ሸንጎ ትናንት በአዲስ አበባ ሰልፉን ላዘጋጁት አንድነት እና 33ቱ ፓርቲዎች የትግል አጋርነቱን ገለጸ

ሸንጎ ለዘ-ሐበሻ የላከው መግለጫ የሚከተለው ነው፦

መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
September 29, 2013

በዛሬው ዕለት በአዲሰ አበባ ውሰጥ የታየውን ታላቅ ሰላማዊ ትእይንተ ህዝብ በአመርቂ ሁኔታ ላሰተባበሩት እና ለውጤት ላበቁት አንድነት ፓርቲንና የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብን “እንኳን ደስ አላችሁ” እያልን የትግል አጋርነታችንንም እንገልጻለን።

እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ገዥው ክፍል የሰልፍ ቦታ በመከልከል፣ ለስልፉ በመቀስቀስና በማስተባበር ተግባር ላይ የተሰማሩትን በማዋከብ፣ በማሰር፣ ወዘተ…. ይህ ሰላማዊ ሰልፍ እውን እንዳይሆን ቢሞክርም፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የፍራቻ ድባብን ሰባብረው፣ ለመብታቸው መከበር ቆርጠው መነሳታቸውን በዚህ ሰላማዊ ትእይንተ ህዝብ ላይ በመሳተፍ አሳይተዋል።

ይህ በጨዋነት እና እጅግ በሰለጠነ ሁኔታ ተጀምሮ የተጠናቀቀው ትእይንተ ህዝብ፣ ቀደም ሲል ከተካሄዱት ሰለማዊ ሰልፎች ጋር ተዳምሮ ሲታይ ህዛባችን ለዓመታት በገዥው ቡድን የደረሰበት ግፍና ከፋፋይነት አብቅቶ መብቱ ሳይሸራረፍ እንዲከበር ለማድረግ ቆርጦ መነሳቱን ያመለክታል።

ይህ የህዝብ መነሳሳት በቀጣይነት እንዲገፋና ወደ “አርድ አንቀጥቅጥ” ሃይልነት እንዲቀየር፣ ትዕግስትና ጥበብ የተሞላበት ቀጣይና የጋራ እንቅስቃሴን ማካሄድ አስፈላጊ ነው እንላለን። በዚህ አኳያ አንድነት ፓርቲና 33ቱ ፓርቲዎች በቀጣይነት ለማካሄድ ላቀዱት ህዝብን ያሳተፈና ማእከል ያደረገ ትግል ያለንን አድናቆትና ድጋፍ እንገልጻለን።

በህዝባችን ላይ የተጫነው የግፍ አገዛዝ አክትሞ በምትኩ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት፣ የሰብዓዊ መብት በተግባር የሚከበርባት፣ የህግ የበላይነት የሚረጋገጠባት፣ አንድነቷ በምንም መልክ ለድርድር የማይቀርብባት፣ ዜጎቿ ሁሉ የሚኮሩባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ዜጋ ትግሉን እንዲደግፍና ተግባራዊ ተሳትፎውንም ከፍ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባልን።

በውጭው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች እና ድርጅቶችም ይህ ውጤትን በማሰመዝገብ ላይ የሚገኝ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲያድግና ስር እንዲሰድ ቀጥተኛ ድጋፋችሁን እንድታበረክቱ፣ ይህን ትግል ለማደናቀፍና ለማጣጣል የሚጥሩትንም አበክራችሁ እንትታገሉ ጥሪ እናቀርባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእስር ላይ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ቶርቸር እየተፈጸመ ነው። ከማጎሪያ እስር ቤት ከእስረኞች የተላከ መልዕክት

የተባበረንና ህዝብን ማእከል ያደረገን ትግል ሊያግድ የሚችል ምንም ሀይል የለም።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

 

5 Comments

  1. every thing possible in Ethiopia……..Ethiopia progressing economically politically ,PEACE full demonstration is good for Ethiopia,….BUT why opposition party..always asking..about extremist , why they r not arrange demonstration for political issue….ANDAREGACHEWU OR MUSLIM AFELALAGI….IS NOT PROBLEM OF ETHIOPIA…OUR PROBLEM IS DEHENET,,,LET THEM STAY IN PRISON..THAT IS THEIR PRIZE .THEY R EXTREMIST …….long live Democratic Republic OF Ethiopia.

  2. አይ ማሞ!አማርኛው ሳይሆንልህ ወደ እንግሊዘኛው ገባህ::ሀሳብህን በእንግሊዘኛ ለመግለፅ መጀመሪያ ኤ ቢ ሲ ዲ በደንብ አጥና! ግን እኮ አንተ ቀድሞ ነገር ሀሳብ idea የሚባል ነገር የለህም:: ገና ለገና ያቺን ፍርፋሪ አጣለሁ ብለህ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው ሲባል ሲቃ ያዘህ! እንግዲህ ወያኔ እንዳንተ ያለውን ነው ሰብስቦ የያዘው! አሁን በእንግሊዘኛ የፃፍከው ምን ለማለት እንደፈለክ ካንተ በቀር የሚረዳው የለም::ይሄኔ ያ የፈረደበት MA ዲግሪ ከድንጋይ ማምረቻ ተቁዋም በእጅህ ገብቱዋል::አለበለዚያማ እንግሊዘኛዋን ጭራሽ አትሞክራትም ነበር::አሁን እኔ የምመክርህ መሞንጨሩን ትተህ እኛ የምንፅፈውን እያነበብክ ተማር!ይሄ የደንቆሮ ካድሬዎች መድረክ አይደለም!

  3. የትግል አጋርነትን መግለጽ በፊት ነበር የሚያምረው….

    ካለፈ በኋላ፡

    ውጤታማ መሆኑ ከታወቀ በኋላ፡

    ድጋፍ ማስጠት ማን ያቅተዋል!

  4. Mamo kilo, I see you are a very sick man. Those people who are languishing in kality prison are brave Ethiopians. They are there because of principle. The whole world knows that these people are there to defend their religion from atheist like you. Others are there for simple reason that to free the Ethiopian people, including you. You probably do not know it, but I tell you that you are in very terrible prison yourself. You are in the prison of hate, stubbornness, racism, malice, anger, violence, lie, and deceit. You are advised to get out your prison. We are going to dismantle what you call democratic republic whatever. There is no democracy in Ethiopia. That is the main reason that I believe you are in the prison of lie. If you keep believing you lie, there is nothing we can do about you. What is left for you is to stay in prison of lie. Who is the father lie? Read the gospel of John 8:45. You will get the answer.

Comments are closed.

Share