ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የመጀመርያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆኑ

ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ዳኜ መላኩ በፈቃዳቸው የሥራ መልቀቂያ በማቅረባቸው ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊን በዕጩ ፕሬዚዳንትነት አቅርበው አሹመዋል፡፡

ወ/ሮ መአዛ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፤ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ በሕግ ትምህርት አግኝተዋል፡፡ በአሜሪካ ኬንታኪ ዩንቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ግለ ታሪካቸው ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ በንግድ ሚኒስቴር የሕግ ባለሙያነት፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት እንዳገለገሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን በመመሥረትና በመምራት ለሴቶችና ለሕፃናት መብትና ፍትሕ መታገላቸውንም ገልጸዋል፡፡ በንግድ ዓለምም ውጤታማ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ ከህጉም ወጣ ብለው የመጀመሪያው የሴቶች ባንክ የሆነው እናት ባንክ መስራች ሲሆኑ በቦርድ ሰብሳቢነትም አገልግለዋል።
ይህ ባንክም ለሴቶችና ለሴቶች ኢንተርፕረነሮች የገንዘብን አቅርቦትን ለማሳለጥ የተመሰረተ ባንክ ነው።
በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የማስተርስ ትምህርታቸውን በአለም አቀፍ ጥናት ትምህርት ከኮኔክቲከት አግኝተዋል።
በወቅቱም የመመረቂያ ጥናታቸው የነበረው ሴቶች በህዝብ ውሳኔ ላይ ያላቸው ተሳትፎን በጥልቀት ማየት ነበር።
በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትም ተሳትፎ ያላቸው ወይዘሮ መዓዛ የሞ ኢብራሂም አፍሪካ ገቨርናንስ ኢንዴክስ አድቫይዘሪ ካውንስል አባል ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፀሐፊም ተመርጠው የአፍሪካ የሴቶች ኮሚቴ ለሰላምና ለልማትም አባል ሆነው አገልግለዋል።
ለተለያዩ አገልግሎታቸውና በተለይም ለኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ላበረከቱት አስተዋፅኦ የተለያዩ ሽልማት ያገኙ ሲሆን ዘ አፍሪካን ሊደርሺፕ ፕራይዝ ኦፍ ዘ ሀንገር ፕሮጀክትና፤ ኢንተርናሽናል ውሜን ኦፍ ከሬጅ ይገኙበታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: የዩክሬይን ፖለቲካና እግርኳስ

ምክር ቤቱ ዕጩ ፕሬዚዳንቷን በሙሉ ድምፅ የተቀበለ ሲሆን፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የቀረቡለትን አቶ ሰሎሞን አረዳንም በተመሳሳይ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

አቶ ሰሎሞን አረዳ በአሁኑ ወቅት የስመ ጥር ዓለም አቀፍ ተቋማት የሕግ አማካሪ እንደሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት የተሿሚው የግል ታሪክ ተመልክቷል፡፡

አቶ ሰለሞን በኩዩ ገብረ ጉራቻ የተወለዱ ሲሆን፣ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በሕግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዳገኙ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሕግ ከአምስተረዳም ዩኒቨርሲቲ እንዳገኙ ተገልጿል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በሕዝብ አስተዳደር እንዲሁም በሕግ ከሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ሄግ) በግልግል ዳኝነትም አገልግለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ እንደተናገሩት ተሿሚዎቹ ‹‹ፍትሕ ፍትሕ የሚሸት ተቋም እንደሚያደርጉት እተማመናለሁ፤›› ብለዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=NaLy5pGAFTc

7 Comments

  1. ኣየህ! ኣየህ!ኣየህ!
    መዓዛን!የመስከረም ሽታ ዓደይን
    ለፍትህ ለመብት ጥቅምትን
    እሸት ልንበላ በቆሎን
    ኣተር! ባቄላ! ሽምብራን!
    ኣየህ! ኣየህ!ኣየህ!ሰብላችን
    ጎመራ! ኣልጎመራም? የሰብል መዓዛችን!

  2. ከድንቁርናም ይሁን ትምክህት ወይ ከሁለቱም ; የኛን የፖለቲካ ፕሮግራም እስከፈጸመ ድረስ ማሀይምን ሚኒስትር ማረግ እንችላለን በተባለበት ሀገር ሙያን፣ባለሞያን አና ስነ ምግባርን ባቀናጀ መልኩ ሹመት እያየን በመሆኑ የወንድማችን ለውጥ ሂደት በርግጥ ጥፍር እና ጥርስ ለማውጣቱ ማረጋገጫ ነው።
    Congratulations Abiy !
    Congradulations Meaza and Solomon !

  3. This is congra for Meaza. But you remembered that during 1997 pre-election campaign as a human right & civil right activist you were in mind of many people.

    But then people afraid of you as your activist movement were not clear to many of your supporters. So this will be a right time for you to do things right, do your job autonomously, and reward those people who seek justice, fairness and human right by law.

    Wish you a good time keeping in mind that you are shouldering a voice of many disadvantaged groups.

    Long live to Ethiopia!!

  4. Though Mrs. Meaza’s career is positive, the fact that she is married to one of the top TPLF’s functionaries, her appointment to the top job gives some bitter after taste!

  5. Congra!! የሚያስብል ነው፡፡ ሆኖም በዚህች አገር ውስጥ ትክክለኛ ፍትህ በማሰፈን ሂደትና በሕግ የበላይነት ስራዎች ላይ ከባድ ኃላፊነት፣ ቁርጠኝነትና አደራ እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን ለቀጣይ ምርጫም ገለለተኛ የሆኑ የፍትህ አካላት፣ ነፃና ፍትሓዊ ምርጫ በማስፈን ሂደት ከእርሶ ጠንካራ ስራ ህዝቡ ይጠብቃል፡፡

    ፍትሕና ዲሞክራሲ ከማስፈን አንፃር መልካም የስራ ጊዜ ይሆኑሎ፡፡

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

  6. ኣየህ! ለውጡን? ኣየህ?
    መች መስከረም?
    መዓዛ እኮ ነው! የጠፋበት ኣረም!
    መስከረም! ዓደይ!ኣረም! ኣበባም!
    ግን መዓዛ! ሽታ! የጥቅምትም
    ወፎች በሰብ ላይ ሲከንፉም
    መች መስከረም!? የበዛበት ዓረም?
    መዓዛ ነው! መዓዛ! የሰልብ ሽታ! ጣዕም!
    ባበሻ ልብስ ኣጊጣ!
    መች በሎቲ ኣፍጣ?
    ፈገግታ ቸራ! የምትል ኣምጣ
    መዓዛ! የሰብል ሽታ! የሴት ጣጣ!
    መች እንደ መስከረም ዘብጣ??

Comments are closed.

Share