የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል

የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው 

በጉራጌ ዞን የሶዶ እና የሚቄ ማዕከል የወረዳ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ያደነቀው ጉህን ‹‹የጉራጌን ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የዴሞክራሲ ስርዓት ከማስፈን አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡›› ብሏል፡፡ ይሁን የመስቃን ማእከል ወረዳ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ጥያቄ እንዳላቸው ገልፆ ‹‹በተመሳሳይ መልኩ ሰላማዊ እና ህጋዊ በሆነ መልኩ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ተደርጎ በአፋጣኝ እንዲወሰን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፡፡›› ሲል አስረድቷል፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=9K1EwuewSOA

ጥያቄ የጠየቀ አንድም ጉራጌ መጠቃት እንደማይገባው ያሳሰበው ጉህን ጨምሮም ‹‹ለሀገር ሰላም የሚሰራው የፌደራል መንግስትም ይሁን የክልልና ዞን አመራሮች በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት ያስፈልጋል፡፡›› በማለት ገልጿል፡፡

 መግለጫው በመቀጠልም ‹‹ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያማከለ ስርዓት እና ህግ እስካልተዘረጋ የጉራጌን ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ህዝቦች ጋር በእኩልነት እና በአንድነት ሊመለስ እንደሚገባ ጉህን ያምናል፡፡

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ሀገርን መገንባት አዳጋች ከማድረጉም በተጨማሪ ለአንዱ የፈቀደውን ለሌላው የተፈቀደለትን ስርዓት መዘርጋት የህዝብን ፍላጎት እና ብሶት እንደማፈን ስለሚቆጠር መንግስት በአፋጣኝ ህዝባዊ መሠረት ያለው ምላሽ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ህዝቦች ሊሰጥ እንደሚገባ ጉህን ያሳስባል፡፡›› ብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር ሙሉ ነጋ ያወጡት ጉድስለጀነራሎችና ስለመቶ ቢሊየን ብሩ ያልተሰማ ሚስጥር
Share