አገርህን አትልቀቅ! ሰላም ሐበሾች! ሰላም ኢትዬጲያውያን ወገኖቼ! – ዓሣዱር ከለንደን

ወገኖቼ፦ ይህን መልዕክት ስፅፍ ከትናንት በስቲያ ከሊቢያ ሰማይ ላይ የጦር አመፀኛው የጄነራል ካሊፋ አፍታር ተዋጊ ጄት አውሮፕላኖች ትሪፑሊ አጠገብ በቦምብ ያጋዩዋቸውን ኢትዮጲያዊያን ፣ ኤርትራውያንና ሌሎች እፍሪካዊያን ስደተኞች ልብ የሚሰብር በድን በቴሌቪዥን እየተመለከትኩኝ ነው። ለዚህም የመጀመሪያ ፅሁፌ መነሻና ምክንያቴ ይኽው የአገሬ ወጣቶችና አፍሪካዊያን ወገኖቼ አሣዛኝ አሟሟት ነው።

ውድ ወገኖቼ፦ የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ለትምህርት ወደ ውጭ አገር ወጥቼ በዚያው ስደት ዓለም ገብቼ በለንደን ከተማ ኗሪ ነኝ። ከአገራችን ውጪ በሌላው አገር በገንዘብ ፣ በምቾት የውስጥ ጊዜያዊ ደስታ እናገኛ ይሆናል። ዋናው ሰላምና የመንፈስ እርካታ ግን ሁሉም በአገር ነው ከሚሉት ወገን ነኝ።

ምሣሌ ልጥቀስ፦
በአሁኑ ጊዜ እኔ በምኖርበት በለንደን ከተማ እኛ ጥቁሮች በየቀኑ ለልጆቻችን በሰላም ውሎ መግባት በከፍተኛ ጭንቀትና ሃሣብ ላይ ነን። ለምን ብትሉኝ በየቀኑ እስከ ሁለት ወጣቶች በመሰል ጥቁር ወጣቶች ፀብ የእርስ በርስ የጩቤ ውጊያ ይሞታሉ።
ባይገርማችሁ ታላቅ የሚባለው የእንግሊዝ አገርና መንግስት በሌሎች አገሮች ሰላምን አሰፍናለሁ እያለ ላይ ታች ሲባዝን በBBC ማየት የተለመደ ነው። በሌላ በኩል ላለፉት ዓመታት በለንደን ጎዳና በእርስ በርስ ፀብ እንደ ቅጠል ለሚረግፉት ከ16 እስከ 19 ዓመት ላሉ የአገሬው ዜግነት ላላቸው አብዛኛው ጥቁር ወጣቶች የጩቤ ውጊያ ወይም knife crime ዕልቂት ስርነቀል መፍቴህ እስከአሁን አለማግኘቱ በዓለም ደረጃ እንደመንግስት ያሣፍራል። አለያም ለጥቁሮች ሕይወት ፍፁም ግዴለሽ መሆንን ያሣያል። በተለይ የእኛን የጥቁሮች ሕይወትም አደጋ ላይ ጥሎ ይገኛል። Really Black Lives Matter?

ውድ የኢትዮጲያ አገሬ ወጣቶች፦ አገራችሁ ኢትዮጵያን አትልቀቁ ፣ አትሰደዱ ፣ ከሁሉም በላይ ኢትዮጲያ የእናንተ ናት ፣ ሣትፈልጉ ተወልዳችኋባታልና በዘር ፖለቲካ ብትማገዱም፣ ወደአልተወለዳችኋባቸው አገሮች ስትሸሸሹ ትደፈራላችሁና ፣ ትዋረዳላችሁና ፣ በባርነት ቀንበር ትወድቃላችሁና ፣ እንደ ትናንት እንደሊቢያው ባልጠበቃችሁት ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ትቃጠላላችሁና ፣ ትታረዳላችሁና ፣ ኢትዮጵያዊነት ሣስቶ ዘረኝነት በአገራችን ቢገንም ጊዚያዊ ነውና ፣ እናት አገራችሁን ኢትዮጵያን የባሰም አለና አትልቀቁ። አትሰደዱ ፤ ዘረኝነትን ተፋለሙ ፤ እምቢ በሉ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: በኢትዮጵያ ቪያግራ ገበያ ደርቷል፤ * የቪያግራ ተጠቃሚዎች ሊያውቁት የሚገቡ እውነታዎችና ጥንቃቄዎች

ወገኖቼ፦ በሰሞኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ አትደናገጡ ፤ ተስፋ አትቁረጡ ፤ ሁሉም ነገር ለበጎ ሊሆን ይችላልና በኢትዮጵያ አንድነትና በኢትዮጲያዊነት ተፋቀሩ ፤ ዘረኝነትን ተፋለሙ። በተለይ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጲያዊነት ቅንነት ፣ ደግነት ፣ አንድነት ፣ ከእኔ አንተ ትብስ የመረዳዳት መንፈስ ፣ ከፍፁም ዘረኝነት የመንጣት መንፈስ አንገብጋቢና አስፈላጊነት ወሣኝ ስለሆነ ትኩረት ስጡት። እዚህ ላይ የሚከሰት ቸልተኝነትና ማቅማማት በኮንጎ ፣ በሩዋንዳ ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ፣ በማሊና በመሣሰሉት አገሮች እንደታየው ጥቁር በጥቁር ላይ መዝመትና መተላለቅ እንደሆነ ይቀጥላል። በዚያ ብቻ አያበቃም ፤ ጥቁር ወጣቶች አውሮፓ በዕድልና በስደት እንደለንደን ያለው ከተማ ቢደርሱ እንኳን ከላይ እንደጠቀስኩት የመንግስት ትኩረትን ያጣ የጥቁር ወጣቶች የጎዳና ላይ የጩቤ ውጊያ ስጋት እድሜን ያሣጥራልና ተከባብሮ በፍቅርና በሰላም በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጲያ መኖር መታደል ነው እላለሁ።

ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ!

2 Comments

  1. በሊቢያ የወገኖች ሞት ምክንያት በማድረግ በጻፉት አስተያየት ውስጥ በሎንደንም ስለሚጠቁ ወጣቶች ያስተላለፉት ምክር-አዘለ መልዕክት መልካም ነበር፡፡ ግን ወጣቱ ቢመከርም ስለማይሰማ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡ በአገራችን ሁኔታ የህዝቡ ሞራል በመውደቁ ወጣቱ የሆነው ይሁን እያለ ከአገሩ እየወጣ ጭካኔ በተሞላው መልክ እየተገደለ፤ ባህር ውስጥ እየሰመጠና በየዱሩ በአውሬ እየተበላ ያሰበበት ሳይደርስ በየመንገድ ላይ የሚቀር ብዙ ወጣቶች ለወላጆችና ለአገሩ ለሚቆረቆር ህዝብ ከአዕምሮ የማይጠፋ ሃዘን ሆኖበታል፡፡
    በዚህ ነገር ጥናት በማካሄድበት ወቅት እንደደረስኩበት ከሆነ ተሰፋ መቁርጥ፤ውጭ የሚኖር ዲያስፖራ ለጉብኝት እየሄደ ሲዝናና በማየት የውጭው ዓለም ኑሮ ቀላል እየመሰለውና ጥቂቱም ለባህር አሻጋሪ ደላሎች በዶላር ስለሚከፈልላቸውና ወዘተ…ነው፡፡ይህን በተመለከተ መንግሥት የወሰደው እርምጃ ምን እንደሆነ የተሰማ ነገር የለም፡፡
    ተሰድደው በሚኖሩበት የባዕድ አገር ከተማ ስለሚገደሉት ወጣቶች በተመለከተ በመሠረቱ ጸሐፊው የሚኖሩበት ለነደን “ጥቁርና እስፕሪንግ ተጭነው ካልያዙት ተስፈንጠሮ አፍንጫ ይመታል” ብሎ በሚያምን አገር ውስጥ ይህ ነገር ቢፈጸም አያስገርምም፡፡የጥቁር ወጣቶች መገደል በሎንደን አገር ብቻ ሳይወሰን የጥቁር ህዝብ ነጻናት አለ ተብሎ በታወጀበትና ለሰው ልጅ መብት መከበር ቆሜያለሁ በሚሉ አገሮች ውስጥ የሚሞተው ወጣት ስፍር ቁጥር የለውም፡፡
    ይህም በመሆኑ ወንድ ልጆች ያላቸው ወላጆቻቸው በእጅጉ ግራ ተጋብተዋል፡፡ያም ሆነ ይህ የአገራችን ሁኔታ ውሉ የጠፋበት ድር በመሆኑ ለእኛ ኢትዮጵያውያን በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ የተመቸን ነገር የለም፡፡ በቸር ይግጠመን፡፡

  2. In the diaspora me and my family are making relentless efforts by making example of many Ethiopians that tried to live in the diaspora to feel the unnecesity of migrating,by persuading them not to come or even after they come to MEDEMER and go back to Ethiopia,we intentionally make life hard on the new arrivals or potential migrants right at first when they arrive or right when they are about to leave Ethiopia to diaspora, that way they tell others the hardship of life in the diaspora and persuade others not to come. We get them to suffer as much as possible so they discourage others from migrating and they themselves go back to MEDEMER.

    Whenever people show up to diaspora from Ethiopia for short term vacation , for trainings/education or other short term visits we diasporas should show them the bad side of life in the diaspora rather than buying them so many expensive gifts,we do them a favor by showing them hardships in the diaspora , so that way, they themselves and others they talk to in the future will be discouraged from migrating.

Comments are closed.

Share