የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰማች

ከኢሳት የተገኘ ዜና

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም -በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተ ክርስቲያኑዋ ታሪክ ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ” ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል።

የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ተቃውሞው የተሰማው።

እድሉን ያገኙት ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም የሰሜን ወሎ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቄርሊዮስ ፣ የምእራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ ሄኖክ፣ የጋሞ ጎፋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ፣ የወላይታ ዳውሮ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብጹ አቡነ ማርቆስ፣ የደቡብ ጎንደር ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድሪያስ የመንግስትን ፖሊሲ እአነሱ ትችት አሰምተዋል።

በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ፣ ግድያና ጫና መጨመሩን የተነጋሩት አባቶች፣ ፓትሪያርኩም እውነት ነው ይህ ሁሉ ጫና አለብን በማለት በሊቀ ጳጳሳት የቀረቡውን ሀሳብ ደግፈዋል።

ከመላው አለም የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀይማኖቱ መሪዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን የሀይማኖት ታሪክ በማሳነስ ባቀረቡበት ወቅት የሀይማኖት አባቶች ስሜት በተቀላቀለበት ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።

የህዝቡን መሬት ነጥቃችሁ፣ ህዝቡንም መሬቱንም የመንግስት ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ኢትዮጵያዊው ሀብትና ንብረት እንዳይኖረው አደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግስታት በባሰ ህዝቡን ያስጨነቀ ይህ መንግስት ነው በማለት አባቶቹ ተናግረዋል።

“በአጼዎችም ዘመን ቢሆን ይህችን አገር ስትረከቡ እስከ ታሪኩዋ ነው፣ ታሪኩዋን አላጠፋችሁም ወይ?” በማለት ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ሲናገሩ ከተሰብሳቢው ከፍተኛ ድጋፍ ተችሮአቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጎንደር ከተማ የታገቱ አማራ ተማሪዎች እንዲለቀቁ የሚጠይቀው ሰላማዊ ሰልፍ

የሀይማኖት አባቶች የቤተክስርቲያኑዋን ታሪክ አዛብታችሁዋል፣ ቤተክርስቲያኑዋንም ታሪኩዋን አጥፍታችሁዋል በማለት ወጥረው መያዛቸው ታውቋል።

 

4 Comments

  1. long over due! but if it really happen, then we praise you for your courage and determination. you have to keep speaking up and stand beside the people of Ethiopia. Since orthodox church a big part of Ethiopian history, our fathers should feel obligated to keep that history intact. free yourself from these children of devil and claim back your degnity and respect.

  2. Ethiopia Orthodox church requesing is not the first time please, read ,read, read history. why you say in history? or you want to say in EPRDF regim? confused please do not confused peoples by releasing such news. I agree in EPRDF/TPLF regim but in history is unacceptable.

    • if this news is true it will be the first in history , what kind of history mr temesgen do you read, ye menekosat teret teret?? have you forgot that ethiopian orthodox chuch and the government were one until derg came to power. Or you want to write another teret teret kkkkkkk.
      remember the state and the church were together all in ethiopian history .

      adios amigos !!!

  3. @temesgen. No body confusing this article it’s clear and real I’m surprised finally their voice came out. Good for ethiopian orthodox believers we need to stop together weyanes agenda,

Comments are closed.

Share