የክፍለ ከተማው ባለስልጣን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ ይዘው ተሰወሩ

በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር የኮንስትራክሽንና ህብረተሰብ ተሳትፎ ፅ/ቤት ሓላፊ የነበሩት አቶ አለም ገ/ሚካኤል ገንዘብ ይዘው ተሰወሩ፡፡ የካ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ግለሰቡ ከህብረተሰቡ ለልማት ስራ የተሰበሰበ 2 ሚሊየን 70 ሺ ብር ከባንክ አውጥተው ተሰውረዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ፅህፈት ቤቱ አስታውቆ ህብረተሰቡም አስፈላጊውን መረጃ እንዲስጥ ጠይቋል፡፡ የምርመራ ዉጤቱን እየተከታተለ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እንደገለፀ ከየካ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ በቅርቡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከለውጡ ጋር የማይሄዱ ያላቸውን በርካታ አመራሮች በማንሳት አዳዲስ አመራሮችን እየተካ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ “የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ መፅሃፍ፡-
Share