ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ የማራቶን ውድድር ድል ቀናቸው

May 7, 2017

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገው የፕራግ ማራቶን ድል ቀናቸው:: በወንዶች ምድብ በተደረገ ውድድር ኢትጵያዊያን ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ቦታ ይዘው አጠናቀዋል::
ገብረጻድቅ አብርሃ ውድድሩን 2፤08፤47 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አንደኛ ሲሆን ባዙ ወርቁና መኩዋንት አየነው ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ምድብ በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ሲጨርሱ ኬንያዊቷ ቫላሪ ጀሚሊ አይአቤይ 2፡21፡57 በሆነ ሰዓት ገብታ ውድድሩን አሸንፋለች::
አማኔ በሪሶ በ2፣22፣15 ሁለተኛ ስትሆን ታደለች በቀለ በ2፡22፡23 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች:፡

Previous Story

«ደሸት» የብርሃን እውነት! -ወለላዬ ከስዊድን

Next Story

«ፍልስፍና የሚጀምረው ከመደነቅ ነው» – የሞረሽ ወገኔ አዲስ መግለጫ

Go toTop