October 10, 2019
23 mins read

አዲስ አበባ እንደ ሮም ወይስ እንደ ኖርማንዲ? – ደረጀ ተፈራ (የግል ምልከታ)

፩) መግቢያ:

ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መፈጠሪያ ቦታ ለመሆኗ በሳይንስም ሆነ በሃይማኖት የተረጋገጠ ሃቅ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአርኪዮሎጂ ቁፋሮ በሚገኙ የሰው ቅሪተ አካላትና በ DNA ምርመራ መሠረት የሚሰጡ ሳይንሳዊ ትንታኔዎች የሚያመላክቱት ጥንታዊ ሰዎች የሀገራችንን ስምጥ ሽለቆ መነሻ በማድረግ በአካባቢያቸው የሚገኝ የተፈጥሮ ልምላሜንና የወንዞችን ተፋሰስ በመከተል በቅድሚያ በዙሪያቸው በኢትዮጵያ ምድርና በአፍሪካ በቀጣይም ሀገራችንን በየብስ እና ቀይ ባህርን አቋርጠው ወደ ተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እንደተሰራጩ ይገልፃሉ። በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ኤደንን ከከበቧት አራት ወንዞች መሃል አንዱ ከኢትዮጵያ የሚመነጨው የግዮን (አባይ) ወንዝ መሆኑን ይነግረናል። ፈጣሪ አዳምንና ሄዋንን ከምድር አፈር ከፈጠርራቸው በኋላ በዚሁ በኤደን ውስጥ እንዲኖሩና ዘራቸውን እንዲተኩ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዋት ብሎ እንደባረካቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። በመሆኑም በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ልጆች ሲወለዱ፣ ተወልደው ሲያድጉ፣ አድገው እነሱም በተራቸው በመውለድ ሲበራከቱ ባጠቃላይ የህዝቡ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲመጣ ለጎጆ መቀለሻ፣ ለእርሻ፣ ለከብቶች ግጦሽ ማዋያ፣ ለአደንና ለመሳሰለው የሚሆን ሰፋ ያለ ተጨማሪ ቦታ (መሬት) ማስፈለጉ አይቀርም። በመሆኑም የሃገር ድንበርና ወሰን በማይታወቅበት በዛ ወቅት የነበሩ ጥንታዊ ሰዎች በግላቸውም ሆነ በቡድን እየሆኑ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፉ ወይም እርቀው ሊሰደዱ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የሚጠበቅና ተፈጥሯዊ ክስተት ነው። የማህበራዊ ህይወት አጥኚዎች (Sociologist) ቀለል ባለ ሁኔታ እንዲህ ይላሉ: “The history of the world is the history of human migration and settlement.”  ባጠቃላይ የሰው ልጅ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሲፈልስ፣ ሲሰደድ፣ ሲስፋፋ ኖሯል። ለምሳሌ ፈረሰኞቹ ሞንጎልያዎች ከምስራቃዊ ኤሲያ እስከ መሃል አውሮፓ ድረስ በፈፀሙት ወረራ የአአካባቢውን ህዝብ በሂደት እንዲቀየጥ አድርገዋል፣ ለቻይና እንደ ሃገር መፈጠርም ከኮንፊሽየስ ቀጥሎ እንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳሉ። አውሮፓውያን ደግሞ ወደ ህንድ በመፍለስ ከነባር የሃገሩ ህዝብ ጋር በመቀላቀል አሁን ያለውን ህዝብና ባህል ሊፈጥሩ ችለዋል። በአህጉራችን ደግሞ ከምዕራብ አፍሪካ ከናይጄሪያ እና ከካሜሩን ድንበር ተራራማ አካባቢ የተነሱት የባንቱ ከብት አርቢ ጎሳዎች ወደ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ አጥለቅላቂ ፍልሰት ማድረጋቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።

 

፪) የኢትዮጵያ ህዝብ ፍልሰትና መቀላቀል (ባጭሩ)

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ ጊዜ የተደረጉ የህዝብ ፍልሰትና ስርጭት በሦስት አቅጣጫ የተደረጉ ነበሩ። አንደኛው ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ውጭ የተደረገ ፍልሰት፣ ሁለተኛው ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገ፣ ሶስተኛው ደግሞ ከአንደኛው የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል የተደረገ የሃገር ውስጥ ፍልሰት ነው። በመሆኑም  ኢትዮጵያ በአንድ በኩል የሰው ልጅ መገኛ በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ ሰዎች ተሰደው በመምጣት የኖሩባትና ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የተቀላቀሉባት ናት። ቀደምት አባቶቻችን በዚህች ምድር ላይ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ፣ በዓየር ንብረት መዛባት እና በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደዋል፣ ከአንዱ የሃገራችን ጫፍ ወደሌላው ጫፍ ተመላልሰዋል፣ በሂደቱም ህዝቦች ከህዝቦች ጋር ተደባልቀዋል። ከሃገር ውስጥ ፍልሰት እንደ ምሳሌ ለማንሳት ያህል 1) ዮዲት ጉዲት በአክሱም መንግስት ላይ የፈጸመችው ውድምት ምክንያት የንጉሳን ቤተሰቦች ጭምሮ በከተማው በተለያየ ሞያና ስራ ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የማህበረሰቡ ክፍሎች ወደ መሃል እና ደቡብ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው፣ 2) በኦቶማን ቱርክ ይታገዝ የነበረው ግራኝ አህመድ (ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም አልጋዚ) ከሃረር ( እና ከዘይላ) ተነስቶ በወቅቱ በነበረው በኢትዮጵያ የክርስቲያን መንግስት፣ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና በምዕመኑ ላይ ከ 14 ዓመት ላላነሰ ጊዜ የፈጸመው ሰፊ ወረራ፣ ውድመት፣ ቃጠሎ፣ ግድያና ዝርፊያ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የህዝብ ፍልሰት፣ ከዛም በመቀጠል 3) ቦረና እና ባሬንቱ የሚባሉ ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደር ነገዶች (Primitive Oromo pastoral tribes) ቀድመው ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ በሁለት አቅጣጫ ፈልሰው በመምጣት “በባሊ” (ባሌ) እና “መደ ወላቦ” በተባሉ አካባቢዎች መጥተው ሰፈሩ። ከጊዜ በኋላ የህዝቡና የከብቱ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ የመሬት ጥበት ችግር ስላጋጠማቸው ከጎሳ እስከ ነገድ ድረስ ቅንጅት በመፍጠር ገዳ በሚባል ባህል በመደራጀት ጎረቤቶቻቸው ላይ ጭካኔ የተሞላበት ሁኔታ በመንጋ ወረራ በመፈፀም ነዋሪውን ህዝብ ከኖረበት ቀዬው በማፈናቀል፣ በመግደል ወይም ማርኮ በማወረም (በሞጋሳ ባህል) በመሬቱ ላይ ስፈሩበት። ይህ ድርጊት ከተፈፀመ ዘመናት ያስቆጠረና ባልሰለጠነ ኋላ ቀር ጊዜ የተከሰተ በመሆኑ በታሪክነቱ መዝግቦና ትምህርት ወስዶ ከማለፍ ውጭ በዚህ ዘመን ለጸብና ክርክር ምክንያት መሆን የለበትም። እዚህ ላይ ማንሳት የምፈልገው ሌላው ነገር ግን በጥንት ዘመን የነበረው ጥንታዊ የኦሮሞ ማህበረሰብ (Primitive Oromo pastoral tribes) እና አሁን በዘመናችን በሚገኘው የኦሮሞ ህዝብ (Contemporary Oromo) መሃል የባህል፣ የአኗኗር፣ የእምነት፣ የአስተሳሰብ፣ የህዝቡ ስብጥር እና በመሳሰለው ብዙ ልዩነት አላቸው ነው

 

ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገን ፍልሰት ስንመለከት ደግሞ ከሺህ ዘመን በፊት ቀይ ባህርን አቋርጠው ከኢትዮጵያ ምድር ተነስተው ወደተለያዩ የዓለማችን ክፍል ተሰደው ከነበሩት ጥንታዊ ነገዶች ውስጥ በሄዱበት ቦታ አዲስ ባህልና ቋንቋ አዳብረው ክርበርካታ ትውልድ በኋላ በወጡበት ባል አል ማንዳብ (Bal-al-Mandab) ተብሎ በሚጠራው በቀይ ባህር ሰርጥ በኩል ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ፈልሰው በመምጣት ከነባሩ ህዝብ ጋር ተቀላቀሉ፣ ከነዚህም ውስጥ ሳባውያን ይጠቀሳሉ። ሳባውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት 1000 ዓመታት አካባቢ የኤደንን ባህረ ሰላጤን በማቋረጥ ወደ ሃገራችን መፍለሳቸው ይታወቃል።

፫) “Barbarians at the Gate” 

ሮማውያን “Barbarians at the Gate” የሚል አገላለፁ ነበራቸው። አባባሉ የቆየ ታሪክ ያለው ሲሆን በህግና ስርዓት የማይመሩ፣ ያልሰለጠኑ፣ ባዕዳን ማህበረሰቦች (Barbarians) የሮማን ከተማ በመንጋ በመውረር በከተማው ላይ ያስከተሉትን ውድመትና በነዋሪው ህዝብ ላይ የፈጸሙትን እልቂት ለመግለጽ የተጠቀሙበት አገላለጽ (Metaphor) ነው። በተለይ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ቫይኪንግ/ ኖርማንስ  (Vikings/ Normans) የተባሉ በእስካንዴኔቪያን (Scandinavian) ሃገሮች ማለትም በኖርዌይ፣ በስዊድንና በዴንማርክ ይኖሩ የነበሩ ጥንታዊ ህዝቦችን ነበሩ። እነዚህ ህዝቦች አሣ በማጥመድ፣ በአነስተኛ ግብርና፣ የባህር ላይ ንግድ እንዲሁም የባህር ላይ ዘረፋ (pirates) እየፈጸሙ ይኖሩ ነበር። የቫይኪንግ ህዝቦች በቤተሰብና በነገድ ደረጃ ተሰባስበው የሚኖሩ፣ በዛፍ፣ በተራራ፣ በመብረቅና በመሳሰለው ተፈጥሮን የሚያመልኩ ነበሩ። የቫይኪንግ ህዝቦች ጠላቶቻቸውን አድብተው በመውረር ያለምንም ምህረት ወንድ፣ ሴት፣ ህፃን፣ ሽማግሌ ሳይሉ ገለው የሚያጠፉ ጨካኝ ጦረኞች ናቸው። በዚህም የተነሳ በነባሩ የአውሮፓ ህዝብ ባዕዳን፣ ያልሰለጠኑ፣ አረመኔዎች፣ (Barbarian/ Savage/ Pagans) እየተባሉ ይጠሩ ነበር።   

 

አውሮፓውያን በጥቅሉ “Barbarian” (Foreigners/ ባዕዳን) ብለው የሚጠሯቸው እነዚህ ማህበረሰቦች ወደ ምዕራብና መካከለኛው የአውሮፓ ክፍል በተለይም ከጀርመን ምድር የራይንን (Rhine) ወንዝን በመሻገር በሮማ ኢምፓየር ላይ በፈፀሙት የመንጋ ወረራ ለሮም ስልጣኔና መንግስት መዳከም በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ መፍረስ በዋና ምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ናቸው። አረማውያን የሮምን ከተማ በመውረር የነዋሪውን ህዝብ ሰላም አናጉት፣ በከተማው ዝርፊያ ተበራከተ፣ የእምነት ተቋማት ረከሱ፣ መነኮሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ ታረዱ፣ ሴቶች ተደፈሩ ማህበራዊ እሴቶች ተናጉ። ባጠቃላይ ህግና ስርዓት ተፋለሰ፣ ከጥንት ጀምሮ ሲገነባ የመጣው የሮም የስነ መንግስት ስልጣኔና ታሪክ ፈርሶ እጣ ፈንታዋ በባርባሪያን እጅ ወደቀ፣ በየጊዜው በዙሪያዋ ከሚገኙ ገጠራማ መንደሮች በርካታ ሰው ወደ ሮም ከተማ በመፍለሱ የህዝቡ ቁጥር ከመጠን በላይ እየጨመረ መጣ። የህዝቡ ብዛት የሮም ኢኮኖሚ ሊሸከመው ከሚችለው አቅም በላይ እየሆነ መጣ። ችግሩ ጠና፣ በዚህ ላይ በባርባሪያን ዝርፊያ፣ ቅሚያና አምባጓሮ ተበራከተ፣ ስርዓት አልበኝነት ነገሰ፣ የሮም ከተማ በችግሮች ተወጠረች፣ ተወጥራም አልቀረችረች በመጨረሻም ፈነዳች! የከተማዋ ነዋሪ የሚከሰተውን ፈጣን ተለዋዋጭ ክስተት እንደ ተአምር ፈዞ ከመመልከት ውጪ ችግሩን ለማስተካከል አንድ ነገር ሳያደርግ ቆሞ ሲመለከት አይኑ እያየ ሃገሩ ፈራረሰች። ያቺን ጥንታዊት ኢምፓየር የሚታደጋት አጥታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፈራረሰች። ታሪክ ሆና ቀረጭ።

 

፬)  አዲስ አበባ እንደ ኖርማንዲ (Normandy) 

የቫይኪንግ/ ኖርማንስ የወረራ ታሪክ የራይን ወንዝን በእግርና በፈረስ በማቋረጥ በሮም መንግስትና ህዝብ ላይ በፈፀሙት ውድመትና ወረራ ብቻ አያበቃም። ነገር ግን ከእስካንዴኔቪያ አካባቢ በመነሳት በቡድን በቡድን በመሆን በትናንሽ ፈጣን የእንጨት ጀልባዎች ባህሩን እያቋረጡ አሁን ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ስፔን ወዘተ ተብለው ወደሚጠሩት የአውሮፓ ክፍሎች ከ8ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባሉት ዘመናት በመፍለስ ከቀድሞ ጊዜ ጀምሮ ይኖር የነበሩትን የሃገሩን ነባር (Native) ማህበረሰቦች በወረራ እያፈናቀሉ፣ እየዘረፉና እየገደሉ በመሬቱ ላይ ይሰፍሩ ነበር። በወቅቱ ፈረንሳይን ይገዛ የነበረው ንጉስ  ቻርለስ 3ኛ ነበር (Charles III, 893 – 922) ንጉስ ቻርለስ 3ኛ ፈሪና ተለማማጭ ስለነበረ ሰራዊቱን አሰማራቶ ሃገሩን ከጥፋት ማዳን ሲችል ከቫይኪንግ ወራሪዎች ጋር መደራደር ጀመረ። ንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ ሃገሩን ሁሉ ከሚያጠፉት መሬት ስለሚፈልጉ የጠተቁትን ያህል ለመስጠት ከቫይኪንግን መሪያቸው ጋር ባደረገው ድርድር ሰሜናዊ የፈረንሳይ ክፍለ ሃገር የነበረችውን “Normandy” የምትባል ግዛቱን በ911 እንዲሰፍሩበት አሳልፎ ሰጣቸው። (በነገራችን ላይ ኖርማንዲ በ2ኛው የዓለም ጦርነት የጀርመን ናዚ ጦር ከፈረንሳይ (allies) ጋር ከፍተኛ ውጊያ የተደረገበት የደም መሬት ነው)።

ታላቋን ሮምን በጎሳ ደርጃ የሚያስቡ ያልሰለጠኑ በመንጋ የሚያስቡ ቫይኪንጎች እንዳወደሟት ሁሉ በዚህ ባለንበት በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ፊደል ቆጥረናል የሚሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች ሳይቀሩ ሁሉ ነገር “ኬኛ” በሚል “ክፉ የዘረኝነት መንፈስ” ተለክፈው ለንደል ላይ እንደ ቃልቻ ሟርት ኢትዮጵያን አፈራርሰን የኦሮሚያ ሪፕብሊክ እንመሰርታለን በማለት ፎከሩ። በሃገር ውስጥ ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ባለቤት ኦሮሞ ነው፣ ሊላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ተከራይ መኖር ብቻ ነው፣ የራሱንም እድል በራሱ ለመወሰን ሰው መሆኑ በቂ ሆኖ ሳለ የአዲስ አበባ ህዝብ ብሔረሰብ ስላልሆነ መብት የለውም በማለት ቁጥሩ ወደ 6 ሚሊዮን የሚጠጋ የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ተሳለቁ። በእንደመር ሂሳብ ተቅለስለሰው ሃገር ውስጥ ገብተው ሲያበቁ ሃገራችንንና ከተማችን አዲስ አበባን በማፍረስ፣ ህዝቧን በመበተን ሃገር አልባ፣ ባይተዋር ለማድረግ፣ ያልደከሙበትንና ያልገነቡትን ከተማ ሊወርሱ ቀን ከሌሊት እየዶለቱ ይገኛሉ። ሰባተኛ ንጉስ ነኝ ያለን ጠቅላይ ሚኒስትራችን የፈረንሳዩ ንጉስ ቻርለስ 3ኛ “ኖርማንዲንን/ Normandy” ቫይኪንጎች ሃገሩን ሁሉ ከሚያጠፉት አሳልፎ እንደሰጥቸው እንደመር በሚል ውል በሌለው ቃላት ህዝቡን እያጃጃለ ለዘመናችን ቫይኪንግ ለሆኑት ኦነጋውያንና ጃዋራውያን ሃገራችንን እና ህዝባችንን ለባርነት አሳልፎ ለመስጠት እያደባ ይገኛል።

አዲስ አበባን አይደለም መላው ኢትዮጵያን ይታደጋሉ ብለን ተስፋ አድርገንባቸው የነበሩት አዲስ አበባ ሲገቡ ጭራቸውን ቆልፈው በሰባተኛው ንጉስ እግር ስር ተንበርክከው ፍርፋሪ ለቃሚ ሆኑ። ከኔ በላይ እሱን ስሙት አሉን። ስለሆነም ነፃነታችንን ማስከበር ያለብን እኛ እንጂ ሌላ ሰው ሊሆን አይገባውም። ስለዚህ የአዲስ አበባ ህዝብ ሆይ እራስህን ከመዋጥና ከመጥፋት አድን፣ በሃገርህ ላይ ሁለተኛ ዜጋ ሳያደርጉህ፣ የአፓርታይድ ሰለባ ስዳትሆን፣ በሃገርህ ላይ ስደተኛ፣ የበዪ ተመልካች ሳያደርጉህ፣ ተጫውተህ ካደክባት፣ አግብተህ ከወለድክባት፣ ወግ ማዕረግ ካየህባት፣ እናት አባቶችህ ዋጋ ከፍለው ካስረከቡህ ከሃገርህ ላይ እንደ እንጉዳይ ከሥርህ ነቅለው ሳይጥሉህ ለመብትህና ለነጻነትህ ተነስ። ሮም በወራሪዎች ጠፍታለች አንተም ለመብትህ ካልታገልክ አዲስ አበባም ተመሳሳይ እድል የማያጋጥማት ምክንያት የለም። ለነጻነትህ ተነስ! ተደራጅ! ታገል! “Freedom is not free”–//–

ደረጀ ተፈራ

Previous Story

ፊታችሁን ወደምስራቅ አማራ! (ሙሉአለም ገ/መድህን)

Next Story

 ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ – አገሬ አዲስ   

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop