የሽሬ ትግራይ ወጣቶች መከላከያውን ይቅርታ ጠየቁ

በትናንትናው ዕለት ከ20 በላይ የመከላከያ ሠራዊት ከባድ መኪኖችን መንገድ ዘግተው አላሳልፍም በማለት ሽሬ ስታዲየም ውስጥ ወታደራዊ መኪኖቹ እንዲያድሩ ያስገደዱት የከተማው ወጣቶች በዛሬው ዕለት ከመከላከያው ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ::
https://www.youtube.com/watch?v=pKU8igiCV3I&t=500s

ትናንት የትግራይ ወጣቶች በመከላከያው መኪና ላይ ጭምር በመውጣት መከላከያውን ሌባ እያሉ እየተሳደቡ መንገድ መዝጋታቸው አግባብ እንዳልሆነ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገልጸው ነበር:: ” የትግራይ ህዝብ ህጋዊ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ ሳይረበሽ በልማቱ ላይ ሊያተኩር ይገባል:: የመከላከያ ሰራዊት ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ ህጋዊ ኃላፊነቱንም ለመወጣት እንዲችል እንቅስቃሴው ሊረበሽ አይገባም ” ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን የትግራይ ሕዝብ የሚያነሳው የህገ-መንግስት ይከበርልን ጥያቄ እራሱ ከማክበር የሚጀምር መሆኑንም ተናግረው ነበር::

” የክልሉን ሰላምና ጸጥታ የማስከበርን ጉዳይም ህዝቡ በፈጠረው አደረጃጀት አንድነቱን ማስቀጠል አለበት::” ያሉት ዶክተሩ አያያዘውም የገና በዓል ዕለት ስለተከፈተው የኢትዮ ኤርትራ ኦምሃጅር ጎንደር መንገድ ተናግረዋል:: “የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ባደረጉት የጋራ ስምምነት የሁመራ ኦምሃጀር መንገድ መከፈትም ለሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ጠቃሚ ነው:: መንገዱ የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማሳደግ ባለፈው ቀጣይ ህጋዊ መስመር ለማስያዝም ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል” ብለዋል::

በትናንትው ዕለት በሽረ ከተማ ወደ ሀዋሳ በማምራት ላይ የነበረ የመከላከያ ሰራዊት ኮንቮይ ላይ መንገድ የዘጉ ወጣቶች፣ ከመከላከያ ሀላፊዎች ጋር ዛሬ በተወያዩበት ወቅት ወጣቶቹ መከላከያው ላይ መንገድ በመዝጋታቸው እና በመሳደባቸው ይቅርታ መጠየቃቸውን ሰምተናል:: ከስፍራው የመጡ መረጃዎች እንደሚሉት ወጣቶቹ ከመከላከያው ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ በሽሬ ስታዲየም ያደሩት ወታደራዊ መኪኖችና ከባድ መሳሪያዎቻቸው እንዲንቀስቀሱ ተስማምተዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡነ ሉቃስ | አታለለን | የውሸት ዘሩን ዘራበን | አንተ ጠንቋይ የሚመራህ | ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተነሱ ግንባሩን

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል አመራሮችና በኤርትራ ባለስልጣናት መካከል የመነጋገር ፍላጎት እንዳለ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካዔል ተናግረዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=pKU8igiCV3I&t=500s

Share