የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ በሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ

በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዜና በኦሮሚያ ክልል በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እየዋሉ ስላሉ ዜጎች መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት የታሳሪዎች ቁጥር 75 መድረሱን የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ከታሳሪዎቹ መካከልም የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባና ምክትሉ እንደሚገኙበት ሰምተናል::

የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ ከበደ፥ዛሬ እንዳስታወቁት በሌብነት ተጠርጥረው እስካሁን በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም፦
ከኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ተቋም
– አቶ ተሾመ ለገሰ- ዋና ዳይሬክተር
– አቶ ተሾመ ከበደ- የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
– ወይዘሮ መስከረም ዳባ- የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
ከኦሮሚያ ግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ አመራር የነበሩ እና በአሁኑ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ
አቶ መሃመድ ቃሲም- ዋና ዳይሬክተር
አቶ እንዳልካቸው በላቸው- የኤጀንሲው የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
አቶ ይልማ ዴሬሳ- የኤጀንሲው የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
አቶ አብዶ ገለቶ፦ የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር
አቶ መንግስቱ ረጋሳ፦ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚሮ ምክትል ሀላፊ የነበሩ በአሁኑ ወቅት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ
ከሻሸመኔ ከተማ
አቶ ፈይሳ ረጋሳ፦ የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ
አቶ አብዶ ገበየሁ፦ የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አቶ ገመዳ በዳሶ፦ የሻሸመኔ ከተማ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ
ከጅማ ዞን
አቶ ፋንታ በቀለ፦ በጅማ ዞን የማንቾ ወረዳ አስተዳዳሪ
ይገኙበታል::
https://www.youtube.com/watch?v=JAP5FStPHSY&t=3s

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሪሂቡ አፍሪካ - በስንታየሁ ግርማ አይታገድ
Share