November 7, 2017
5 mins read

ወያኔ ተልካሻ የእርሻ መሳሪያዎች ማስገባቱ ለቅራኔ እንደዳረጉት ታወቀ | ወያኔ የሽብር ድርጊት የሚፈጽሙ አሰልጥኖ ማሰማራቱ ተሰማና ሌሎችም (የፍኖተ ዴሞክራሲ የዛሬ ዜናዎች)

የፍኖተ ዴሞክራሲ የዛሬ ዜናዎች
ወያኔ የሽብር ድርጊት የሚፈጽሙ አሰልጥኖ ማሰማራቱ ተሰማ

▪ በቅርቡ በነቀምት ከተማ የኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ በዐል የሆነው ኢሬቻን ለማክበር በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ ቦምብ ለመወርወር ተሰማርተው የነበሩ በሕዝብ መያዛቸው ጋር በተያያዘ ይህ ዓይነቱን እኩያ ድርጊት ከዚህ ቀደም ወያኔ ማካሄዱ የሚታወስ ነው ተብሏል፡፡ መኪናዎች ውስጥ፣ መስቀልኛ መተላፊያ መንገዶች ጥግ፣ የአውቶብሶችና የታክሲ መቆሚያዎች፣ በትምህርት ቤትና በገበያ ቦታዎች፣ በቤተክርስቲያንና በመስጊዶች፣ በአውቶብሶች በታክሲዎች እንዲሁም በባቡር ውስጥ፣ ወዘተ. ወያኔ ፈንጂዎች በማስቀመጥ በህዝብ ላይ አደጋ ለማድረስና አሁን ያለውን ፀረ- ወያኔ እንቅስቃሴ ለማሽመድመድ በእቅድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ከወያኔ ሾልኮ ከወጣ መረጃ መገንዘብ ተችሏል፡፡ የዚህ ምስጥራዊ ሰነድ ምንጮች አያይዘው፣ ማንኛውም ሰው በተቻለው አቅም አካባቢውን መቃኘትና በፕላስቲክ ወይ በጨርቅ ወይም ደግሞ በወረቀት የተጠቀለለ አንዳች ነገር ካዩ በተቻለው ከቅም ከዚያ አካባቢ መራቅ እንዳለበት ምክራቸውን ይሰነዝራሉ፡፡

ስኳር ከውጪ እንዲገባ መደረጉ አሳዛኝ መሆኑ ተነገረ

▪ወያኔ በያመቱ ለስኳር ልማቶች ማስፈጸሚያ እያለ የገንዘብ ዘረፋውን እንደሚያጧጡፍ በየጊዜው እየተዘገበ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ በስኳር ልማት ስም የዓባይ ፀሀይና የሳሞራ ዩኑስ ቡድን ከሁለት መቶ ቢሊዮን ብር በላይ እንደዘረፈ በመረጃ የተደገፈ ሰነድ እንዳለ በስፋት ቢነገርም እስካሁን የዚህ ዘረፋ ቀንደኛ ተዋናይ የሆኑት ዓባይ ፀሀይ እና ሳሞራ ተወንጅለው ዘብጥያ መወርወር ይገባቸው ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ የገበያ ዋጋ ሰማይን እያከከ ባለበት ወያኔ ባስከተለው ችግር አንድ ኪሎ ስኳር በተለያዩ ከተሞች ከስልሳ እስከ ሰባ ብር ሲሸጥ መክረሙ የወያኔን ገፋፊነት የሚሳይ መሆኑን በርካቶች በምሬት ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡ ወያኔ በዚህ ሳምንት ባሰራጨው ወሬ በ 30.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር፣ 700‚000 ኩንታል መገዛቱና መጓጓዝ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡ ታዛቢዎች እንደሚሉት ከዚህ ከተባለው ስኳር ከግማሽ በላይ የሚሆነው አየር በአየር በወያኔ ቁንጮዎች እንደተለመደው ሊቸበቸብ እንደሚችል ነው፡፡ ወደ ኬንያ በሌለ ዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት ስም ሊወጣ የነበረው ስኳር ወደ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ መጋዘን እንዲገባ መታዘዙ ከመታወቁ ውጪ እስካሁን የስኳሩ መዳረሻ አይታወቅም ተብሏል፡፡

ወያኔ ተልካሻ የእርሻ መሳሪያዎች ማስገባቱ ለቅራኔ እንደዳረጉት ታወቀ

▪ በወያኔ ቁንጮዎች የንግድ ድርጅት ከቻይና የገቡ አነስተኛ የእርሻ ማሽኖች እርባና ቢስና ስንኩል መሆናቸው ሆን ተብሎ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ዐይን ያወጣ ዘረፋ ነው ተባለ፡፡ የማሽኖቹ መዋቅሮች የተነደፈው ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን የተሰሩት በቻይና መሆኑ ታውቋል፡፡ ለሠላሳ ሺ ማሽኖች ወጪ የተደረገው ገንዘብ ከሠላሳ ሚሊዮን ብር በላይ ነው ተብሏል፡፡ መሽኖቹ ገበሬዎች በግዳጅ እንዲገዟቸው ለማድረግ የተደረገው ሙከራ በማሽኖቹ ስንኩልነት ሳይሳካ መቅረቱ ታውቋል፡፡ እነዚህ ማሽኖች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የተደረገው በወያኔ የግብርና ኃላፊዎች ትእዛዝ በመሆኑ ለኪሳራው ተጠያቂው ይኸው መሥሪያ ቤት ሲሆን ጉዳዩ ብዙ እርቀት ከተጓዘ ቁንጮ ወያኔዎችን ስለሚነካካ ባጭሩ ሊዳፈን ይችላል የሚል ግምታቸውን የሚሰነዝሩ በርካቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

Previous Story

“የህወሓትን ሕዝባዊ ጭፍጨፋና ከፋፋይነት እንኮንናለን፣” – በኮሎኝና አካባቢዋ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ/ኮሚኒቲ ኮሎኝ/ጀርመን

nosebleed diagram
Next Story

ነስር (Nose bleeds)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop