ሰው መሆን ይበቃል (ዘ-ጌርሣም)

ህይወት ተገብሮ
ከአገሩ ተባርሮ
የአገር ሀብት ጨምሮ
በግፍ ተመዝብሮ
ለስደት ተዳርጎ
በአራዊት ተበልቶ
እንደ እንስሳ ታርዶ
ሳምባ ኩላሊቱ ሆድ እቃው ተሽጦ
ባሀር ውስጥ ሰጥሞ
ግፍን አጣጥሞ
በጉልበታም ዱላ አከላቱን አጥቶ
አንገቱ ተቀልቶ
የተገኘውን ለውጥ አብሮ ለመደገፍ
ሰው መሆን ይበቃል አለያም ዞር ማለት
ከመሆን አንቅፋት
ሌሎች እንዲጓዙ በአንድ ላይ የቆሙት
ዶክተር ፕሮፌሰር
ጀኔራል ኢንጅኔር
ሌላም ሌላም መባል
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እራስን ማታለል
ትርጉምም የላቸው
ቅንነት ያዘለ ዕውነት ከሌላቸው
ቅን መሆን ይበልጣል
እራስን ከመውቀስ ከፀፀት ያድናል
አብሮ ለመሻገር ግቡ ላይ ለመድረስ
የጠፋውን ጊዜ በልማት ነው መካስ
የተገኘውን ለውጥ አብሮ ለመደገፍ
እጅና ጓንት ሆኖ ውጤቱን ለማግዘፍ
ሰው መሆን ይበቃል አለያም ዞር ማለት
ከመሆን እንቅፋት
ሌሎች አንዲጓዙ በአንድ ላይ የቆሙት
ዞር ብሎ አለማየት
መውቀስ አለመቻል አራስን በፀፀት
ያስከፍላል ዋጋ ለትውልድ የሚተርፍ
መሸከም አቅቶት ሞልቶ ሲፈስ ግፍ
ይቅር የሁዋላችን
እንይ የፊታችን
ይቅርታን እናድንቅ
ፍቅርን እንሰንቅ
ከሌሎች እንማር
ደግ ደጉን ነገር
ወድቀን ከምንቀር
ወንዙን ሳንሻገር
ምስጢሩ ቀላል ነው
በደንብ ካስተዋልነው
ሰው መሆን ይበቃል አልያም ዞር ማለት
ከመሆን እንቅፋት
ሌሎች እንዲጓዙ በአንድ ላይ የቆሙት

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሥጋ ! ማስታወሻ ! -   መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share