በምእራብ በግጭት ምክንያት ኦሮሚያ 26 ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በምዕራብ ኦሮሚያ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 26 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን አስታወቀ፡፡ በቢሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ተሰማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በምዕራብ ወለጋ በተፈጠረው ግጭት 15 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ገልፀው ከመካከላቸው የተቃጠሉና የመማሪያ ክፍልና ወንበሮቻቸው የተሰባበሩ እንዳሉ አስረድተዋል፡፡ በምስራቅ ወለጋ የተዘጉት 11 ትምህርት ቤቶች ግን በስጋት ምክንያት ተማሪ ስላጡ መሆኑን አቶ አፍሬም ተናግረዋል፡፡

ግጭት በመፈጠሩ ከአካባቢው ከ5 ሺ በላይ ተማሪዎች እንደተፈናቀሉ ያስታወቁት አቶ ኤፍሬም እነዚህ ተማሪዎችለጊዜው በሰፈሩበት አካባቢ ተመዝግበው እንዲማሩ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡ ለተፈናቃዮቹ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 800 ሺህ ብር በማበርከቱምበላይ ለተማሪዎቹ የመማሪያ ቁሳቁስ እና ዩኒፎርም እንዲሟሉላቸው አድርጓል ብለዋል አቶ አፍሬም፡፡

በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስም በአጠቃላይ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያስፈልግም በጥናት መረጋገጡን ምክትል ቢሮ ሃላፊው ጨምረው አስታውቀው የጥናት ውጤቱ ለትምህርት ሚኒስትር እንደተላከ አስረድተዋል፡፡
26 ትምህርት ቤቶች የተዘጋባቸው ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ሲሆን የቤንሻንጉል አጎራባች ዞኖች ናቸው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=Kiw-PSSXvLY

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች ሽኝት ተደረገ
Share