በጎንደር መከላከያውን በመቃወም ሰልፍ ተካሄደ

January 9, 2019
4 mins read
93607

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳ ውሃ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በትላንትናው ዕለት ካለምንም ትዕግስት በከፈቱት ተኩስ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸው እና 15 መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን ይህን ድርጊት በመቃወም ዛሬ በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል:: ሰልፈኞቹም በአካባቢያቸው የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት ከስፍራው ለቅቆ እንዲወጣ በምሬት ጠይቀዋል::
https://www.youtube.com/watch?v=pKU8igiCV3I&t=500s

የጀርመን ድምጽ ያነጋገራቸው የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ አንድ የዓይን እማኝ እንደተናገሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በነዋሪው ላይ ተኩስ የከፈቱት በነዋሪዎች ታግተው የነበሩ የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ተሽከርካሪዎችን ለማስለቀቅ በሚል ነበር። “የመከላከያ ሰራዊት የእሩምታ ተኩስ ተኩሶ ጉዳት አድርሷል። ባለኝ መረጃ መሰረት ህጻናትን ጨምሮ ወደ 15 ገደማ የሚሆኑ የቆሰሉ ሲሆን የሟቾቹ ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል” ሲሉ እኚሁ የከተማይቱ ነዋሪ ተናግረዋል።

የሞቱትም ሆነ የተጎዱ ሰዎች ወደ ገንዳ ውሃ መተማ ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚናገሩት የዓይን እማኙ ከማቾቹ ውስጥ የስድስት ሰዎችን አስክሬን መመልከታቸውን ገልጸዋል። “እኔ ስድስት ሰዎች ተመልክቻለሁ። እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት እስከነበርኩበት ድረስ ከገንደ ውሃ ከተማ አንዲት ህጻንን ጨምሮ ሶስት ሰዎች፣ ከኮኪት ከተማ ደግሞ ሶስት ሰዎች ነበሩ” ሲሉ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ከቆሰሉት ውስጥ በእርሻ ስራ ላይ ቆይተው ሲመለሱ የነበሩ የቀን ሰራተኞች አሉበት ብለዋል።

የገንደ ውሃ ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊትን እርምጃ በመቃወም ዛሬ አደባባይ ወጥተዋል። ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ በዘለቀው ተቃውሞ ይሰሙ ከነበሩት መፈክሮች ውስጥ “የወህሓት መከላከያ እኛን አይወክልም፤ በፍጥነት ይውጣልን”፣ “በአማራነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ይቁም” የሚሉ እንደሚገኙበት ከሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች አንዱ ተናግረዋል።

ሰልፈኞቹ ትላንት ወደ ኮኪት ከተማ እንዲወሰዱ የተደረጉት የሱር ኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች ወደ ገንደ ውሃ ከተማ እንዲመለሱ እንዲደረግ እና አስፈላጊውን ማጣራት እንዲደረግባቸው መጠየቃቸውን የከተማይቱ ነዋሪ ገልጸዋል። በተቃውሞ ምክንያት ከአዘዞ እስከ መተማ የሚዘልቀውን አውራ ጎዳና መዘጋቱንም ጨምረው አስረድተዋል። ለተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ምላሽ ለመስጠት የአካባቢው አስተዳደርም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች በስፍራው አለመገኘታቸውንም አክለዋል።

93604
Previous Story

የሽሬ ትግራይ ወጣቶች መከላከያውን ይቅርታ ጠየቁ

93610
Next Story

“ለአመታት የተሰራበት ስለሆነ፣ እንዲሁ በአጭር ቀናትና ሳምንታት አዲስና በጣም መሰረታዊ ለውጥ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅም አልነበረም” – ጀነራል አሳምነው ጽጌ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop