October 28, 2013
1 min read

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አመጽ አነሳስተዋል ያላቸውን 27 ሠራተኞቹን ከሥራ አባረረ

(የባህር ዳር ከተማ)
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አመጽ አነሳስተዋል ያላቸውን 27 ሠራተኞቹን ከሥራ አባረረ 1
የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ መልስ እንደሚሠጣቸው ቃል ገብቶ እንደነበር ታውቋል፡፡ ነገር ግን በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ስራአስኪያጅ አቶ አባይ መላኩ ስምና ፊርማ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል የፋብሪካው ስራስኪያጅ የሆኑት አቶ አባይ መላኩ ሰራቸኞች መባረራቸውን አምነው ቁጥራቸው ግን 5 ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የመባረራቸውን ምክንያትም ቢሆን በተባለው ጊዜ ምንም እውቅና የሌለው ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ስላደራጁ ነው ብለዋል፡፡

Previous Story

ፍትሃዊ አስተዳደር ሳይኖር ልማት እንዴት ይታሰባል? (በጌታቸው)

habtamu
Next Story

Hiber Radio: ጄኔራሎች በምደባ ስም እየተበወዙ ነው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop