የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2ለ1 አሸንፎ የዓለም ዋንጫ ጉዞውን አሳመረ

(ዘ-ሐበሻ) ብራዚል ላይ ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ከደቡብ አፍሪካ፣ ቦስትዋና እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ተደልድሎ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ6 ጨዋታ 13 ነጥቦችን በማግኘት ወደ ዓለም ዋንጫ የሚያደርገውን ጉዞ አሳመረ። ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በኮንጎ በስታድ ማሴምቤ ስታዴየም የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክን በወሳኝ ጨዋታ ገጥሞ 2ለ1 በማሸነፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስፈንጥዟል። በዚሁ ኢትዮጵያ ካለችበት ምድብ ደቡብ አፍሪካ ቦስትዋናን ገጥማ 4ለ1 ብታሸንፍም ያላት ነጥብ በድምሩ 11 ብቻ በመሆኑ ከዓለም ዋንጫ በማጣሪያው ልትሰናበት ግድ ሆኖባታል።
ሐገር ተጫወተ ጎል ነጥብ
ETH 6 8 13
RSA 6 12 11
BOT 6 8 7
CTA 6 5 3

በዛሬው ጨዋታ እስከ እረፍት ባለው ጨዋታ ብሔራዉ ቡድናችን በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ተጫዋቾች ከመበለጣቸውም በላይ 1 ለ 0 ሲመሩን ቆይተዋል። ሆኖም ግን ዋሊያዎቹ ከ እረፍት መልስ ጨዋታውን በመቀየር ሳላዲን አህመድ በ48ኛው ደቂቃ እንዲሁም ምን ያህል ተሾመ በ61ኛው ደቂቃ ባገቡት ጎል 2ለ1 አሸንፏል።

ብሔራዊ ቡድናችን በብራዚኡ የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ከአሁን በኋላ ከአንድ ብሄራዊ ቡድን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ይቀራቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ስምምነት ሊፈፅሙ ነው"

1 Comment

Comments are closed.

Share