November 26, 2013
2 mins read

ከቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የቀድሞውን የዞን አስተዳዳሪ ጨምሮ 4 ግለሰቦች ታሰሩ

Fnote

የቁጫ ህዝብ ካለፈው አመት ጀምሮ እያነሳቸው ባሉት የማንነት ፣የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ከመንግስት ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ መንግስት የጀመረውን የእስር እርምጃ ገፍቶበታል፡፡

የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዳስታወቁት በትላንትናው ዕለት ኅዳር 16 ቀን 2006 ዓ.ም አቶ ቱማ አየለ የተባሉ ቀድሞው የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና በአሁኑ ወቅት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሌክቼረር፣ አቶ ፍሬው ጳውሎስ የተባሉ ታዋቂ ባለሀብት እና አቶ እንድሪያስ ሄባና የተባሉ የቀድሞ የእርሻና እጽዋት ተመራማሪ በአሁን ወቅት ደግሞ ‹‹ሜርሲኮር-ኢትዮጵያ›› ተብሎ ለሚጠራው አለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅት የአርባ ምንጭና የአከባቢው ዳይሬክተር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በፖሊስ ታስረው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የትራፍክ ፖሊስ የሆኑት ዮሐንስ ፈረንጃ፤ ከባለፈው ዓርብ ዕለት ህዳር 13 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ትላንት ወደ አርባምንጭ ማረሚያ ቤት መወሰዳቸውም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

9957
Previous Story

በእሁዱ ታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ታላላቅ አትሌቶች በፍርሃት ሳይገኙ መቅረታቸው ተዘገበ

9968
Next Story

Video: የአንዱአለም አራጌ ታሪክ በዳንኤል ተፈራ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop