August 4, 2020
2 mins read

ምነው ምነው ? ( ዘ-ጌርሣም)

ጆሮ ያለው ይስማ
ላልሰሙት ያሰማ
ግልፅ እኮ ነው
ነጋሪም አያሻው

ኢትዮጵያ በችግር
ህዝቧ በቸነፈር
በሽታ ድህነት
ሲፈራረቁባት

ሲወረወርባት ከያቅጣጫው ሾተል (ጦር)
ከፊሉ ከጠላት ቀሪው ባገር በቀል
እንቅልፍ የላቸውም አዘቅት ውስጥ ሊጥሏት
አሸክመው ቀንበር እየገፈተሯት

ምነው ?

እስከ መቸ ድረስ ተዋቸው ይባላል
ግፍ እኮ ሲብዛ ወደ ላይ ይፈሳል
ምነው ለግፈኞች ህጉ መራራቱ
ቀይ መስመሩ ታልፏል በቃ አለማለቱ

ምነው ?

ይፍጨረጨራሉ አይሳካም እንጅ
መሆኗን ሳያውቁ በፈጣሪዋ እጅ

ለማን አቤት ትበል በደሏን ዘርዝራ
ማነን ስማኝ ብላ ጮህ ብላ ትጣራ
የትኛው ጠበቃ ይከራከርላት
በደሏን ዘርዝሮ ፍትህ ያስገኝላት

ምነው ?

እስኪ እግዚኦ በሉ
ኢትዮጵያውያን በሙሉ
አባት እናትነት
እህት ወንድምነት
ፍቅርና አንድነት
የሁላችን ዕሴት
በአንድ ላይ ያኖሩን
በሥጋና በአጥንት አብረው የገመዱን
እንደምን ይረሱ
የዝምድና ክሮች ለምን ይበጠሱ ?

ምነው ?

ተዋልዶ
ተካብዶ
የአብሮነትን ፀጋ በፍቅር ገንብቶ
ጦርነት ሲመጣ አብሮ ተሰልፎ
ክፉ ቀን ሲመጣም ነበር ተደጋግፎ

የታለ ? ያ ! ዕሴት !!
የሁላችንም ሀብት
ሌሎች የሌላቸው
ጥላቻና ቅናት የሚያሳርራቸው
ፈልፍለው በማወቅ ደካማ ጎናችን
ጠላት ያደርጉናል እርስ በራሳችን

ምነው ?

በቋንቋና ባህል ልዩነት በመፍጠር
በሰላም እንዳንኖር እንድንጠራጠር
አጉል ተስፋ ሰጥተው
አባብለው ሸንግለው
ግማሹን በንዋይ ቀሪውን በሥልጣን
ለማይገኝ ነገር ከንቱ ህልም ለሚሆን

ምነው ?

አገር ትፍረስ ይላል
ህዝብን ያጫርሳል
ህዝቡን ያለያያል
ከዚያም አልፍ ሲል
ለአመፅ ያዘጋጃል
የብዙሀንን ደም በከንቱ ያፈሳል
ሳይተኛ ሌት ተቀን አገርን ያምሳል

ምነው ምነው ?
የጤና ውይስ ዕ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop