ከሜቴክ የተነጠቁት የህዳሴ ግድብ ስራዎች ለቻይና ኩባንያዎች ተሰጡ

ከሜቴክ የተነጠቁት የህዳሴው ግድብ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ገጠማና ሙከራ፣ እንዲሁም የብረታ ብረት ሥራዎች ለቻይና ኩባንያዎች ተሰጡ፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ስራውን ለመስራት ሀይድሮ ሻንጋይ የተሰኘው ኩባንያ የ77 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8
ድርጅቱም ለህዳሴ ግድቡ ስድስት የተርባይን ጀኔሬተሮች ግንባታና የተጓደሉ ዕቃዎችን ለማቅረብ፣ የተከላ፣ የፍተሻና የሙከራ ሥራዎችን ለማከናወን ተስማምቷል፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የቮይት ኃይድሮ ሻንጋይ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ታንግ ሹ በአዲስ አበባ እንደተፈራረሙ ከመሥሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዳሉት፣ የተጓተተውን የግድቡን ግንባታወደ ቀድሞው ፍጥነት ለመመለስ ከኩባንያው ጋር የተደረገው ስምምነት ወሳኝነት ከዚህ ስምምነት ቀደም ሲልም ፓወር ቻይና ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የኃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ግንባታ ለማከናወን፣ የ125.6 ሚሊዮን ዶላር የግንባታ ስምምነት መፈራረሙ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የኮንትራት ስምምነቱ የተከናወነው የውኃ መቀበያአሸንዳዎችንና የመቆጣጠሪያ በሮችን፣ እንዲሁም የ11 ኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን የዲዛይን፣ የአቅርቦት፣ የገጠማ፣ የፍተሻና የሙከራ ሥራዎች ለማከናወንከኩባንያው ጋር ስምምነት እንደተደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  You oughta know my name by now, better think twice
Share