !”
ዛሬም እላለሁ …
የ66ቱ አልሞትኩም አለሁ።
ዛሬም በዘመናዊ ፉከራ
ምን አለ ?…
እንደትላንት ሐሰት ባወራ ??? 2013 ዓ/ም የግጥሙ ደራሲ መኮንን ሻውል ወ/ጊ
ብሔርተኝነት ፊክሽን እንጂ ፋክት አይደለም።
መኮንን ሻውል ወ/ጊ
ለዚህ ፅሑፍ መነሻ የሆነውን የፅሑፉን መግቢያ ግጥም የፃፍኩት የአገሬ መንግሥት የፖለቲካ አካሄድ ክፉኙ ሥላሥፈራኝ ነው።
ከፉኛ አሥፈራኝ ሥል በዜጎች ላይ ያንዣበበው የሞት ጥላ ታይቶኛል ማለቴ መሆኑ ይታወቅልኝ።ይህንን ሥል አንዳንዶች እንደሞርተኛ ፣ ጥቂቶች ደግሞ በካራቴ ሴጣንን እንደሚያደባልሉት የኃይማኖት ሰዎች ሊቆጥሩኝ ይችላሉ። ይሁን እንጂ እኔ ከሁለቱም የለሁበትም። ማርያምን !!
በግጥሜ ለማሳየት እንደሞከርኩት፣ የአገሬ መንግሥት የፖለቲካ አካሄድ ፣ ከደርግ እና ከወያኔ አዙሪት ያለመውጣት ብቻ ሳይሆን ያሳሰበኝ፣ በተቃውሞው ጎራ ያሉ ጎምቱ ፖለታከኞቻችን ዛሬም ፈረሶቻቸውን ያለመቀየራቸው ና በትላንት ጥፋታቸው ከቶም ያለመፀፀታቸውም ጭምር ነው።
የዛሬዎቹ ወጣት ፖለቲከኞችም ፣ ጎምቱዎቹ በቀደዱላቸው ፣እጅግ በሚቀፍ የጥላቻ ና የሞት ቦይ ውሥጥ በጭፍን የሚጎዙ የራሳቸው አዲስ አሳብ ከቶም የሌላቸው ና ሳያውቁ የግብፅን ጥቅም ለማሥከበር የሚሰሩ ሆነው ሥላገኘኋቸውም ነጋችን እጅግ አሥፈርቶኛል።
ለምን አልፈራም ? እብድ፣እብድ የሚጫወቱ ፊክሺን በሆነው ብሔርተኝነት ውሥጥ የሚዳክሩ ከሂሳብ ማወራረድ ፣ ከገመድ ጉተታ ና ከሴራ ፖለቲካ በቀር የዘመነኛውን ዓለም ፖለቲካ የሚጠየፉ ፖለቲከኞች እንደአሸን በፈሉበትና በአንጉልና በህሊናው ተጠቅሞ በግሉ በማሰብ ፣ሰው ሁሉ የሚጠቀምበትን ቀና ሐሳብ የማይከተል ፣ በአንዱ እብድ መንገድ ሺዎች እሳት እየነደደ እያዩ በጭፍን በሚነጉዱበት አገር ውሥጥ እያለው መፍራት ግዴታዬ ነው።
መፍራቴን ማቆም የምችለው ፣ በግሉ ረጋ ብሎ የሚያሥብ ሰው በአገሬ ሲበዛ ነው። በአገሬ ግራ ቀኙን አይቶ ፣ፈርሃ እግዜር ኖሮት የሚፈርድ ዳኛ ሲኖር ብቻ ነው የማልፈራው ።… በአንድ እብድ ፤ ሰው መሆኑንን በካደ“ብሔርተኛ “ የማይነዳ ወጣትና ጎልማሳ በአገሬ ሲበዛ ብቻ ነው ፣ ላልፈራ የምችለወ።…
ብሔርተኝነት ያሥፈራኛል።ብሔርተኝነት ፣መለያየትን ፣ጥላቻን ፣ተንኮልን ፣ ሴራን …ከሁሉም ይበልጥ ደግሞ ሰው ሁሉ ዘሩ አንድ ያለመሆኑንን የሚሰብክ ትልቅ ፊክሺን በመሆኑ ያሥፈራኛል ።
ብሄርተኝነት በሰው ልጅ ህሊና ውሥጥ የተፃፈ ፣ በገሃዱ ዓለም ውሥጥ ልንጨብጠው የማንችል ኢ _ሣይንሣዊ የሆነ ፊክሺን ነው። ብሔርተኝነት ግለሰባዊ ማንነት ላይ ያጠነጠነ ከመሆኑም በላይ አንዳችም ታሪካዊ፣ኃይማኖታዊም ሆነ ሣይንሣዊ መሠረት የለውም።አዳሜ ና ሄዋኔ መፀሐፍ ቅዱስን እና ቁራንን አንብቢ። በሣይንሥ የምታምኝም የዳርዊንን ቲዎሪ ገረፍ፣ገረፍ አድርጊ። የዛን ጊዜ ብሔርተኝነት ፊክሺን እንጂ ፋክት እንዳልሆነ ጠንቅቀሽ ታውቄለሽ።
እንስሳትን እና ሌሎች ፍጡሮችን በመቆጣጠር የበላይ እንድትሆኚ ያደረገሽን አንጎልና አእምሮሽን የገዛ ሰውነትሽን እንዲመረምር ጊዜ ስጪውና አንቺ ዓለም አቀፋዊ እንጂ ጎጣዊ ፣ክልላዊ፣አገራዊ እንዳይደለሽ ያሥረዳሻል። ሰው ልጅ ዛሬ የሚያሥፈልገው ወደውሥጡ ማየት ነው። ወደውሥጡ ማየት ሲጀምር የአገር ድንበር ተጣሰ ሲባል በዛ ድንበር አካባቢ ያለ ወገኑ የሆነ ሰው ፣እንግልት ፣ወከባ፣ዘረፋ ሥቃይ ፣ መከራና ሞት እንደደረሰበት ይገነዘባል። ( በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት በየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ላይ የሚደርሰው ጥቃት በራሱ ላይ እንደተደረገ መቁጠር ብቻ ሣይሆን ፣ ጥቃቱ አንገብግቦት ድምፁን ያሰማል። የአቅሙን እና የሚችለውን እርዳታ ለመሥጠትም ወደኋላ አይልም።)
አገር ሲወረር ግኡዙ መሬት አይደለም የሚሰቃየው። የሚደማው ፣የሚታረዘው፣ የሚዘረፈው ። የሚሞተው ። ይህ ሁሉ የሚደርስበት ፣አገሬ ነው ብሎ በዳር ድንበሩ ላይ የሚኖረው ሰው ነው።
ይህ ሰው ደሞ ዓለም አቀፋዊ ሰው ነው።ሰብዓዊ መብት የምንለው ፣ሄውመን ራይት የምንለው ይህንን ነው።
ከአምሥት ሺ ዓመት በፊት እኛ ሰዎች ኑሯችን እንዴት ነበር ? “ ብላችሁ ብጠይቁ ሥለሰብዓዊ መብት ታውቃላችሁ።ሥለ ሥልጣኔ እና ሥለ ዛሬው ዘመን የአጥር አኗኗር ጅማሮ ከታሪክ ትረዳላችሁ።
ታሪክ እንደሚያሥረዳን ሰው ከ20ኛው ክ/ዘ ጀምሮ ነው ታላላቅ የቴክኖሎጂ ድል የተቀናጀው።ብዙም ያልዘመኑትን ዘመናት እንተዋቸውና የ19ኛው ክ/ዘ ብቻውን እንኳን የጦርነት ፣ የመገዳደል፣የአዳዲስ አውዳማ የጦር መሣሪያዎች መሞከሪያ ዘመን ነበር።” ከጥበብ መራቅ አላዋቂዎችን ይገላቸዋል። “ እንዲሊ ዛሬም እኛ በዚህ ክፍሐ ዘ ዘመን እንደሚኖሩ ሰዎች በጠላቶቻችን ስውር ሤራና የገንዘብ ደጋፍ ተረት፣ተረት በሆነው ብሔርተኝነት ፣እርስ በእርሳችን ለመገዳደል ገጀራ እንድናነሰ እየተገደድን ነው። ቆም ብለን በማሰብ ከተያያዝነው የተረት ተረት መንገድ የማነወጣ ከሆነ ራሳችንን በራሳችን ጠልፈን እንደጣልን ከወዲሂ እንወቅ።…
በፊክሽናችን እንቀጥል ወይስ ከፋክት ጋር እንጋባ ? ጥያቄው የሄ ነው? “መሆን ወይም ያለመሆን ?…ጥያቄው ይሄው ነው። “…