በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩ ከ60 በላይ ተጠርጣሪዎችና አዳዲስ ታሳሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በዛሬው ዕለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዳዲስ የተያዙ በሌብነትና በሰብአዊ መብት ረገገጣ የተጠረጠሩ ታሳሪዎች; 28 #METEC የሌብነት ተጠርጣሪዎች 36 #የሰብዓዊመብትጥሰት ተጠርጣሪዎች ; ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላና ሌሎች ፍርድ ቤት ቀረቡ::

በሰብዓዊ መብት ጥሰት በእነ ጎሃ አጽብሃ እና በሌብነት ውንጀል በእነ ብርጋዴር ጀኔራል ጠና ቁርዲ መዝገብ የተካተቱ ከ60 በላይ ተጠርጣሪዎች፥ ለ2ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን በሌብነት የተጠረጠሩት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተደረገባቸው የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ መቅረባቸው ነው::

ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከልም:-

– ብርጋዴር ጀኔራል ጠና ቁርዲ፣
– ብርጋዴር ጄኔራል በረኸ በየነ፣
– ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትለአብ
– እና ብርጋዴር ጄኔራል ሀድጉ ገብረጊዮርጊስ ይገኙበታል።

ሆኖም በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዲ መዝገብ እየታየ የነበረው የ26 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ መደበኛ ሰዓት ስላለቀ ለነገ በይደር ቢቀጠርም የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ግን ታይቷል::

መርማሪ ፖሊስበዛሬው ችሎት ኢቲቪ ጋዜጠኛ ፍጹም የሽጥላ ላይ ያደረገውን ምርመራ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በዚህም ጋዜጠኛ ፍጹም የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አባል ነኝ በማለት ለራሷና ለሌላ አንድ ግለሰብ የአባልነት ደብዳቤ በማጻፍ ለመንግስት ስራ በሚል አሜሪካ ለአንድ ወር መሄዷን ጠቅሷል። በአጠቃላይም 23 ሺህ ዶላር ለአሜሪካ ጉዞ በመውሰድ ትዕግስት ታደሰ ከሜቴክ ሕብረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሐላፊ ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ሀብት በማከማቸት፣ 3ኛ አቶ ቸርነት ዳባ፥ 1 ሺህ 80 የእርሻ ተሽከርካሪ ያለአግባብ ግዥ ከቻይና በድለላ በመፈጸም 42 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ በማድረስና 7 ሚሊየን ብር በመጠቀም እንደጠረጠራቸው ፖሊስ ገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቴዲ አፍሮ ይሞታል ያለው ፓስተር እራሱ ሞተ | ቴዲ አፍሮ የሙዚየም ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ | የዘንዶ ወገብ ተመቷል በቅርቡ ይሞታል | የትግራዩ ከባድ ተቃውሞ በደፂ ላይ |

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፖሊስ ቀሪ ስራዎችን ለመጨረስ ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም ተጨማሪ 10 ቀን ፈቅዷል።
በሌላ በኩልም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የነበሩት የነጎሃ አፅብሃን ጨምሮ የ16ቱ የደህንነት ከፍተኛ የስራ ኃለፊዎችና 18 የፌደራል ፖሊስና የማረሚያ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ክስ ፍርድ ቤቱ ተመለከተ::

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በተለይም በደህንነት መስሪያ ቤቱ በከፍተኛ የስራ ኃለፊነትና ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩትን ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበትን የወንጀል ዝርዝር በየግላቸው ጠቅሶ አቅርቧል።

በሽብር ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማፈን ለረዥም ሰዓታት በምርመራ ማቆየት በአሰቃቂ ሁኔታ መደብደብ ፂማቸውን በላይተር ማቃጠል ጥፍር መንቀል የመሳሰሉትን ወንጀሎች ፈፅመዋል በሚል መጠርጠራቸውን እንዲሁም በቁጥጥር ስር የዋሉት የፌደራል ፖሊስና የሽብር ወንጀል ምርመራ አመራሮች ተጠርጣሪዎችን እየደበደቡ ቃላቸውን እንዲሰጡ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል::
ፖሊስ በእስካሁኑ ሂደት የ70 ምስክሮችን ቃል መቀበሉን ገልፀፆ የተጠርጣሪዎችን ንብረት ማሳገዱን ያልተያዙት ላይ ክትትል ማድረግ ከሆስፒታል የተጎጅዎችን ማስረጃ ማሰባብና ሌሎች የምርመራ ስራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ 14 ቀን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆችና ራሳቸውተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ጠቅላይ አቃቢ ህግ በመግለጫው ተጠርጣሪዎች ላይ በቂ ማስረጃ ተሰብስቧል ብሏል አሁን ላይ ከፖሊስ ማስረጃ እናሰባስባለን ተብሎ ከፖሊስ የቀረበው አቤቱታ ትክክል አይደለም የዋስትና መብታችን ይከበር ብለዋል።
ከተጠርጣሪዎቹ 15ቱ መንግስት ጠበቃ ያቁምልን እኛ አቅም የለንም ሲሉ ግራቀኙን የተመለከተው ፍርድቤቱ ብይን ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና ሰነድ በማሸሽ ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ፊልሞን ግርማዬ እና ቴወድሮስ ጣምአለው፥ ፖሊስ በዋስ ይውጡ በማለት ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ 10 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ፈቅዷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ ጣቢያዋን ለመሸጥ እየተደራደረች ነው

በሌላ በኩል በሰብዓዊ መብት ጥሰትና ባላቸውን በማስመለጥ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ባለቤት ወይዘሮ አዳነች ተሰማ እና ጌታነህ አሰፋ ፖሊስ በዋስ እንደለቀቃቸው ለችሎቱ ገልጿል።

https://www.youtube.com/watch?v=Qd-gjrRllUA&t=387s

Share