በሳንጃ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተወረወረ ቦምብ 6 ሰዎች ቆሰሉ | ከፋኝ ጦር አስተዳዳሪው ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት አደረሰ

ከሙሉነህ ዮሐንስ

ጎንደር ሳንጃ ከተማ በውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ ተዘገበ:: ላለፉት ጥቂት ቀናት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሰነበተችው ሳንጃ ከተማ ውስጥ ከሕወሓት መንግስትና በኩልም እንዲሁም ከከፋኝ ጦርም ጥቃቶች ተሰንዝረዋል::

አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ በ12/07/09 ከምሽቱ 3፡09 ሰዓት በከፋኝ ጦር ወደ ከተማዋ እያሱ ይላቅ ቦንብ አስተዳዳሪው ቤት ተወርውሮ ጉዳት ማድረሳቸው ተዘግቧል:: የከፋኝ ሃይሎች የጀግናው ጎቤ መልኬ ደም በከንቱ ፈሶ አልቀረም ጥቃቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸው ታውቋል።

በጥቃቱ የተበሳጨው ወያኔ ከፋኞችን ከህዝብ ለማጣላት በንግድ ባንክ ላይ ፈንጅ ጥቃት እንደሰነዘረ ጥብቅ መረጃ ደርሶናል። እማኞች እንደጠቀሱት በተመሳሳይ ቀን ሳንጃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተወረወረ የወያኔ ቦንብ ጥቃት ስድስት ሰዎች ቆስለው በአሁኑ ሰዓት ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

ሳንጃ ከተማ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡነ አብረሀም ኮሚሽነሩን አስጠነቀቁ በደመራ ወቅት አደገኛ ዕቅድ ታቅዷል በበአስቸኳይ ተጠንቀቁ ሕገወጡ ቡድን ኢሬቻን ምክንያት በማድረግ ተነሳ
Share