ወይዘሮ ፈትለወርቅ ሞንጆሪንሆ አሁንም ተቃራኒ መግለጫ ሰጡ

ባለፈው ሳምንት የተካሄደው የኢህአዴግ ጉባኤ ግንባሩ ላለፉት 27 ዓመታት ሲመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚተካ ርዕዮተ ዓለም ተጠንቶ ለመጪው ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኖ ይህም በመንግስታዊ ሚዲያዎች ቢቀርብም የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ግን በ11ኛው ጉባኤ ግንባሩ የሚመራበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም ለማጎልበት አቅጣጫ አስቀመጠ እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲን ለመቀየር አቅጣጫ አልተቀመጠም ብለዋል::

የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር የኢህ አዴግ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት በሰጡት መግለጫ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በማለት መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን ግንባሩ ላለፉት 27 ዓመታት ሲመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚተካ ርዕዮተ ዓለም ተጠንቶ ለመጪው ጉባኤ እንዲቀርብ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፏል ተብሎ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ ስህተትና በጉባኤው ሪፖርት የሌለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

“አንዳንድ የግንባሩ አባል ብሄራዊ ድርጅቶች አባላት በጉባኤው ግንባሩ የሚመራበት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራም መለወጥ አለበት የሚል ሀሳብ አንስተው ነበር፡፡ አባላቱ ባነሱት ጥያቄ ዙሪያ በጉባኤተኛው አስተያየት ከሰጠበትና ውይይት ከተደረገበት በኋላ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራምን ይዞ ለመቀጠል ከስምምነት ተደርሷል” ሲሉ የገለጹት ወይዘሮ ፈትለወርቅ፤ ግንባሩ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ በመጓዝ ለውጥ ማምጣት እንደሚችልም በሁሉም ዘንድ መግባባት መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

“የፕሮግራም ለውጥ ለማድረግ ማሰብ ክልክል አይደለም:: በተለያዩ ጊዜያትም ግንባሩ የፕሮግራም ለውጦችን ሲያደርግነበር:: የፕሮግራም ማሻሻያዎችን ለማድረግና የሚተካ ርዕዮተ ዓለም እንዲጠና የሚወሰነው ግን በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ አይደለም::” ያሉት የቀድሞዋ የአባይ ጸሐዬ ባለቤት ወይዘሮ ፈትለወርቅ “ከዚህ ቀደም ግንባሩ የፕሮግራም ለውጦችን ሲያደርግ ነበር፡፡ ማሻሻያዎች ሲደረጉ የነበሩት ጥናት ከተካሄደና መላው የድርጅቱ አባላት እንዲሁም ህዝብ እንዲወያይበት ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ በርካታ ጥናታዊ ጽሁፎችና ኮንፍረንሶችም ከተካሄዱና መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ ማሻሻያዎች ሲደረግ ነበር፡፡” ብለዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የአዲስ አበባን የወደፊት እጣ የሚወስነው ሕዝቡ ነው" | ቃለምልልስ የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ኦዳ ጣሴ ጋር

በተመሳሳይ የሕወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልም ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰኞ ዕለት ባደረጉት ቃለምልልስ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እንደማይቀየርና ይህም የሕወሓት አቋም እንደሆነ ገልጸው ነበር::
https://www.youtube.com/watch?v=CzMvgTPy95U&t=353s

Share