” ጠዋት ወጥቶ ፣ማታ መጥለቅ ” (በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ)

ሰው ነኝ።  ፈጣሪ ፍቃዱ ከሆነ እንደጀንበሯ ፣ጥዋት  ወጥቼ ማታ ልጠልቅ እችላለሁ ። ሌላውም እንደእኔ ሰው ነው። ህይወቱም የምትሰነብተው እድለኛ ከሆነ ፣ከጀንበር ፍንጥቀት እስከሥርቀት ነው ።
   “የሱም ሆነ የኔ ሰው መሆን ነው  እንጂ ዋናው ቁም ነገሩ  ሌለው  በዘመን ውስጥ ሰዎች የፈጠሩት ኮተትና ቆዳ ማዋደድ  እኔን አይመለከተኝም ። (ቋንቋ፣ዘር፣ጎሣ ኃይማኖት፣ ወዘተ ።)” ብዬም ፣አምናለሁ ።  ይህ እምነቴ  “ሁሉ ሰው ዘመዱ ።”ያሰኘኛል።  ከሁሉም ሰው ጋራ ተግባብቼ  ለመኖር የቻልኩትም በተአምር አይደለም ።ሰውን በሰውነቱ ብቻ በመቅረቤ እንጂ ነው።
   የዓለም ሰው ሁሉ  በሰውነቱ  አንድ ነው ። ቆዳው ይለያይ እንጂ የወል መጠሪያው ሰው ነው። ይህ ሰው በመባል የሚታወቀው፣የተለያየ የቆዳ ቀለም ከፈጣሪ የተለገሰው ፣ የዓለም ህዝብ በሙሉ ፣ ወንድሜና እህቴ ነው። ብዬ የማምን  ነኝ። አምኜም ቋንቋው ሣይገድበኝ በወዳጅነት ቀርቤ ና ቀርቦኝ ፣ቋንቋውን ባልችል  እንኳ በምልክት ቋንቋ ፍቅሬን ና አክብሮቴን ገልጬ ከተግባባው ምን እፈልጋለሁ???
 ሲጀመርም የዓለም እውነት ይኸው ነው። … በየሀገሩ የተለያየ ባህል ቋንቋ ና ሀይማኖትን በዘመን እርጅና ውስጥ የፈጠሩትም የትላንት እህትማማችና ወንድምማች ሰዎች መሆናቸውን አንካድ !!!
       በኢትዮጵያ አማርኛ ብቻ አንደበቱ የሚናገር ሆኖም ኦሮምኛ ቋንቋ ከሚናገሩ የተወለደ ግለሰብ  “እኔ እኮ !”ብሎ ኦሮሞነቱን  በአማርኛ ማስረዳት ቢጀምር ሰሚ የሚያጣው ካለን አፍቅሮተ ቋንቋ የተነሳ ነው።
      ይህ ጽሑፍ ሰዎች፣ ቋንቋ ሳይሆኑ ፣ ሰው መሆናቸውን ተገንዝበው ከሁሉም ሰው ጋር በፍቅር እንዲኖሩ ጥቂት የብርሐን ፍንጠቂ በጨለመው መንገዳቸው ላይ ለማኖር ታሥቦ የተሰናዳ ነው።ሰው ሁሉ ምሥኪን ተራ ሟች መሆኑን እንዲያሥተውል ለማድረግ።
  (ምሥጋና ለዘሐበሻ “የድር መረብ ጋዜጣ ” ምሥጋና ይሁንና…)
     አማራ፣ኦሮሞ፣ ትግሬ ፣ ደቡብ  ኢትዮ ሱማሌ ፣ደቡብ  ውስጥ ካሉትም ጎሣ ነኝ ከሚሉት የአንዱ አይደለሁም ።   ዘግይቶም ሆነ ፈጥኖ ወደመቃብር የሚገባ ሰው ነኝ።  የህይወት  ጉዞዬ እንደሁላችሁም  ከጀንበር ፍጥቀት  እሥከ ሥርቀት ነው ። ዘግይቶም ሆነ ፈጥኖ  ከአፈር በመሠራቴ ወደአፈር የምመለሥ ።
  ሁላችሁም እን’ደኔ ናችሁ። የምንበላው ሁሉ ከአፈር የተገኘ ነውና አፈር አይደለንም ለማለት አንችልም።  ሁላችንም ሥንበላት ለኖርናት አፈር  በመጨረሻ  ሥጋችንን ና አጥንታችንን  እንገብራለን።
   “…ምንም ብንጓጓለት ብንስገበገብለት፣ይፈርሳል በግዜይቱ ሥጋ ነውና ከንቱ።…” ብላ እንዳዜመችው አፈር የሆነችው ብዙዬ ነገ ሁላችንም አፈር፣ወይም አመድ እንሆናለን።-(አሥከሬን አቃጣዮች ሥላሉ ነው – አመድ ያልኩት።!)
    ጥላሁን ገሠሠም    “ሀብቴ ተርፎ በዝቶ ብዙ ቢያደረጀኝ፣ሥሞት ሥንቅ አይሆነኝ ኋላ ምን ሊበጅኝ??? ” በማለት   ” እራቁታችንን ወደአለም መጥተናል ከአለምም አንዳች ይዘን አንሄድም ። ” በማለት አዚሟል። እነዚህ በድምፃቸው ወርቅነት የማንረሳቸው ከያንያን ፣እውነቱን ቢያሳውቁንም ፣ሁሌ የሚሞተው በሬሣ ሣጥን ውሥጥ ያለው አሥከሬን ይመሥለናል። “…ሰው ሞኝ ነው ተላላ፣ይጨነቃል ለሀብቱ— ነገ ትቶት ለሚሄደው  ወደ ማይቀረው ሞቱ። “
   ይልቅስ ሰው  መጨነቅ ያለበት ፣ለሀብቱ ሳይሆን ከሱ ሞት በኋላ ሀብትና ንብረቱን ለሚረከበው ትውልድ ነው።
    ሀብትና  ንብረቱ የተገኘው በሌብነት ከሆነ ፣ትውልዱ የሚኮራበት አይደለማ።የማይኮራበት ሀብት ደግሞ መቅኖ የለውም።ባክኖ ነው የሚቀረው።የሰው ደም፣እንባና ሰቆቃን በውሥጡ ያከማቸ የግፍ ሀብት  የኋላ፣የኋላ የማንም ሲሳይ ነው የሚሆነው።
     አንዘናጋ ! ህይወት አጭር ናት። በዚች አጭር ህይወት ፣የግፍ፣የሥርቆት ና የዘረፋ ሐብት ፣በማከማቸት ለልጆቻችን መከራን አናውርሥ። ዘመድ አዝማዱም አይፈርብን። ለዚች ጠዋት  በብርሃን ደምቃ፣በቀትር ሞቃ፣በማታ ቀዝቅዛ  ፣ በጭለማ ጨልማ ፣ አካላዊውን  ሥጋ በምድር ጥላ  ፣ ህይወት የምንላት ነፍሥ ወደ ሠማያዊው ሠማይ ትነጉዳለች  ።
የጀንበር ጉዞ ና ህይወት
ያ -የጀንበሪቱ፣የስርቀት ውበት፣
ያፈዘኛል ያ -ልዩው ፍካት፣
የከሰል ፍም አይነት…
ልብን የሚያሞቅ ድምቀት፡፡
——————————
ይመስጣል፣ የማታ ጀንበር ውበትዋ፣
ስትጠልቅ የምናስተውለው፣ደም ግባትዋ፡፡
ህሊናን የሚያሸፍተው ማራኪ ብርሃኗ፣
እንድናያት ግድ የሚለን ወርቃማ ጨረሯ፡፡
“የአትሸኙኝም ወይ? “የማታ ግብዣዋ፡፡…
የታጀበው በውብ ፈገግታዋ፡፡…
———————————-
ፍዝዝ ብዬ ሳስተውለው፣እባባለሁ፣
በሀሳብ ባህርም ለደቂቃ እሰምጣለሁ፣
በማያቋርጥ ፍልስፍና ውስጥም እገባለሁ፣
በሃሳብ እልም ብዬ እጠፋለሁ፣
የጀንበርን ጉዞ ፣ ከህይወት ጋራ አመሳስላለሁ፡፡
————————————————-
“ጀንበር ለእኛ ብርሀኗን ስትነፍገን
ለሌሎች ደግሞ እንደምታበራ፣
ህይወትም ከህይወት ተጎዳኝታ፣
ሌላ ህይወት እንደምታፈራ፣
እንዲሁ ነው……….
እዛኛው ቤት፣ልጅ ሲወለድ፣
እዚህኛው ቤት፣እናት ሞታ …
እዚህኛው ቤት፣የሠርግ ድግስ፣
እዛኛው ቤት፣ለቅሶ እሪታ…
እዚኛው ቤት፣እፍኝ ቆሎ፣
እዛኛው ቤት ትልቅ ቅልጥም
ሁሌ ቡፌ…”ዶሮ ፋንታ! “
————————
ህይወት ሁሌም እንዲሁ ነች …
በተቃራኒ እውነታ የተሞላች፡፡
እስቲ ለአንድ አፍታ፣እናስተውላት፣
ለደቂቃ ቆም ብለን፣እንመልከታት፡፡
————————————–
‹‹ ሞትና  – ህይወት »
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ!
በጨለማና በብርሃን ይመሰላሉ፣
በተቃራኒ እውነታ፡፡
ጨለማን ማንም አይወደውም፣
ተንኮልና ሸርን መጠንሰሻ፣
በመሆኑ የሞት ጓዳ፡፡
በሱ ተሸሽጎ እኮ ነው…
ሰው ለጥፋት የሚሰናዳ፡፡
—————————————
እርግጥ ነው፡፡…
ሰው ጨለማ ለብሶ አምሳያውን ቢያጠፋ፣
እሱም ፀሐይ ሳትጠልቅ ነው፣በአፍጢሙ  የሚደፋ፡፡
ምንም ቢያልም በግፍ ለመክበር ፣ህይወቱ  አጭር ናት፣
(ከጀንበር ፍንጥቀት –እሥከሥርቀት ፣አጭር  የዞንጋታ ጉዞ ።)
ኑሮዋ፣ በሐዘን፣በፍቅርና በጥላቻ፣ደምቆ የምናያት።
 ኳታኝ ናት ሁሌም፣ከፀሐይ ፍንጥቀት እስከ ሥርቀት፣
ጧት ተጥዳ፣ማታ የምታከትም ናት የኛዋ ህይወት፡፡
——————————————————
አንድ ቀን ናት  የኛ ህይወት፣
ጣፋጭ ሆና ሥቃይ ያየለባት ፡፡
የቀዝቃዛ፣የለብታ፣
የግለት ፣የሞቅታ፣
የስከነት፣ የእረጋታ፣
የአንቅልፍ፤ የእፎይታ፡፡
እንደዛች ጀንበር፣አጭር ጉዘት፣
ከጎህ መቅደድ ፣እሰከ ጀንበር ሥርቀት፡፡
1983 (በደሌ)
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ታማኝ በየነ በኢሳት 3ኛ ዓመት ላይ ያደረገው ንግግር (Video)

3 Comments

  1. Receiving a stolen merchandize is both morally and legally wrong. If I see my cell phone or my vehicle that was stolen from me in somebody else’s possession I will do whatever it takes to get it back . That is what we Oromos are doing . Finfinne was stolen from us and we are taking it,After we take Finfinne back we will decide what we do with the people, be it foreigners or other Ethiopians we will let them stay if they live by our terms if not we kick them out and there is nothing you can do about it. Addis Ababa youth we seen them, they are weak they are no match for Oromia youth.One Oromia youth can chase hundred Neftegnas out of Finfinne. Eskinder Nega admitted by saying “we are powerless to them. We cannot do anything but cluck cluck cluck Sky fell cluck . That is right you are all chickens . Unless you are the once that stole the punishment for receiving a stolen city is not that severe.

  2. EFFORT CONTROLS FIFTY PERCENT OF Ethiopian economy. Meaning we Tigraians can afford to live like Libyans if we want. We can afford to live anywhere in the country while our money works for us. We donot even need to work if we choose to, we can live better quality of life just from our income through EFFORT , we can watch the working class the 80% Ethiopians Amaras and Oromos start working while we rest from the hard work we have done since 1991.

    Tigraians should know that each of us own EFFORT .

  3. You are not human .I haven’t seen any humanity in your ideas . I think you are not Ethiopian . Your game and agenda’s is clear . “the Tuse and Hutu game and agneda .
    “The dog barking in any door becus of food.” I known man is social animal’s .

Comments are closed.

Share