የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጦች ታወቁ

(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ በየዓመቱ አንባቢዎቻቸውን በማሳተፍ “የዓመቱ ምርጥ ሰው” በማለት ይሰይማሉ። ከ2 ዓመት በፊት መምህር የኔሰው ገብሬ በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ዓመት ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት 598 ሰዎች በዓመቱ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ያሉትን ምርጥ ሰው ጠቁመዋል። በተለይ አንባቢዎች እስር ቤት የሚገኙ ወገኖችን አንዱን ከአንዱ ማበላለጥ እንዳይሆን የሚል ፍራቻቸውን እየገለጹ የነበረ ቢሆንም በምርጫው ሕዝቡ እስር ቤት ያሉትን ሰዎች አስታውሶ መምረጡ በራሱ የታሰሩት ወገኖች እንዳልተረሱ ያሳያል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በሌላ በኩል ነበሩ።
የዘ-ሐበሻ 598 መራጮች ባደረጉት ምርጫ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጦች የሚከተሉት ናቸው። (ይህ ማለት ግን ሌሎቹ ምርጥ አይደሉም ማለት ሳይሆን ብዙ ድምጽ ያገኙ ለማለት ነው)

የዓመቱ ምርጥ ሰው፦ አንዷዓለም አራጌ

የዓመቱ ምርጥ ሰላማዊ ትግል፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች

የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ (ከወንዶች)፡ ፡ ተመስገን ደሳለኝ

የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ (ከሴቶች) ፡ ርዕዮት ዓለሙ

የዓመቱ ምርጥ አክቲቪስት ታማኝ በየነ

የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ መሐመድ አማን

(አጠቃላዩን ውጤት በPDF ይመልከቱት)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የምርጫ ህጉን፣ የምርጫ ዘመቻ መመሪያን የሚተላለፉ ንግግሮችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

10 Comments

  1. Just happy Andualem won. Happy new to all the weyane political prisoners! Hope 2006 will be better year to all of us.

  2. Dear Editor! It is a good exercise to select and award contributing people. However, selection should also follow some kind of principles and hence your effort could be legitmet. I tell you including Jawar Mohamed in such a public based selection is a futile. How honest, a guy who is promoting throat cut as his big agenda would be in your list? How you include a person who denied his Ethiopian Citizenship in your list? This shows your total neglect for us who use z habesha as a media.

    It also brought to my mind the two bad choices given to Ertrians—would like to be free or slave?!

    Don’t put very different things as if they are similar. Lewedefitu enkeredade ena sende kelakilachehu lewededer atakerbu!

  3. ጥሩ ምርጫ ነዉ። የአመቱ አሳዛኝና የጅምላ ድብደባ የነሀሴ 3,2005ቱ የኢድ እለት የተከናወነዉ፡ነዉ።ድብደባዉን ለየት ያደረገዉ ደግሞ ህፃን፣ሽማግሌ፡አሮጊት፡አለመለየቱ ብቻም ሳይሆን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድ ጊዜ የድብደባዉ ሰለባ መሆናቸዉ ነዉ።

  4. ጥሩ ምርጫ ነዉ። የአመቱ አሳዛኝና የጅምላ ድብደባ የነሀሴ 3,2005ቱ የኢድ እለት የተከናወነዉ፡ነዉ።ድብደባዉን ለየት ያደረገዉ ደግሞ ህፃን፣ሽማግሌ፡አሮጊት፡አለመለየቱ ብቻም ሳይሆን በፆመኛ አንጀታቸዉ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድ ጊዜ የድብደባዉ ሰለባ መሆናቸዉ ነዉ።

  5. .>>ይሁን መልካም ነው! አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!! ለፉገራ ሥማችሁ የቀረበ አቤት ሲያሳዝኑ!!
    ፩) እንኳንም አቶ መለስ አልሆኑ! “አንኳንም መለስ ሞቱ” ለብዙ ሙሰኞች ለአነስተኛና ጥቃቅን ካድሬዎች ሥራና ሀብት ፈጥረው ለደንቆሮ ምሁራን መፅሐፍ ፅፈው አልፈዋልና፣ እነሱም ቤተመንግስት ድረስ ባነር ወጥረውና ተወጥረው አልቅሰዋል፣ እያለቀሰም ነው፣ ገና ያለቅሳሉም! ለብሔር ብሔረሰብ ባሕላዊ ለቅሶ ማሳያ ተመርጠዋል።
    ፪) እንኳንም ‘ጃዋር’ አልሆነ የድምፁ ቅላጼ የተሸራራፈ፣ ከቅኝት የወጣ ነበር። አድናቂዎቹ ግን በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓና በደቡብ አፍሪካ ታላቀ መሪያችንና ተንታኛችን ሲሉ ብዙ ቀላምደዋል። አሁን ያሰማውን ድምፅ ዶ/ር ገብረጺዮን ገብረሚካኤል በደንብ ሠምተውታል! ‘ሜንጫ’ ጉዱ ፈላ!? አጉል መንጫጫትን ጨምሮ ማለት ነው!።
    ***አንድ በደቡብ የሀገራችን ክፍል ‘በሜንጫ’ ተላለቁ፣ ክርስቲያኑን እረዱት፣ ቤተክርስቲያኑን አቃጥሉ፣ ኢኮኖሚውን፣ መከላከያውን፣ ፖለቲካውን፣ ተቆጣጠሩት ሲባል የሰማው ኢትዮጵያዊ ‘በገጀራ’ የሂሳብ ትምህርት አስተማረበት! አይ የአሜሪካ የፖለቲካ ተንታኝና የሀገረ ኢትዮጵያ የገጠሩ መልካም መምህር ልዩነት!? ዘየገርምዩ አለ፣ ትዝብቲ መሌ አለ.. **የዓመቱ የምርጥ ሠላማዊ ትግል*** አሸናፊዎች እጅግ በጣም የሚደገፍ ነው። ሌባን ሠርጎ ገብን፣ አስመሳይ ጎጠኛና ዘረኝነትን ተጠንቀቁ ! የጠላትህ ጠላት…የአንተ ፍፅም ወዳጅ አይሆንም! የጠላትህም ፍፅዩም ጠላቱ አደለም በለው! መጪው ዘመን የጥሩ ዜጋ ማፍሪያ፣ ለሀገሩና ለሕዝቡ ቅን አሳቢ በሀገርና በማንነቱ የማይደራደር እንቢኝ ባይ ትውልድ ይወለድ! ታፍራና ተከብራ የኖረች የሁላችን ሀገር ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! የ፳፻፮ዓመት የሠላምና የጤና ይሁን!!አንድ የዶሮ እንቁላል ፪ከ፶ !? ብልጽግና ሳይሆን ብልግና ነው በለው! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

  6. የ አመቱ ምርት ሳው ከታወቀ የ10 አመቱ ምርጥ ሌባ ማነው? አዜብ እንዳትሉጘ… እሳቸው ሃዘን ላኢ ናቸው ከሰሞኑ ምህረት በተደረገላቸው ሰዎች ምትክ ስለሚገቡ

Comments are closed.

Share