ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች ሽኝት ተደረገ

261084159 5034623663236136 9201439380626846247 nከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች በዛሬው ዕለት አሸኛኘት ተደርጓል።
የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ አመራሩ ወደ ግንባር በመሄድ ሰራዊቱን እንደሚያበረታታ፤ አባላቱ ደግሞ ወደ ስልጠና በመግባት መከላከያውን ተቀላቅለው ለአገራቸው እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
ኢዜማ የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስጠበቅ ሁልጊዜም ከፊት ይሰለፋል ነው ያሉት አቶ የሺዋስ።
ወደ ግንባር የሚዘምቱ አመራሮችም ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በምትሆንበት ጊዜ መስዋዕትነት መክፈል ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ደም ያለ መሆኑን በመጥቀስ “በድል እንደምንመለስ እርግጠኞች ነን” ብለዋል።
የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደምም የተለያዩ የኢዜማ አባላት ወደ ግንባር መሄዳቸውን ገልጸው “የሄዱት ግን ኢዜማ ስለሆኑ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ የሁላችንም ግዴታ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ እዚህ የተቀረው አባልና ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ለዘማቾች ስንቅ በማዘጋጀት ደጀን እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
EBC

1 Comment

  1. ምንድነው ድፍንፍን ያለ ነገር ብሬ ይዘምታል አይዘምትም? ከዚህ በፊት ዩዘመተው የትኛው አውደ ውጊያ ላይ ነው ሰዎች አታጃጅሉን እንጅ በዚህ ጊዜ እንኳን ታገሱን። በምርጫ 97 ህዝብን ለሰልፍ ጠርቶ ብሬ ወደ እንድ ብር ነው የመሸገው በ10 አመት ኡደት እንዲህ ያለ የጅል ቀልድ ጥሩ አይደለም። የዘመቱት ጎበዞች አውደ ውጊያው ላይ የግምባር ስጋ እንሆናለን ባሉት መሰረት በዚያው ተገኝተዋል። ግንቦት 7 አመራሩ በሜሎቲ ሚሳየል አስመራ መዋጋቱን እናውቃለን ከዛ ውጭ ወረቀትና ዲስኩር ሜዳ ላይ በጣም ተዋግተዋል። ግንቦት 7 ኢዜማን ባያቆሽሸው ተስፋ ያለው ድርጅት በሆነ ነበር።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.