October 29, 2019
6 mins read

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አዳማ ላይ ያደረጉት ንግግር እውነት የትርጉም ክፍተት አለው!? ተከታዩን ያንብቡ

98000

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አዳማ ላይ ያደረጉንት ንግግር በተመለከተ በሶሻል ሚዲያ ሲንሸራሸር የዋለውን ቪዲዮ በተለመከተ እኔም ሁለት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማረጋገጫ ካገኘሁ በኋላ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለጽ ለመንግስት ጥሪ አቅርቤያለሁ። አሁን በውስጥ መስመር ከወንድሜ በፍቃዱ ኃይሉ የደረሰኝ ሌላ ትርጉም ደግሞ ቀደም ሲል ካለው ትርጉም የተለየ እና መሆኑን አረጋግጫለሁ። ከበፍቃዱ ያገኘሁትን ትርጉም ከዚህ በታች እንደሚከተለው አስቀምጠዋለሁ። ቀደም ሲል የለጠፍኩትንም አብራችው እንድታዩት እና ለማገናዘቢያም ይሆን ዘንድ ከገጼ ላይ ሳላጠፋ እዛው ባለበት ትቼዋለሁ። ሁለቱ ተመሳሳይ ትርጉም የሰጡኝ የቋንቋው ተናጋሪዎችም ልዩነቱን አብረው እንዲያዩት እና ስህተት ካለ እንዲያርሙት እጠይቃለሁ።

ትርጉም፤

“ከተማ ውስጥ እንዴት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃው ስላላችሁ ስለምታውቁ እያያችሁ ስለሆነ ይህንን ጉዳይ ተከታተሉልን የእኛን ጉዳይ በአጭሩ ወደኛ ዞራችሁ (እኛን እያጠቃችሁ ነው) የሚል ሃሳብ ነው ያለው።

አሁን በተነሳው ሃሳብ ላይ እንደማመጥ አሁን እሳቸው ባነሱት ሃሳብ ላይ

፩ኛ ሰኞ ጥዋት ሰዎቹ ባሉበት እንወያያለን
፪ኛ ትጥቅን በተመለከተ በቅርብ ስለመጣሁ እኔ መረጃ የለኝም። በመንደራችሁ የታጠቁ ሰዎች ከሌላችሁ ሕግ አክባሪ የሆኑ ስነ ስርአት ያላቸውን ሰዎች ተወያይታችሁበት መርጣችሁ ስም ዝርዝር ትሰጡናላችሁ መሳሪያ እንሰጣችኋለን
፫ኛ እዚህ ጥፋት የሰሩ ሰዎች ሰውም ገድለዋል እናውቃለን ስም ዝርዝር ትሰጡናላችሁ መሳሪያ እንዴት እንደተጠቀሙ እንጠይቃቸዋለን ከሕግ ውጭ ያለ ትጥቅ ካለ እያንዳንድዋን ጠራርገን እናስገባታለን።
፬ኛ ቄስ ሆነ አልሆነ ጳጳስም ቢሆን ከሕግ ውጪ የሃይማኖት አባት ከሕግ ውጭ የሆነ ነገር አያደርግም ሰው አይገልም ሰው መግደል ገነት አያስገባም። እኔ ከላይ እናንተ ታውቃላችሁ ይህንን ድርጊት የፈጸመ ሰው ካለ እጁ ያለበት ካለ ይህንን የሰበከ ቄስም ካለ ከፓትሪያርኮቹ ጋርም ተነጋግረናል እዚህ ብቻ አይደለም መሃል ከተማ ላይም ምንም ባልተፈጠረበት ደውል እየደወሉ ሰው ነቅሎ እንዲወጣ እያደረጉ ነበር እነዚህን ሰዎችን ለይተን እያወጣን ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር እናውላቸዋለን። ከዛ በኃላ ደግሞ የተወሰነባቸውን ውሳኔ የተወሰደባቸውን እርምጃ ለእናንተ እናሳውቃችኃለን ክዝህ በተረፈ ይህ ሃገር የኛ ሃገር ነው። ይህ ሃገር የኦሮሞ አገር ነው። ከሃረርጌ ብትመጡም የኦሮሞ መሬት ነው። የትም መሄድ የለባችሁም መሬቱ የናንተ ነው። ቀን ከሌሊት አብረናችሁ ነን። የሚገጥማችሁ ነገር የለም። ትናንት የተለያዩ ችግሮች ውስጥ ስለነበርን መምጣት አልቻልንም። ለሱ ይቅርታ እንጠይቃለን። ከዚህ በኋላ ያለምንም ስጋት እናንተ ስራችሁንና ኑሮዋችሁን ቀጥሉ። ሰኞ ጥዋት መጥተን እናወያያችዋለን። ከቡር (እናመሰግናችዋለን)፤ በቃ በቃ ሃሳባችሁን እንዳታነሱ”

ከወዳጄ በፍቃዱ BefeQadu Z. Hailu ያገኘሁት ሙሉ ትርጓሜ ይህን ይመስላል። በሁለቱ ትርጉሞች መካከል የሰማይ እና የምድር ያህል ሰፊ ልዩነት አለ። ለተፈጠርው ውዥንብር በእኔ በኩል ከፍ ያለ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሁለቱ ወዳኖቼ ፈቃደኞች ከሆኑ ስማቸውንም ገልጬ እነሱም እርማት እንዲያደርጉ እና አሳስተው ተርጉመውም ከሆነ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስባለሁ። ቀደም ብሎ ከቪዲዮው ጋር የተቀመጠውን ሃሳብ ከገጼ ላይ ስለማላጠፋው ሁለቱን ትርጉሞች አብራችሁ አስተያዩዋቸው።

ትርጉሙን እንደገና ቼክ እንዲደረግ ላሳሰባችሁኝ ሰዎች ምስጋናዮ የላቀ ነው።

ከታላቅ አክብሮት ጋር
ያሬድ ኃይለማርያም የመብት ተሟጋች

2 Comments

  1. ትክክለኛው ትርጉም የበፍቃዱ ኃይሉ ነው። ተመልከቱ፣ የተረገሙ ሴረኞች እንዴት ህዝብ እንደሚያሳስቱ! እንደነዚህ ያሉ ጭራቆች ናቸው ኦሮሞን እንደጭራቅ የሚስሉት! አብዛኛው ችግር የሚፈጠረው በተሳሳተ ትርጉምና አረዳድ ነው።

  2. Abba Caala Wusha,
    Just like “Ye Irgo Zimbe” in every article you rush to comment.
    Still your Qeero, or whatever their name is ARE “Chirak “

Comments are closed.

Previous Story

ክልል ነበርን፣ ክልል እንሆናለን! የአዲስ አበባ ክልላዊ መንግስት! – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Next Story

ይድረስ ለአማራ አክቲቪስቶችና የሚዲያ ሰዎች! – ይነጋል በላቸው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop