ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡
https://youtu.be/epx_GOJUaUQ
በሁለቱ ኩባንያዎች መሀከል ስምምነቱ የተፈፀመ ሲሆን የዋይፋይ አገልግሎቱ ሲጀምር በአለም አቀፍና በአገር ውስጥ በረራዎች የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም አለም አቀፍ ንግድ ኦፊሰሩ አቶ ሰይድ አራጋው ለካፒታል ጋዜጣ ሲናገሩ ‹‹ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ስምምነት ከፈፀምን በኋላ ለአገልግሎቱ ሳተላይት የሚያቀርብልን አለም አቀፍ ኩባንያ እያነጋገርን ነው›› ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም ኢትዮ ቴሌኮም እንደአዲስ ባቋቋመው በዚሁ አለም አቀፍ ንግድ ዲፓርትመንት አማካኝነት ከታዋቂ አፕሊኬሽኖች ጋር እየተደራደረ መሆኑን ኦፊሰሩ አስረድተዋል፡፡ ከእነዚህ አፕሊኬሽኖች መሀከል ፌስቡክና ዋትስ አፕ እንደሚገኙበት አቶ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም ከ27 አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የድምፅ አገልግሎትን በተመለከተ ስምምነት የፈፀመ መሆኑን የተናገሩት ኦፊሰሩ በቅርቡ ደግሞ በፊት በነፃ የነበሩት የፌስ ቡክና የዋትስ አፕ የፅሁፍ መልእክቶች ላይ አፕሊኬሽኖቹ እንዲያስከፍሉ ለማድረግ በድርድር ላይ መሆናቸውን ለካፒታል ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) አራተኛ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ
Share