ለጥንቃቄ፦ ካድሬዎች በሞቫይል ስልክ እያደናበሩ ነው!

የህወሓት መሪዎች የመረጃ ምንጮቼ ለመሰለልና ምናልባት ኔትዎርክ እንዳለኝ ለማወቅ ከኔ ጋር ቅርበት ወዳላቸው ሰዎች (በካድሬዎቻቸው በኩል) ‘አብርሃ ደስታ’ መስለው በመደወል ዜጎችን እያወናበዱ መሆናቸው ደርሼበታለሁ።

 

‘አብርሃ ደስታን ሊያውቁ ይችላሉ’ ተብለው ለሚገመቱ ሰዎች (ካድሬዎቹ) እየደወሉ ‘አብርሃ ደስታ ነኝ፤ ….. ለምናምን ነገር ፈልጌሃለሁ፣ የት ነህ፣ መረጃ ስጠኝ ወዘተረፈ …’ እያሉ ንፁሃን ዜጎች እያደናበሩ ነው።

ዜጎች ለማደናበርና ለመሰለል ከተዘጋጁ ካድሬዎች (የአብርሃን ጉዳይ ለማጥናት) ወደ ሐውዜን ተልከው የጥፋት ተልእኳቸውን እየፈፀሙ ያሉ 13 ግለ ሰቦች ሲሆኑ በመቐለ ደግሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አሉ። ወደ ሐውዜን ከተላኩ የተወሰኑ ስም ዝርዝራቸው ደርሶኛል።

ስለዚህ በሐውዜን፣ መቐለ እንዲሁም በሌሎች አከባቢዎች የምትገኙ ጓደኞቼ ‘አብርሃ ደስታ ነኝ’ ብሎ ለሚደውልላቹ ማንኛውም ሰው ከማመናቹና መረጃ ከመስጠታቹ በፊት እንድታረጋግጡ በትህትና አሳስባለሁኝ። ‘አብርሃ ደስታ ነኝ’ የሚል ደዋይ ካጋጠማቹ የተደወለላቹሁ ስልክ ቁጥር በፌስቡክ መልእክት አድርሱኝ። ማንነቱ አጣርተን እናጋልጠዋለን። ስልክ ቁጥሬን የምታውቁ ካላቹ ደግሞ እኔ መሆኔን ደውላቹ አረጋግጡ፤ አደራ።

ሰሙኑ አቶ አባይ ወልዱ ታማኝ የተባሉ የፓርቲው ሰዎች ሰብስቦ በአብርሃ ደስታ እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንከር ያለ የስለላ ተግባር መከናወን እንዳለበት ትእዛዝ ሰጥተዋል። የአባይ ወልዱ ዛቻ ትርጉም የሚሰጠው ባይሆንም ጥንቃቄ ማድረጉ ግን ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ቴሌን በሕገወጥ መንገድ ለፓርቲ ስለላ እየተጠቀመ ነው። ብዙ ጉዳትም ሊያደርስ ይችላል።

ህወሓት የመንግስት ሃብት (ቴሌን) ለግል (ለፓርቲ) ጥቅም በማዋል በሙስና ሊከሰስ በተገባ ነበር። ለካ ቴሌን ለፓርቲ ጥቅም ለማዋል ነው በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገው።

ግን…

በአሁኑ ሰዓት የደህንነት ሰዎች በጣም ተዳክመዋል። በስለላ እየተሰማሩ ያሉ የደህንነት ሰዎች ሳይሆኑ ተራ (ግን ታማኝ የሚባሉ) ካድሬዎች ናቸው። እነዚህ ሆድ-አደሮች ማሸነፍ ደግሞ ቀላል ነው።

It is so!!!

! ……. የገዢዎቻችን ነገር ……….!

ኣንድ

በ1993 ዓም የህወሓት ክፍፍል መለስ የነ ስየ/ተወልደ ቡድን ለማሸነፍ በህወሓት ሰነፎች (የራሳቸው ነፃ ሓሳብ ያልነበራቸው) የፓርቲው ሰዎች ኣሰባስቦ ‘እኔን መርጠዋል’ ብሎ በህወሓት ሊቀመንበርነቱና የጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣኑ ይዞ እንደሚቆይ ኣሳወቀ። ኣቶ ኣባይ ወልዱም ይሄንን ‘የመለስ ራእይ’ (ሰነፎች ማሰባሰብ፣ ጎበዞች ማባረር) እየተገበረ ይገኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው ሕዝባዊ አመጽ ገቢዬን ቀንሶብኛል ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አማረረ

ሰነፎቹ ስልጣን ተረካቢዎች ኣሁን የጠበቁት የህዝብ ድጋፍ ባለ ማግኘታቸው ግራ ተጋብተው የሚናገሩትን ነገር እስካለማወቅ ደርሰዋል። በተለይ ኣዜብ መስፍንና ኣባይ ወልዱ (እንዲሁም ስብሓት ነጋ) ለሚናገሩት ነገር ‘ይቅር’ እንበላቸው። ብቁ ፖለቲከኞች ኣለመሆናቸው እየነገሩን ነው። ጭንቀታቸው በኣደባብይ ሲናገሩ ያሳዝናሉ።

ሁለት

የህወሓት መሪዎች ከስልጣን መውረድ የማይፈልጉበት ምክንያት (1) እስካሁን የሰሩት ጥፋት እንዳይጋለጥ ይሰጋሉ። (2) የትእምትን ሃብት ማጣት ኣይፈልጉም። (3) ፓርቲው ስልጣን ከለቀቀ ልክ እንደ የድሮ የደርግ ባለስልጣናት በጠላትነት ተፈርጀው ከሀገር የሚባረሩ ይመስላቸዋል።

‘ትእምት ግን የማን ነው?’ ብለን ስንጠይቅ መልሱ ‘የህወሓት መሪዎች’ የሚል እንደሚሆን ግልፅ ነው። ባለፈው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የማረት ሓላፊ ኣቶ ተክለወይኒ ኣሰፋ ትእምት የህወሓት ንብረት እንጂ የትግራይ ህዝብ ሃብት እንዳልሆነ መናገሩ የሚገልፅ post ኣድርጌ ነበር። (መረጃው ያገኘሁት ከፌስቡክ ጓደኛየ ነበር)። መቼና የት እንደተናገረው መጥቀስ እንዳለብኝ ከጓደኞቼ ኣስተያየት ደርሶኛል።

ከተሰጡኝ ኣስተያየቶች በመነሳት ለማጣራት ስሞክር ተክለወይኒ ኣሰፋ ይሄን የተናገረው ባለፈው ዓመት ሮብ ሚያዝያ 10, 2004 ዓም ሲሆን ቦታው በMIT የስብሰባ ኣዳራሽ እንደነበር ለመረዳት ችያለሁ። ‘ለምን ያን እንዲናገር (ኣምኖ እንዲቀበል) ተገደደ?’ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ነው፣ ምክንያቱም ብዙ ግዜ (ወይ ሁልግዜ) የህወሓት መሪዎች ትእምት የግል ሃብታቸው መሆኑ እያወቁ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ግን ‘ትእምት የህዝብ ነው’ ይሉን ነበር።

MIT (Mekelle Institute of Technology) ሲቋቋም ዓላማው የክልሉ ጎበዝ ተማሪዎች ተመጠው እዛው ተምረው ገዢውን ፓርቲ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ታስቦ ነበር። ቁስ ነገር በመስጠት ጎበዝ ልጆችን ባርያ ኣድርጎ ለመግዛት፣ ይህንን ካልተቻለ ደግሞ ስርዓቱ እንዳይቃወሙ ለማድረግ ነ ው። ህወሓቶች ጎበዝ ተማሪዎችን (ወይ ሙሁራን ባጠቃላይ) ይፈራሉ። ምክንያቱም እነሱ በደምብ የሚያውቁት በሓሳብ ማሸነፍ ሳይሆን ተኩሶ መግደል ነው። ኣሁን የቸገራቸው ይሄንን ነው፤ (ውድድሩ በጠመንጃ ሳይሆን በሓሳብ መሆኑ)።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምስራቅ ጎጃም የመኢአድ አባል በካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አለፈ

የMIT ተማሪዎች ግን ህወሓቶች እንደጠበቁት (ስለበሉ ስለጠጡ) ‘ታማኝ ኣገልጋዮች’ መሆን ኣልቻሉም። ጥያቄዎች ማንሳት፣ መብት መጠየቅ፣ መቃወም … ምናምን ጀመሩ። ማስተካከል እንዳለባቸው ተነገራቸው። ኣልተሳካም። ህወሓቶች በጉዳዩ ተሰብስበው ተወያዩ። ‘እነዚህ ተማሪዎች በራሳችን ገንዘብ ኣስተምረን ለኛ ጠላቶች እየፈጠርን ነን።’ (MIT fund የሚደረገው ከትእምት ነበር)። እንደዉጤቱም ‘ጠላቶች’ ለመፍጠር ገንዘባቸው ማባከን እንደሌለባቸው ተስማምተው የMIT ቡጀት ተዘግቶ ተቋሙ ወደ መቐለ ዩኒቨርስቲ እንዲጠቃለል (በጀቱ ከፌደራል መንግስት እንዲሆን ተወሰነ)።

ይሄን ዉሳኔ የMIT ማህበረሰብ ተቃወመው (በወቅቱ ስለ ጉዳዩ ፅፌ ነበር)። ብዙ ችግር ተፈጠረ። የህወሓት መሪዎች የMIT ማህበረሰብ (ተማሪዎችና ኣስተማሪዎች) እየሰበሰቡ ማነጋገር ተያያዙት ። ከነዚህ መሪዎች ኣንዱ ተክለወይኒ ኣሰፋ ነበር። እሱ ተማሪዎቹን ሰብስቦ በበጀት እጥረት ምክንያት MIT fund ማድረግ እንደማይችሉና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኣካል መሆን እንዳለበት ይነግሯቸዋል። ሰመረ የተባለ ተማሪ እጁን በማውጣት ‘ትእምት የትግራይ ህዝብ ሃብት ነው ትሉናላቹ ግን በትክክል የህዝብ ከሆነ ለምን ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ ኣታውሉትም?’ ብሎ ይጠይቃል። ተክለወይኒም በጣም ተናዶ “ማን ኣለህ ዉሸታም! ትእምት (EFFORT) የህወሓት ነው፤ ህዝብ ደሞ ማነው?” (“መን ኢሉካ ሓሳዊ! ትእምት ናይ ህወሓት እዩ። ታይ እዩ ህዝቢ ኸ?” ብሎ መለሰለት።

ተክለወይኒ እንዲህ መናገሩ ምን ኣዲስ ነገር ኣለው? ኣዲስ ነገር ኣይደለም። ምናልባት ኣዲስ ከሆነ ግን በራሳቸው ኣንደበት በህዝብ ፊት መናገራቸው ብቻ ነው እንጂ የህወሓት መሆኑማ ማንም ሰው ያውቃል። ኣሁን ኣሁን እኮ ግን ትእምት የህወሓት ኣባላት መሆኑ ቀርተዋል። ትእምት የሁሉም ኣባላት ኣይደለም። ትእምት የተወሰኑ የህወሓት መሪዎች የግል ሃብት ነው። የጥቂት ሰዎች ነው።

ሦስት

በመኾኒ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖርያ ቤቶች እንደሚፈርሱ በመንግስት ኣካላት ከተነገረ በኋላ ኗሪዎቹ ኣማራጭ መጠልያ እንዲዘጋጅላቸው ቢጠይቁም መፍትሔ እንዳላገኙ ጠቅሼ ነበር። ከዚህ በመነሳት “ቤቶቹ የሚፈርሱት በምን ምክንያት ነው?” የሚል ነገር ተነስተዋል። የሚፈርስበት ምክንያት “ሕገ ወጥ ግንባታ” ተብሎ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio ተገሏል ተብሎ ሲወራበት የነበረው ታጋይ ተስፋሁን አለምነህ ከኤርትራ ተናገረ - "የአማራ ሕዝብ ካልታጠቀ ከሕወሓት ጥቃት አያመልጥም" ቤተአማራ

በመኾኒ ወደ 7 ሺ የሚጠጉ ቤቶች ‘ሕገ ወጥ’ ከሆኑ ‘ሕጋዊ የሆነ ቤት የለም’ ልንል ነው። ግን ይህን ሁሉ ቤት ‘በሕገውጥ መንገድ’ ሲገነባ (ለብዙ ዓመትም ኑሮበታል) ኣስተዳዳሪዎቹ (የመንግስት ተወካዮቹ ) የት ነበሩ? እስኪገነባ ድረስ ዝም ብለው እያዩ ነበር ወይስ ከተገነቡ በኃላ፣ ኣገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በኋላ ነው ‘ሕገወጥ’ የሆኑት? ‘ሕገወጥ’ ቤት ከተገነባ ከጅምሩ ነው መቆም የነበረበት። ራሳቸው ይፈቅዳሉ፣ ይሰጣሉ፣ በኋላ ያፈርሳሉ። ይህንን ተግባር በነዋሪዎቹ የሚፈጥረው የስነ ልቦና ችግር ቀላል ኣይደለም። እንደዚህ ዓይነት ችግር ከመልካም ኣስተዳደር እጦት የሚመነጭ ነው።

የህወሓት መሪዎች ያዳላሉ። ምሳሌ ልስጣቹ፡ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በመቐለ ከተማ የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ጉድ ነበር። ብዙ የከተማው ነዋሪዎች ‘ሰራዋት’ ተብሎ በሚጠራ ኣከባቢ (የከተማው ኣስተዳደር ፍቃድ ኣግኝተው፣ ማንም ሳይከለክላቸው) በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተገነቡ። ኣገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

በተመሳሳይ መልኩ (በተመሳሳይ ግዜና ሁኔታ) ግን ለየት ባለ ቦታና ለየት ባሉ ሰዎች ሌላ ዓይነት ቤቶች (ቪላዎች) ይገነቡ ነበር። እነዚህ ለየት ባለ ቦታ የተገነቡ ቪላዎች Hill Top Hotel ኣከባቢ በሚገኝ ‘ልዩ መንደር’ ነው። ‘ልዩ መንደር’ ያልኩበት ምክንያት እዛ ኣከባቢ ቤት መስራት የሚፈቀድለት ሰው የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን መሆን ኣለበት። ሌላ ተራ ሰው እዛ ኣከባቢ ቤት መስራት ኣይፈቀድለትም። በወቅጡ የነበረ “ጥሕሎ” የተሰኘ መፅሔት “ኣፓርታይድ መንደር” ብሎ ሰይሞታል። እስካሁንም “ኣፓርታይድ መንደር” ተብሎ ይጠራል። ባለስልጣናቱ ለብቻቸው ተለይተው የሚኖሩበት ሠፈር ስለሆነ ነው።

ሁለቱም የ’ሰራዋት’ (የሰላማዊ ሰው)ና ‘ኣፓርታይድ መንደር’ (የባለስልጣናቱ) የቤት ግንባታዎች ማንሳት ለምን ኣስፈለገ? በሰራዋት የተገነቡ ቤቶች ሁሉም በግፍ (በዶዘሮች) እንዲፈርሱ ሲደረግ የባለስልጣናቱ (ኣፓርታይድ መንደር) ግን ማንም ሳይነካው እስከኣሁን ድረስ ኣለ። የተራ ህዝብ ፈረሰ (ሕገወጥ ተባለ) የራሳቸው (የባለስልጣናቱ) ግን ‘ሕጋዊ ሆነ’ (ምክንያቱም እነሱ ኮ ከሕግ በላይ ናቸው)።

ወይ ኣድልዎ!

It is so!!!

 

5 Comments

  1. Abrham:

    Be careful brother, the apartheid regime and the war lord, Abey Woldu, may intimidate you and may be attempt to kill you. I will love to read your thought every day. I am proud of you, and have a little hope when I read your manuscript.

    God bless you keep it up!!!

  2. May God Bless you Abreha! I never ever see a determined young, who decided to live truth, in one of the most dengerous zone. As you said, without going anywhere, even for data collection, you won the whole AGAZI, and my government who is above law. Pls keep that: Ethiopia need a determined peaceful struggler like you. May God bless your pen! I am always proud of you!

  3. long life to you brother. there are some who still are fighting for the truth and the people. You made my day hopeful.

Comments are closed.

Share