ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የቀረበውን የሽብር ክስ ውድቅ አደረገው

የኦነግን አቀባበል ምክንያት በማድረግ በቡራዩና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የቀረበውን የሽብር ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገው፡፡

በመሆኑም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የግድያ ወንጀል ክስ ሊመሰረት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎች በዛሬው እለት 17 ያህል ተጠርጣሪዎች የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የቀረበባቸው ክስ የሽብር ወንጀልን አያሟላም በማለት በግድያ ወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ጉዳያቸውም ከዚህ በኋላ በሶስተኛና ሃያኛ ችሎት እንዲታይ ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ መሰጠቱ በተጠርጣሪ ቤተሰቦች ዘንድ በተወሰነ ደረጃ ደስታን የፈጠረ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ምክንያቱም በሽብር የተጠረጠረ ምንም ዋስትና የማይፈቀድለት ከመሆኑም በላይ ጉዳዩ የተንዛዛና ረጅም አመት የሚፈጅ፣ እንዲሁም በጅምላ የሚፈርጅ ይሆን ነበር፡፡ ወደግድያ ወንጀል መቀየሩ ግን የእያንዳንዳቸውን ጥፋት በተናጠል በማስረጃ እንዲጠየቁ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ካለጥፋታቸው የታሰሩም የሚፈቱበትን እድል ያመቻቻል ሲሉ አንድ የህግ ባለሙያ ለዘሃበሻ ተናግረዋል፡፡ ዘሃበሻ የአዲስ አበባ ወጣቶች ክስ ሽብርተኝነት መሆኑን በብቸኝነት ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ክሱ ወደግድያ ከተቀየረ በኋላ ግን በርካታ የመንግስት ሚዲያዎች ክሱ ሽብርተኝነት እንደነበር ዛሬ እንደአዲስ እየዘገቡት ነው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=mCS4y1SnXxw

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት ፈፀመ
Previous Story

«የቅማንቶች ጥያቄ» ነበር. . . | አቻምየለህ ታምሩ

Next Story

ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ሊደረጉ የነበሩት ህዝባዊ ሰልፎች ተራዘሙ

Latest from ዜና

ልዕልት ሂሩት ደስታ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

ከአንሙት ስዩም እስካሁን በኖርኩባቸው አመታት የተረዳሁትና የገባኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በዝህብ ላይ መጥፎ ስራ የሰሩትን ወንጀለኞች ለፍርድና ለቅጣት የማቅረብና የማስፈረድ ልምድ ያለንን ያህል፤ መልካም ለሰሩት ግለሰቦች ግን ተመጣጣኝ የሆነ የስማቸው

Share