አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አገኘ

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉትና ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ይሟሉልኝ በማለት ለፍርድ ቤቱ ያመለከቷቸው አቤቱታዎች ነበሩ።

https://www.youtube.com/watch?v=9K1EwuewSOA

ከነዚህ መካከል በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት የጀመሯቸውን ስራዎች ከማረሚያ ቤቱ እየወጡ ለማከናወን የተወሰነ ጊዜ እንዲፈቀድላቸው፣ መጽሐፍትና መጽሔቶች ማረሚያ ቤት እንዲገቡላቸው መጠየቃቸው ይገኝበታል፡፡ ተከሳሹ የግል ኩባንያ የቦርድ ሰብሳቢና ስራ አስኪያጅ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ትልልቅ አገራዊ ጉዳዮችን ለማከናወን ውጥን ስራዎች ጀምረው እስከተያዙበት ዕለት ስራ ላይ እንደነበሩ አስረድተዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ 15ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ተከሳሹ ያቀረቡትን አቤቱታ አድምጦ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህ መሰረት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እንደማንኛውም የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪ ማረሚያ ቤት መቆየት እንዳለባቸው ገልፆ ነገር ግን በአቤቱታቸው መሰረት ውጥን ስራዎቻቸውን ለመፈጸም የሚፈልጓቸውን ሰዎች ዝርዝር አሳውቀው ለአንድ ወር እንዲያገኟቸው ፈቅዷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጅንካ ከተማ ወጣቶች ከአንድነት አባላት ጋር በመቀናጀት እየቀሰቀሱ ነው
Share