ኦነግ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የቀድሞ ዋና ፅህፈት ቤቱን ተረከበ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ የሚገኘውን የቀድሞ ዋና ፅህፈት ቤቱን በዛሬው ዕለት ተረከበ።

የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ እንደገለፁት ኦነግ ዛሬ የተረከበው ፅህፈት ቤቱ እስከ 1985 ዓ.ም ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑን ተናግረው ግንባሩ ከሽግግር መንግስቱ ራሱን ካገለለበት ጊዜ ጀምሮ ፅህፈት ቤቱ ከኦነግ ተቀምቶ ለተለያዩ የመንግስት ግልጋሎቶች ሲውል እንደነበር አስረድተዋል።

ግንባሩ ዛሬ የፅህፈት ቤቱን ህንፃ የተረከበው ከወራት በፊት በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገረሳ የተመራ ልኡክ በአሰመራ ከኦነግ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት፥ ለግንባሩ እንዲመለስ በተስማሙት መሰረት መሆኑን አቶ ቶሌራ አስታውቀዋል። የፌዴራል መንግስት እና የኦሮምያ ክልል መንግስት ቃላቸውን ጠብቀው ፅህፈት ቤቱ ለግንባሩ እንዲረከብ ላደረጉት አስተዋፅኦም ኦነግ ምስጋና አቀርቧል። ይህ የኦነግ ፅህፈት ቤት በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በተለምዶ ጉለሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፊ ግቢ ወስጥ የሚገኝ ነው፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=6Vu03MkJX_0

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቓፍታ ሑመራ ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ታሰሩ
Share