አማሮችን በገጀራ! ህወሃት በኢሉባቦር እየሰራ ነው

ክንፉ አሰፋ

ህወሃት የአማራው ሕዝብ ላይ ያለው አቋም ከፋሺሽት ጣልያን የተወሰደ ውርስ ነው። በበላይ ዘለቀ ይመራ የነበረው ጦር ጣልያንን እስከፍጻሜው ተፋልሞ ባዋረደበት ግዜ – የጣልያኑ ጀነራል ደቦኖ የተናገረው በታሪክ መዛግብት ላይ ተቀምጧል።

“ደጋግሜ ተናግሬ ነበር። አማራና ኦርቶዶክ ቤተ ክርስትያን ካልጠፉ ሰላም ልናገኝ አንችልም። “
አቦይ ስብሃት እና አባይ ጸሃዬም ይህንኑ የደቦኖ አነጋገር በተደጋጋሚ ሲሉት ተደምጠዋል። የዛሬ 40 ዓመት የወጣው የህወሀት መኔፌስቶም በገፅ 15 እና 16 ላይ “ጨቋኟ አማራ ህብረተሰብአዊ እረፍትና ሰላም አታገኝም” ብሎናል።

ይህ ፕሮግራም በወረቀት ላይ ብቻ ሰፍሮ አልቀረም። በተግባርም እያሳዩን ነው። በማጂ፤ ጉራ ፈርዳ ወረዳ ሠፋሪ አርሶ አደሮች በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገድደው ቀያቸውን ለቅቀው ወጥተዋል፤ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ በአስር ሺ የሚቆጠሩ አማሮች ላይ የማፈናቀል ዘመቻ ተደርጓል፣ ከዚህ ቀደምም በበደኖ፣ በኢንቁፍቱ፣ በወተር፣ በአርሲ፣ ወዘተ አማሮች ላይ የደረሰው ግፍ በታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም። እስካሁን መልስ ያላገኘው በሕዝብና ቤት ቆጠራ 2.5 ሚሊዮን አማሮች የገቡበት ያለመታወቁም አንዱ የመሰሪ ፕሮግራም እቅድ ነው።
የህወሃት ማኒፌስቶ ወደ ተግባር ተለውጦ፣ ላለፉት 26 አመታት ግፍ እየሰራ ረጅም ተጉዟል። ወልቃይትና ቅማንት ላይ ሲደርስ ደግሞ ማንነትን የሚፈታተን ትንቅንቅ ላይ ይገኛል።
የገጀራው እልቂት ግን ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ሳይሆን ይቀራል? ነገሩ እንዲህ ነው። እየተንጠባጠበ ከሚወድቀው የንግድ አጋራቸው ይልቅ፤ የ”ጣና ኬኛ” ፖለቲካ እነ ደብረጽዮንን እረፍት እንደነሳቸው በስፋት ይነገራል። የማይወድዱት የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ህብረት መፈጠሩ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ገና ዳቦ የሚለበልብ ነቄ ትውልድ ሳያስቡት መጣባቸው። ለጭንቅ ግዜ የቀመሩት የፖለቲካ ሂሳብም እንደቀድሞው ማርሽ እየቀየሩ የሚሄዱበት መንገድ አልሆን አላቸው። ስለዚህ ፊት ለፊት ገጀራ ይዘው መጨፍጨፍ/ማስጨፍጨፍ ተያይዘዋል። በዚህ ሁኔታ ስንቱን ገድለው እንደሚዘልቁት የሚያውቁት ግን አይምስልም።
ወትሮም ውርደት ጌጥ በሆነላቸው የብአዴን ዋርድያዎች ይህ የሚያሳስባቸው ጉዳይ አይደለም። ይልቁንም የአስደናቂው የ”ጣና ኬኛ” ፖለቲካ አቀንቃኞች ለዚህ ጉዳይ ምላሽ ሊሰጡበት እንደሚችሉ እርግጠኞች እየሆንን ነው። እነ ለማ መገርሳ ከነበሩበት የፍርሃት ቋት ራሳቸውን አውጥተው ከህወሃት እኩል መነጋገር የጀመሩ ይመስላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ክልል ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ላቀ አያለው እና ባልደረቦቻቸው የተናገሩት

የእነ ደመቀ መኮንን ነገር ባይነሳ ይሻላል። ሲያሻው በቃርያ ጥፊ ሲያጮላቸው – ሲያሻው ደግሞ ሲተፋባቸው ይዘልቁታል እንጂ እንዲተነፍሱም እድል አይሰጣቸውም። በዘረኝነት ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኙ ላሉት ለእነ ደብረጽዮን ከጥፊዋ ዋጋ ይልቅ የጥፊዋ ጠቀሜታ ነው የምትታያቸው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው አማራው ሲታረድ እነሆ ዝም ብለዋል።

ግዜውን ጨርሶ በባከነ ሰዓት እየተንፈራገጠ ያለው የትግሬ ቡድን ዛሬ በኢሉባቦር ከ20 በላይ ዐማሮች በአንድ ቀን ብቻ በገጀራ መጨፍጨፉ እጅግ የሚያንገበግብ ቢሆንም አዲስ አይደለም። ገዳዮቹ ግን ከቶውንም ከፍርድ አያመልጡም። መውደቅያቸው ላይ ማጠፍያ ሲያጥራቸው ታርዶ እንደሚንፈራፈር ዶሮ የሆኑ ይመስላል… ይህ ሁሉ ሲሆን የአማራው ህዝብ ትዕግስት እንደ ፍርሃት ተቆጥሮ ከሆነ ግን ትልቅ ስህተት ነው። ሁሉንም ግዜ ይፈታዋል!

2 Comments

  1. የከፋው ደደብነት ወሮ በላ ጠባብ ገዳይን ነፃ አውጥቶ ሌላ ጠላት ማፈላለግ ነው ፡፡ በመሀይምነትና በድንቁርና እየተመሩ አእምሯቸውን አጥብበው እንደ ፊጋ በሬ የሚነፈራገጡትን የኦነግና የጀዋር ልቃሚዎች ሀይ ማለት ያሻል ፡፡

    ጎረቤትህን ወገንህን ማጥቃት የበታችነት ምልክት ነው ፡፡
    መሬቱ የኔ ነው የሚለውን እንደ አፄዎቹ ከርስቱ መንቀል ሳይሻል ይቀራል ??

    ዘረኝነት የአእምሮ በሽታ ነው !!

  2. Urgent action is needed!

    ወንድሞቼ እስቲ እባካችሁ ለድርጊት እንነሳ:: የምናደርው ስራ ጥንቃቄ የተሞላበት ና በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት:: ለወደፊትም ታሪካዊና የማያዳግም ትምህርት የሚሰጥ መሆን አለበት እላለሁ:: የአሁን የአማራዎች በገጀራ መጨፍጨፍ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም ስለዚህ ወደፊትም በስፋት ሊቀጥል ይችላል::
    ታዲያ መከላከያችን ምን መሆን አለበት መጮህ? ማልቀስ? ይሄ ይሰራል ያ ያዋጣል ብሎ መነታረክ? ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ሰልፍ? በየአገራቱ ዋና ከተማዎች ሰንደቅ ዓላማ ይዞ ሰልፍ መውጣት? ይሄ ሁሉ አልሰራም:: የአማራን ከመታረድ አላስቆመም::
    ለምን ብለን እንጠይቅ

    1ኛዉ እና ዋናዉ ጉዳይ እራሳችንን ስለምንሸነግል, አንዴም ሰብአዊ ነኝ በማለት አሊያም አለምአቀፋዊ ነኝ በማለት:: ይሕንንም ለማስጨበጥ ከብዙ መጽሓፎች ብዙ ምሳሌዎችና አባባሎች በመጥቀስ ራስ ተደናብሮ ሌላውን ማደናበር ::

    2ኛዉ ደግሞ ሁሉንም ነገር ኃላፊነቱን ለእግዚአብሔር ስለምንሰጥ (ኧረ እስቲ ተመልከቱ! እግዚአብሔር እንድንመለከትና እንድናስብ ሁሉንም ነገር አሟልቶ በነጻነት ፈጠረን ታዲያ መልሰን አንተው አመጣኸው አንተው ጨርሰው ብሎ ያለ አቅም መንጠራራት ምን አመጣው? አሁንስ ለእግዚአብሔር በጣም አዘንኩለት:: ከምር:: )

    3ኛው ደግሞ ከመጠን ያለፈ ይሉኝታ

    4ኛው እነኝህን ከላይ የጠቀስኴቸውን ድክመቶቻችን ላይ በመመርኮዝ የአማራ ህዝብ ጠላቶች (በዋናነት ወያኔ በአስፈጻሚነት፥ በተባባሪነት እና ዝምታን በመምረጥ ኦነግ ኦፒዲኦ እና ብአዴን) በዚህ ህዝብ ላይ ከ፵ ዓመታት በላይ በጥንቃቄ የሸረቡት የጥፋት ሴራ እና ቀጥተኛ ጥቃት ሲሆኑ ይህንን በአንድ ነገድ ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ጥላቻ ከውጭ ሀገር ሆነው ቤንዚን ሲያርከፈክፉ ያሉት እንደ ጃዋር መሓመድ እና ፀጋዬ አራርሳ የመሳሰሉት ይገኙበታል፥፥

    ታዲያ ካለን የቦታ ና የአቅም ውስንነት የተነሳ በስደት ያለው አማራ እና ሰላም ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በስደት እየኖረ ምን ማድረግ ይችላል? (ወይም አለበት?)
    በዚህ ጉዳይ አንዳንድ ማድረግ የምንችላቸውን ሀሳቦች ማጋራት እፈልጋለሁ።

    ፩ኛ፥ ከሁሉ አስቀድመን ለጊዜውም ቢሆን ይሉኝታችንን ማገድ (suspend ማድረግ) ይኖርብናል

    ፪ኛ፥ አማራ ላይ ያነጣጠረ ማንኛውንሞ ከበቂ በላይ የተከማቸ ኦዲዮ ቪዲዮ እና ጽሑፎችን ማሰባሰብ ማጠናቀር

    ፫ኛ፥ እስካሁን ድረስ ለአለፉት 26 ዓመታት በብቸኝነት የችግሩ ሰለባ የሆነው የአማራው ህዝብ ስለሆነ የአማራውን ሰቆቃ ለመታደግ አሁን የተፈጠሩት የአማራ ድርጅቶች በዋናነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ አንድነት እና ደህንነት የሚታገሉ ዜጎችን በተባባሪነት ያቀፈ ግብሪኃይል ማቛቛም

    ፬ኛ፥ ይህ ግብረኃይል ከአማራው በነፍስ ወከፍ ወይንም በውዴታ ግዴታ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ግለሰብ በውዴታ በሰነድ የተደገፈ በቂ ገንዘብ ማሰባሰብ

    ፭ኛ፥ በአለም አቀፍ ህግ እና በወንጀል ህግ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ወይንም ያልሆኑ የህግ ባለሙያዎችን ማፈላለግ

    ፮ኛ፥ በአሁኑ ሰዓት በዉጭ አገር የሚገኙ ከዚህ በፊትም ሆነ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ህዝብ ላይ በማነጣጠር የወያኔ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ቀጥተኛ ትእዛዝ ና ትብብር የሰጡትን የጥላቻ ሐውልት ያቆሙትን (እንደ ታምራት ላይኔ፣ ሰዬ አብርሃ፤ ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ጁኑዲን ሳዶ፤ ሌንጮ ለታ ) እንዲሁም ከርቀት ሆነው ሜንጫቸውን በመሞረድ አማራውን በሀገሩ ስደተኛና መጤ ያስደረጉትን (እንደ ጃዋር መሓመድ፣ ጸጋዬ አራርሣ፤ እንዲሁም “አምቦ” ተብዬው ወዘተ) አይነቶችን ነቅሶ በማውጣት በወንጀለኛነት በየአሉበት አገር መክሰስ

    ለምን እነኝህን ብቻ? ዋናዉን ወያኔ ትቶ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል:: ግን እንደኔ እይታ ውጭ አገር ሆነን በቀጥታ ማድረግ የምንችለው አቅማችን ይሄንን ብቻ ስለሚፈቅድ ነው፤፤
    አንደኛ ገንዘባችንን በማዋጣት አሁኑኑ ማድረግ እንችላለን፤ ሁለተኛ ይህን ለማድረግ ብቁ የህግ ባለሙያዎች ያሉን ይመስለኛል (ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ እንዲሉ ማንኛውም የአማራ ወይንም ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሞያ ለዚህ ታጥቆ መነሳት አለበት እላለሁ)::
    ባለጉዳዩ ነኝ የሚል ከጠፋ አለበለዚያ እንደራሳቸው ጉዳይ አድርገው ለሚመለከቱ ጂዊሽ የህግ ባለሙያዎች ጉዳዩን መስጠት ይቻላል::

    ልብ በሉ ዘረኞች ግለሰቦች የተባበሩበት የአማራ ጥላቻ ፖለቲካ እነሆ ፍሬውን አፍርቶ ምርቱ እየታጨደ ሳለ እነሱ በበኩላቸው ኃላፊነቱን ላለመውሰድ ሌንጮ ሲጠየቅ ዳውድ ሲል እሱም በበኩሉ ሌሎች ናቸው ይላል፥ ሌሎቹ ደግሞ እኛ አመጹን አንመራውም ይላሉ፥፥

    ስለዚህ እኛ ደግሞ “እከሌ ተከሌ” ብሎ ነገር የለም: ሁላችሁም ወንጀለኛ ናችሁ እንላለን::

    በነገራችን ለይ አንድ ግሩፕ በሚያደርገው ድርጊት መንስኤ የጀኖሳይድ ውጤት ከመጣ ያ ድርጅት ወይንም ሰው ከመጠየቅ አያመልጥም (ልብ በሉ ሜንጫ ብሎ አበረታታ ፥ በሜንጫ ተጨፈጨፉ)
    አንድ ሰው እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የወንጀል ክስ ከተመሰረተበት ክሱን በብቃት ለመከላከል እንዲችል ከሚሰራው ስራ የሚታቀብበት አጋጣሚ ይፈጠራል (እንደምንም ብለን እዚህ ካደረስናቸው የኛን ግዴታ በመጠኑም ቢሆን ተወጣን ማለት ነው፥፥ በዚያ ምክንያት ስራቸውን ቢያጡ፣ እሰየው! (This would be the minimum we can achieve, easily, if not more) በነሱ የጥላቻ ፖለቲካ በገጀራ ተጨፍጭፈው ህይወታቸውን ያጡት ምን ይባሉ! እዚህ ላይ ይሉኝታ አይኖረኝም:: )

    Bear in mind, whether some one is working for WHO or UNDP or teaching at University there will be no spare from being legally prosecuted!

Comments are closed.

Share