የቻይናው ዜድቲኢ ኩባንያ በታክስ ማጭበርበር ተከሰሰ፣ 10 ክስ ቀርቦበታል

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኢኮኖሚና ታክስ ወንጀሎች ዳይሬክትሬት በቻይናው አለም አቀፍ ኩባንያ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍና በቀድሞ ሁለት ስራ አስኪያጆቹ ላይ ክስ መሰረተ፡፡
በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ የመሰረተው ክስ ይህ ኩባንያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ባለመክፈል፣ የገቢ ግብር በማጭበርበርና ህገወጥ ደረሰኝ በመጠቀም እንደተጠረጠረ ያሳያል፡፡ ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው ዜድቲኢ እ.ኤ.አ ከ2009 እስከ 2012 ባለው ጊዜ የ128 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ታክስ በማጭበርበር ተከሷል፡፡

በተጠቀሰው ወቅት ድርጅቱ የሰበሰበው 941 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር እንደነበር መታወቁን ያስረዳው ክሱ በዚህም ጊዜ ከተጠቃሚዎች በተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ስም 28 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሰበሰበ ቢሆንም ይህን ገንዘብ ለመንግስ ገቢ አለማድረጉን ይገልፃል፡፡ የገቢዎች ሚኒስትር በድርጅቱ የአራት አመታት የሂሳብ መዝገብ ላይ ባደረገው ማጣራት 34 የኦዲት ስህተቶችን ያገኘ ሲሆን በዚህም የተነሳ 857 ሚሊዮን ብር ታክስ ድርጅቱ እንዲከፍል ጠይቆ ነበር፡፡ ይሁንና ድርጅቱ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ባለፈው አመት ወደ 412 ሚሊዮን ብር እንደተቀነሰለት ካፒታል አስረድቷል፡፡

ይህም ሆኖ ኩባንያው ህገ ወጥ ድርጊቶችን እየፈፀመ ስለመሆኑ ለፖሊስ በቀረበው ጥቆማ መሰረት ምርመራ እንደተደረገም ተዘግቧል፡፡ ሌላው በዜድቲኢ ላይ የቀረበው ክስ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ባለው ፕሮጀክት ስም የተፈፀመ ማጭበርበር ነው ተብሏል፡፡ ዜድቲኢ በቢሊዮን ብሮች የሚያወጣውን ፕሮጀክት ወስዶ የተሰጠውን ከቀረጥ ነፃ የማስገባት ፈቃድ በመጠቀም ማጭበርበር እንደፈፀመም በክሱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የነበረው የስራ ውል ህግና ደንብን ያልተከተለ እንደሆነ መታወቁ ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ አቃቤ ህግ በዚህ የቻይና አለም አቀፍ ኩባንያ ላይ 10 ያህል ክሶችን መስርቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐቢይ ጄኔራሎች የዝርፊያ ገመና | ለአልሻባብ መሣሪያ የሚሸጠው አበባው ታደሰ | ታከለ ኡማ እና አዳናች አቤቤን የጋበዘው…

በዚክ ክስ ኩባንያው አንደኛ ተከሳሽ ሲሆን ሁለት የቀድሞ ስራ አስኪያጆቹም ተካተዋል፡፡ እነሱም ከዲሴምበር 28 ቀን 2006 እስከ ጃንዋሪ 16 ቀን 2009 ስራ አስኪያጅ የነበሩት ጂያንግ ዩንግ ጁን እና ከጃንዋሪ 2009 እስከ ኖቬምበር 2012 የሰሩት ዛን ያን ሚንግ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ዜድቲኢ ከዚህ ቀደም ከህወሀት ባለስልጣናት ጋር የቀረበ የጥቅም ትስስር እንዳለው ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በተለይም የባለስልጣናቱን ልጆች በቻይና የትምህርት እድል እንዲያገኙ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
https://youtu.be/fabcQQpKeQU

Share