የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ

ከግራ ወደ ቀኝ – ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ተክሌ በቀለ ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራት ከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡

ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡

ለመጨረሻው ዙር ሳያልፉ የቀሩት አቶ ትግስቱ አወሉ እና አቶ ሽመልስ ሀብቴ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረው አንድነትን ለመምራት ከሚመረጠው ቀጣይ ሊቀመንበር ጋር ትግሉን ለማፋጠን እንደሚተጉ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5718#sthash.mnRx1QXg.dpuf

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባህርዳር ውጥረት ውስጥ ናት፥ ዘመነ ካሴን ለመያዝ የተደረገው የመጀመሪያ ሙከራ ከሽፏል፥ በአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ቀጥሏል

2 Comments

  1. Why this guy(Giachew) again? This was the person who weakened and divided UDJ,when he bring Siye Abraha to take over the party.I don’t trust Gizachew any more,he should not be around at all,leave alone choosing him as a chair person.these old guards must retire.let the new Generation lead our country.

Comments are closed.

Share